>

አቶ አባይ ወልዱና ዶ/ር አብርሀም ተከስተ መያዛቸው ተረጋግጧል...!!! (ሚዛን ዜና)

አቶ አባይ ወልዱና ዶ/ር አብርሀም ተከስተ መያዛቸው  ተረጋግጧል…!!!

ሚዛን ዜና

ከዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል በፊት የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አባይ ወልዱና የቀድሞው የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ሚንስትር ዶር አብርሀም ተከስተ መያዛቸውን የመከላከያ ሚንስቴር ምንጮች ገለጹ።
ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የመከላከያ ምንጮች ለሚዛን እንደገለጹት ሁለቱ የሕወሐት ባላስልጣናት መከላካያ ሰራዊቱ ሰሞኑን ባካሄደው አሰሳ ተይዘዋል።
ዶክተር አብርሀም ተከስተ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስትርነት ተነስተው ወደ መቀሌ ከሄዱ በኋላ የትግራይ ክልል ንግድና ኢዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ናቸው።
ሁለቱ የሕወሐትት ቁንጮ ባላስልጣናት ከተያዙ በኋላ ለምን በመንግስት በኩል እስካሁን ይፋ እንዳልተደረገ ምንጩ ምክንያቱን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
ምናልባትም ሁለቱ ባላስልጣናት መያዛቸው ያልተገለጸው የሕወሐት ስትራቴጂስት የነበሩትን አቶ ስብሀት ነጋን በማስቀደም ለሎችን ለማስከተል የታለመ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
በቀጣይም በጦርነቱ ተደምስሰዋል የተባሉ ሁለት የሕወሐት ጄኔራሎችን መንግስት በማጣራት ላይ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገልጸውልኛል።
መንግስት የአቶ አባይ ወልዱ እና የዶር አብርሀም ተከስተን መያዝ ግልጽ ከማድረግ ቢቆጠብም ምናልባት በቀጣዮቹ ቀናት ይፋ ሊያደረገው እንደሚችልም ይጠበቃል።
ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሕወሀት ጋር በተካሄደው ጦርነት የተገደሉም ሆነ የተያዙ ሌሎች የሕወሀት ባለስልጣናት ስም ዝርዝርን መንግስት ይዟል።
በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት ጉዳዩን ለምን በሚስጥር ይዞ ቀስ እያለ ስማቸውን ይፋ እንደሚያደርግ ግን ምክንያቱ ግልጽ አይደለም።
Filed in: Amharic