ፍፃሜያቸውን ያፈጠነው የመጨረሻው ውሳኔ!!!
ደጀኔ አሰፋ
<< የሰሜን እዝን ለመውጋት ረቡዕ ጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ወሳኔ አሳለፉ! አለም ገብረዋህድ የውሳኔው ዋነኛው ተዋናይ ነበር!!!! >>
*.. አዎ!!! በመጨረሻ ፍትህ አሸነፈች!!!
ኢትዮጵያ አሸነፈች!!!
ኢትዮጵያን አፍርሰው ትግራይ የምትባል አገር ለመፍጠር ሲያሴሩ የኖሩ ድኩማኖች በመጨረሻ ራሳቸው ተዋርደው ተበትነዋል!!!! ፈርሰዋል!!! ድርጅታቸው ጠፍቷል!!! ህወሃት ታሪክ ሆኗል!!!!
ከኢትዮጵያ በዘረፉት ሃብት እና ንብረት ትግራይ የምትባል አገር መፍጠር እንደማይችሉ ብቻ ሳይሆን የዘረፉትን ገንዘብ መብላት እንኳን እንዳልቻሉ ታይቷል!!! ስንት ቢሊየን ብር ዘርፈው የሲጋራ ቁሩ ሲለምኑ በአይናችን አይተናል!!!
እነዚህ ድንዙዛን ጁንታዎች አይደለም አዲስ ትግራይን ሊፈጥሩ ይቅርና “ህዝቤ” የሚሉትን የትግራይን ህዝብ እንኳን በአግባቡ መጠበቅ የማይችሉ እንኩቶዎች እና ከሃዲዎች መሆናቸው ተረጋግጧል!!! ህዝቡን ትተውት ፈርጥጠዋል!!! ታሪክ መዝግቦታል!!
የትህነግ ችግር ከጥንስሱ ጀምሮ የአመራር (የ leadership) ችግር ነው!!! ሲነሳም በቀነጨሩ አእምሮዎች ተቀምሮ መገንጠልን በአላማነት ያነገበ የወንበዴዎች ስብስብ ነው:: በዚህ የመከነ እሳቤያቸው ሳቢያ የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት 45 አመታት ፍዳውን በልቷል:: ጭራሽ መንግስት ሲሆኑ አገሪቱን አዘቅት ውስጥ አስገቧት:: ህዝብን ከህዝብ እያባሉ እድሜ ለመቀጠል ብዙ አደረጉ:: አደኸዩን:: የገንዘብም የእሴትም የሞራልም ድሃ አደረጉን:: ኢትዮጵያውያን ያለ እሴት ባዶ እጃችንን ቀረን:: መተዛዘንን አጠፉት:: ወንድማማችነትን አረከሱት:: መተማመን ሞኝነት ሆኖ ሴራ የፖለቲካ ልሂቅነት ማሳያ ሆነ:: ክህደትን መገለጫ አደረጉት:: በደም ላይ ደም ጨቀየን:: ወዘተ . . . .
.
ከጥንስሱ ጀምሮ ትህነግ የአመራርም የሃሳብም የአካሄድም ጥልቅ ችግር ነበረበት:: ሰው የላቸውም:: የተለየ ሃሳብ ያለው ሰው ከመጣ ደግሞ ያጠፉታል:: ከሃዲ ባንዳ ይሉታል:: ለፖለቲካቸው ታማኝ ከሆንክ ብቻ በህይወት እንድትኖር ይፈቀድልሃል:: ከጥንት ጀምሮ የትህነግ ሊደርሽፕ ችግር ቢኖርበትም ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ሊደርሽፑ ሙሉ በሙሉ ወድቋል (fail አድርጓል)!!! Leadership failure!!! ጁንታው የተሸነፈው በወታደራዊ መስክ ብቻ አይደለም:: ከዚያ ይልቅ ፖለቲካዊ ውድቀታቸው የከፋ ነው:: የጁንታው አወዳደቅ ያላማረው በመሳሪያ ማነስ ሳይሆን ፖለቲካቸው በደረቀ ጭንቅላት ስለተመራ ነው!!!! በደነዘዘ ህሊና ፖለቲካውን ስላቦኩት ነው:: ጭንቅላታቸው ደረቀ:: ከዚያም እንደተባለው ኪሳቸው እየደረቀ ሲሄድ እጅግ ደነገጡ:: የብር ኖት ቅያሪው ብቻ የሚይዙትን የሚጨብጡትን አሳጣቸው:: ከዚያም መላ ሰውነታቸው ደረቀ:: በድን ሆኑ:: ያልሆነ ፈንጅ ረገጡ:: ገሚሱ ተደመሰሰ ገሚሱ ተማረከ ገሚሱ አሞራ በላው ገሚሱ አንገቱ ተቆረጠ!!! . . .ፍፃሜያቸው ይሄው ሆነ!
.
አሁን በማንም ላይ ማላከክ አይችሉም:: ነውር ነው!!! ዶክተር አብይ ሶስት አመት ሙሉ በአንቃልባ አዝሎ እሽሩሩ አላቸው:: አያሌ እድሎች ተሰጣቸው:: የወንድ በር ተከፈተላቸው:: እድሉን እንደመጠቀም አፌዙበት:: እብሪታቸው ሰማይ ነካ:: እንደ ልመና ቆጠሩት:: በኢትዮጵያ ላይ ተዘባበቱ:: ፈርሳለች እያሉ አሟረቱ:: የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም አለ:: መንግስት ግራ ገባው:: በትዕግስት ጠበቃቸው:: እነሱ ግን በእብሪት ታወሩ:: የማይሆን ፈንጅ ረገጡ:: ሰሜን እዝን በለሊት ወጉት:: እንደተኙ አረዷቸው:: ገሚሱን ራቁቱን ባዶ እግሩን አባረሩት:: የገሚሶቹን አስከሬን አቃጠሉ:: አስክሬን እየመረጡ ሳይቀብሩ ቀሩ:: ምድሪቱ መሸከም የማትችለውን ግፍ ፈፀሙ:: ይህንን ግፍ “መብረቃዊ” ጥቃት ሲሉም አሞካሹት:: ይህም ሌላ ግፍ ሆኖ ተመዘገበ:: ኢትዮጵያውያን ወደ ውስጥ አነቡ:: እናቶች ሃዘናቸው አልወጣ አላቸው:: ሁሉም በሚባል ደረጃ በቁጭት ተብሰለሰለ:: ሰማያት ጠቆሩ:: ምድሪቱም በግፍ ብዛት ተንቀጠቀጠች:: ሃዘን ብቻ ሆነ!!!
.
አዎ የጁንታው እቅድ ሰሜን እዝን በመውጋት የወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድል ማስመዝገብ ነበር:: ይህም በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ላይ የስነልቦና የበላይነት ለመቆናጠጥ ያለመ ነው:: ግን ህልማቸው በዚህ አያበቃም:: በመሃል አገር እና በየክልሉ ያዘጋጇቸው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች #መፈንቅለ መንግሥት እንዲያካሂዱ ዝግጅታቸውን ጨርሰው ነበር:: ለዚያ ማስፈጸሚያ የሚሆን በቂ የጦር መሳሪያ ተዘጋጅቶም ነበር:: አዲስ አበባ በሚገኙት በስዩም መስፍን ቤት እና በደብረፅዬን ሚስት ቤት የተያዙት በርካታ ኮንቲነሮች የዚሁ ዝግጅት ጥቂት ማሳያ ናቸው::
.
የሰሜን እዝን እንደወጉት ዓላማቸው በሁለት አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ መትመም ነበር:: አንደኛው በጎንደር በኩል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቆቦ ወልዲያ በኩል ወደ መሃል አገር ለመትመም ነበር:: በእነዚህ ከተሞች በቂ የሰው ኃይል አዘጋጅተው ነበር:: የከተማ እና የዞን አመራሮች ውስጥ ለዚሁ ዓላማ ያዘጋጇቸው ሰዎችም ነበሩ:: መሃል አገር እንደሚገቡም እርግጠኞች ነበሩ:: በዚያ ላይ በዚህ ሂደት ውስጥ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ እንድትናጥ በየክልሉ ያስቀመጧቸው የጥፋት ኃይሎች ነበሩ:: ይህም የነሱን ጉዞ እንደሚያሳልጥ ታምኖበታል::
.
ጁንታው ለዚህ ዓላማው በትግራይ ክልል በአጠቃላይ 6 ብርጌዶችን አዘጋጅቶ ነበር:: እነዚህ 6 ብርጌዶች ልዩ ሃይል እና ሚሊሻን ያካተተ ቢሆንም በሰራዊት ጥራት ግን ብዙም አይደለም:: የሰሜን እዝን ሲወጉ ከሰሜን እዝ የዘረፏቸውን ከባድ እና ዘመናዊ መሳሪያዎች ለነዚህ ብርጌዶች አከፋፍለው ነበር:: ሆኖም ከፍተኛ የእውቀት እና የክህሎት ችግር ታይቷል:: በዚያ ላይ ጀግናው የአየር ኃይላችን አብዛኞቹን በቆሙበት ነበር ወደ ተራ ብረትነት የቀየራቸው:: ድምፅ አልባ ድሮኖቹም መፈናፈኛ አስጥተዋቸው አብዛኞቹ ጥቅም ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል:: በዚህ ሰዓት ስድስቱም ብርጌዶች እንደ ብርጌድ ተደምስሰዋል:: አባላቶቻቸው በርካቶቹ ሞተዋል:: ገሚሶቹ ጠፍተዋል:: አብዛኞቹ ተማርከው ትጥቅ ፈትተዋል:: ገሚሱ ወደ እርሻው ተመልሷል:: ከባድ መሳሪያዎቹ ተቃጥለዋል::
.
(( ጁንታው ከባድ መሳሪያዎችን ተጠቅሞ ያጠቃው ቢኖር የራያን እና የእንደርታን ህዝብ ነው:: ጁንታው በራያ ጨርጨር በቢሶ በር እና ዙሪያውን የገደላቸውን ሰዎች እና ያቃጠላቸውን መንደሮች በዝርዝር ከፎቶ ማስረጃ ጋር ለማቅረብ ዝግጅቴን እየጨረስኩ ነው:: ))
.
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰሜን እዝን ጥቅምት 24/2013 ለመውጋት የጁንታው አመራሮች የወሰኑት ረቡዕ ጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ነበር:: ስብሰባውን የመራው እና ውሳኔውን ሲያስተጋባ የዋለው የትህነግ ስራ አስፈፃሚ አባልና የድርጅቱ ፅ/ቤት ኃላፊ አለም ገብረዋህድ ነበር:: “አሸንፈን ከመውጣት ውጭ አማራጭ የለንም” የሚል ዲስኩር ሲደሰኩር ውሏል:: ለማሸነፍ ደግሞ ሰሜን እዝን በተኛበት ማረድ እና መውጋት ቀዳሚ እርምጃ ተደርጎ በጁንታው አመራሮች ተወሰነ:: ከጥቅምት 4 በኃላ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ አመራር የሆኑ የጁንታው አባላት ፈቃድ እየጠየቁ ወደ መቀሌ እና ወደ ሽሬ መጏዝ ጀመሩ:: ከዚያም ኦሬንቴሽን ተቀበሉ:: ቀኑ በድብቅ ሲጠበቅ ሰነበተ:: ጥቅምት 24 ቀን ላይ የሰሜን እዝ አመራሮችን እና አባላትን በሰብል ስብሰባ ሲያደክሟቸው ዋሉ:: ማታ ላይ ሽልማትና እውቅና በሚል በውስኪ አደነዘዟቸው:: ለሊት ላይ ገብተው አረዷቸው::
.
እንግዲህ ይህ በታሪካችን የሌለ አሳፋሪው ግፍ ነው የኢትዮጵያን ሰማይ ያጠቆረው:: ይህ ግፍ ነው በተቀረው የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ብሶትን የወለደው:: ይህ የጭካኔ ግፍ ነው የአማራ ልዩ ኃይልን እና ሚሊሻን እንደ አንበሳ ያስገሳው:: ይህ አረመኔያዊ ግፍ ነው የአፋር ልዩ ኃይልን እና ሚሊሻን ያስጨከነው:: ይህ ግፍ ነው በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ተሰንቅሮ ሌት ተቀን አላስተኛ ያለው:: እውነት አነባች!!! ፍትህ ጨከነች!!!! በዚህም ሳቢያ የጁንታው መጨረሻ ምን እንደሆነ ብናገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆናል:: የውሻ ሞት በስንት ጠዓሙ!!! በዘራችሁ አይድረስ አለ ጀነራሉ?! ቱ! አበስኩ ገበርኩ!
.
አዎ! በመጨረሻ ፍትህ አሸነፈች!!!
ኢትዮጵያ አሸነፈች!!!
የጁንታው ብኩን አመራር እንክትክት ብሏል!!!
ጁንታውን ተስፋ የምታደርጉ ተስፋ ቁረጡ!!!! እርማችሁን አውጡ!!! በቃ ሌላ ነገር አይፈጠርም!!!!
ጁንታው አብቅቶለታል!!! ትህነግ እንደ ተቋም ፈርሷል!!! ህውሃት ተደመስሷል!!!! ከዚህ በኃላ ህወሃት ታሪክ ሆኗል!!! ሃቅ ነውና ተቀበሉት!!!! ባንዳዎች ጠፍተዋል!!! ኢትዮጵያ ግን ለዘላለም በክብር ትኖራለች!!! ክብርና ምስጋና ለጀግኖች ልጆቿ!!! ትልቁ ካንሰር ተወግዷል!!! ድሉ ጣፋጭ ነው!!! መጭው ዘመን ብሩህ ነው!!! ብሩህነቱ ቀጣይ እንዲሆን ግን የዛሬ መሪዎቻችን በተለይም ብልፅግና ፓርቲ ትምህርት ይውሰድ!!! ያለፈው ይበቃናል!!!! መልካም ዘመን ለሃገራችን እና ለህዝቦቿ እንሻለን!!! ልብ ይስጣችሁ!!! አሜን!!!