>

ፋሽዝም ሲከስም የኢትዮጵያ ትንሳዔ ይጀምራል...!!!   (በክርስቲያን ታደለ (የአብን አመራር)

ፋሽዝም ሲከስም የኢትዮጵያ ትንሳዔ ይጀምራል…!!!

          በክርስቲያን ታደለ (የአብን አመራር)

 

 
መተከል ኢትዮጵያ እንዳዲስ የምትወለድበት ምድር ይሆናል!
*****
ዛሬም የዘር ማጥራቱ ቀጥሏል።
 
ዛሬም የዘር ፍጅቱ ቀጥሏል።
 
ዛሬም ከዘር ፍጅቱ ይልቅ ዘር ፍጅቱ ይቁም ማለት ገዥዎችን ያስጨንቃል
ዛሬም በዘር ፍጅት ፈፃሚዎች ላይ ሳይሆን የዘር ፍጅት ይቁም በሚሉ ወገኖች ላይ ጣቶች ይቀሰራሉ።።(አርፋችሁ እለቁ መሆኑ ነው! )
ዛሬም ለመሬት ብለው የዘር ማጥራትና የዘር ፍጅት የሚፈጽሙት ሳይኮነኑ በንጹኃን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ይቁም የሚሉት በተስፋፊነት ይከሰሳሉ። (በሞታችንም ዓይናፋር ሊያደርጉን ይዳዳቸዋል! )
ዛሬም ለተበዳይ መወገን፤ የዘር ፍጅትን አምርሮ መቃወም ዘረኝነት ነው ይሉናል። (ሞት የተፈረደበት ነፍስ መሰል ነገር የሚገደው ይመስል! )
ዛሬም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ችግር መኖሩን ያሳወቀውን በጠላትነት መፈረጅ አለ። (ግም ሸተተኝ ብሎ አፍንጫን ለመቁረጥ መከጀል! )
ትናንት እንደዛሬዎቹ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያን ባልን አማሮች ላይ ግፍን ያደረጉ ሁሉ መጨረሻቸው አላማረም። የትንናቶቹም እንደዛሬዎቹ ስማስም ሲሰጡን ነበር። ሀ ብለው በደልን በጀመሩበት ወልቃይት፤ የግፍን ጥግ ባሳዩበት ወልቃይት ሞታቸውም በዚያው ሆነ። የዛሬዎቹም የግፍ ጉዞ በትናንቶቹ ጎዳና ነው። ይኼ ሁሉ ግን ያልፋል። ኢትዮጵያ በአባታችን ኢትኤል ግዮን ዳር ነው የተወጠነቺው። ታሪክ ራሱን ይደግምና፤ ኢትዮጵያችን በግዮን መውጫ መተከል ዳግም ትወለዳለች። ኢትዮጵያን ሲያተራምሱ የኖሩ የውጭ ጠላቶችም፤ ኢትዮጵያንም አማራንም ሲያርዱ የኖሩ ፋሽስቶች መተከል ላይ ፍፃሜያቸው ይሆናል። የውጪውም የአገር ውስጡም መንጋ በምኞቱና በመጎምዠቱ ጥልቅ ላይመለስ መተከል ላይ ይከስማል! ፍትኅ፣ እኩልነት፣ ነፃነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት፤ የሁሉም፥ በሁሉም የሆነቺዋ ኢትዮጵያችን እውን ትሆናለች።
Filed in: Amharic