>

ፀሃዩ መንግስት በርታ ዘጋቢውን ነው ማሳደድ - ገዳይማ ወገንህ ነው ¡¡¡¡¡ (መስከረም አበራ)

ፀሃዩ መንግስት በርታ ዘጋቢውን ነው ማሳደድ – ገዳይማ ወገንህ ነው ¡¡¡¡¡

መስከረም አበራ

* አስከሬን በአይሱዘ ተጭኖ የሚታሰርባት የጉድ አገር
የመተከል ኮማንድ ፖስት በዚህ ሰአት ስብሰባ ተቀምጧል። የስብሰባው አጀንዳ ገዳይ ቡድኑን እንዴት እንደምስሰው ሳይሆን ስራችንን አላሰራን ያለው #ያለለት_ወንድዬ ነው ስለሆነም በቁጥጥር ስር እናውለው የሚል ነው።
የመተከል ድምፆችን በማሳደድ ማሸነፍ አይቻልም፤ ዛሬ የመተከል ኮማንድ ፖስት ተሰብስቦ Yalelet Wondye ን ለማሰር ወስኗል። ከዚህ ቀደም ወንድማችን ምናልባት ይታያውን ከመተከል አሳደው ወደአማራ ክልል ቢመጣም የብአዴን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ” በማቀድና ሽብር በማሰናዳት” ወንጀል ከሶታል።
የሚገርመው የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ የመሠረተው ስልጣን ሳይኖረው ነው፤ በአዲሱ የፀረ ሽብር አዋጅ ከ 2012 ዓ.ም ወዲህ ሽብርተኝነት የሚመለከቱ ነገሮች የፌደራል መንግስቱ ስልጣን እንደሆነ ተደንግጓል። እነ ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ በችሎት ይሄንን ተቃውሞ ቢያነሱም በቀጠሮ እንደታለፈ ሰምቻለሁ::
 ታዲያ ልጁን በዚያ ወንጀል ለመጠርጠር የሚያበቃ ምክንያት ሳይኖርና ለመክሰስም የሚያስችል ስልጣን ሳይኖር የአብክመ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማንን ለማስደሰት ይሆን? በማንስ ትዕዛዝ ይሆን? መተከል ላይ ጡጫው ከውስጥ እስከውጭ የጠነከረው ለምን ይሆን??
በእኔ ግምት ብአዴን ወንድማችን ያለለትንም ወይ አሳልፎ ለኮማንድ ፖስቱ ይሰጠዋል አሊያም እነአብይን ለማስደሰት ያስረዋል። ከምንም በላይ በየቀኑ 300 አስከሬን በግሬደር እየተቀበረ ዝም ማለታችን ለአሳሪና ገዳዮች የልብ ልብ ይሰጣቸዋል።
*    *   *
ያለለት ወንድዬ በገጹ ይህን ምላሽ ሰጥቷል:-
 
ስራ ያላሰራኋችሁ …!!!
በምትፈልጉት ልክ የመተከልን አማራ ጨርሳችሁ ባለመጨፍጨፋችሁ እቅዳችሁን ስላስተጓጎልኩባችሁ?
የአማራን/የአገውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ፍንጭ እንዳይገኝ አድርጋችሁ የምትሰሩት መንግስታዊ ሸፍጥ ይፋ ስለወጣባችሁ?
የወገኖቻችን ደም ያፈሰሱ ህይወታቸውን የነጠቁ ነፍሰ በላ አረመኔዎችን ስላጋለጥኩባችሁ? አላሰራችሁ አልኩኝ?
በዛሬው እለት (ረቡእ) እንኳ
መተከል ድባጤ ጋሌሳ ከ80 በላይ አስከሬን   ከቡለን ወረዳ ዶዘር አስመጥታችሁ ካልቀበርን ብላችሁ  ከህዝቡ ጋር ግብግብ በመፈጠሩ  በአይሱዙ መኪና ላይ ጭናችሁ ፖሊስ ጣቢያ እንዳስገባችሁት እየታወቀ በድርጊቱ ከማፈር ይልቅ ለምን ህዝቡ ሰማብን በእናንተ ቋንቋ “ስራ አላሰራ አለን” ብላችሁ ታሳድዱናላችሁ።
እኔ ያለለት ወንድዬ 
ለታላቁ የአማራ ህዝብ  እስር ቀርቶ ሞት እንኳ ቢሆን እየተፍነከነኩ የድል አድራጊነት ሳቅ እየሳኩ የምሞትለት የአባቶቼ ልጅ መሆኔን ባለማወቃችሁ ነው የተበሳጨሁት።
Filed in: Amharic