>

ሱዳን ፕሬዚዳንቷ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ጄነራሏ ወደ ካይሮ ሩጫ ላይ ናቸው - ኢትዮጵያስ... ?!?(እስሌማን አባይ)

ሱዳን ፕሬዚዳንቷ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ጄነራሏ ወደ ካይሮ ሩጫ ላይ ናቸው – ኢትዮጵያስ… ?!?

እስሌማን አባይ

የሱዳኑ ሽግግር ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ ሰሞኑን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ UAE ነበሩ። ጉብኝቱ ይፋ ያልሆነ ነበር። ዛሬ የመመለሳቸው መረጃ ብቻ ነው በሱዳን ኒውስ በኩል የተዘገበው። በጦሩ አመራሮች ቡርሃንና ሔሜቲ ጫና የበረታባቸው ሐምዶክ የጦሩ አሻንጉሊት ሆነሃል የሚል ትችት ከዜጎች እየተሰነዘረባቸው ይገኛል። በአንፃሩ የአል ቡርሃን ጭፍሮች በጄነራል ከባሺ በተመራ ልዑክ ዛሬ ከግብፁ አልሲሲ ጋር በካይሮ መክረዋል፤ ዶልተዋል።
UAE በሱዳን የጦር ምክር ቤት ላይ የረዘመ እጅ አላት። ከኢትዮጵያ መንግስትም እስከ ወታደራዊ የደረሰ ድጋፏ እንዲሁ። ከኤርትራም ጋር በብዙው ይደጋገፋሉ። የሱዳኑን ጦር ምክር ቤት ከሚፃረሩት ደግሞ ቱርክ ትጠቀሳለች። UAE ደግሞ ከቱርክ ጋር የበረታ ቅራኔ አላት።
አል-ቡርሃን ጎቶት ወደ ውጊያ ከከተተን በወታደራዊ አቅም በተለይም በምድሩ ሳይሆን በሌሎች ጉዳዮች ላይ አፅንኦት ይመከራል..፤ የዲፕሎማሲ ስራ በአየር ለሚኖር የጀርባ ድጋፍና ሚዛን ወደተፈለገው ይሆን ዘንድ ሁነኛ ነው።  ግብፅ ሱዳንን ወደ ውጊያ ከመማገድ ያለፈ ድጋፍ ታደርጋለች ተብሎ አይጠበቅም። ለሊቢያው ሃፍታር አይዞህ ስትል ከርማ በመጨረሻ ጦሯ በሊቢያ ድንበር ቆሞ እንዲጠብቅ ብቻ ነበር ውሳኔዋ። ለዚህም የህዳሴ ግድቡ ጉዳይ በምክንያትነት መጠቀሱ አይዘነጋም።  በሜዲትራኒያን፣ በሊቢያና ቀይ ባህር ቱርክ አድፍጣባታለች። ሌሎች አገራትም ያነፈንፏታልና ለሱዳን የረባ ድጋፍ አይኖራትም ነው የሚባለው።
ኢሳያስ የሱዳንን እንቅስቃሴ ከመፃረር የግብፅን አምባሳደር እስከማሰናበት መጓዙ፣ ከ UAE እና ሳዑዲ ያለው የጂኦ-ፖለቲካ ጥምረት አንድምታም እዚጋ በታሳቢነት ይጠቀሳል።
በኢትዮጵያ ቀጠናዊ ደህንነት ላይ የገልፍ አገራት መዳፎችን ማኔጅ ማድረግ ቀዳሚ ትኩረት ማግኘት እንዳለበት የዘርፉ ጠበብት ምክረ ሐሳብ የሰነዘሩት ቀደም ካሉ አመታት ጀምሮ ነበር።
Filed in: Amharic