>
5:21 pm - Friday July 21, 0017

የመተከል እውነት ከውስጥ ሲፈረቀጥ...!!! ( ዝርዝር ሪፖርታዥ) መስቀሉ አየለ

የመተከል እውነት ከውስጥ ሲፈረቀጥ…!!!

( ዝርዝር ሪፖርታዥ)
መስቀሉ አየለ

ወያኔ መሃል ሸዋ ነግሶ በኖረባቸው ዓመታት እንደ ማንኛውም ተቃዋሚ ለቤንሻንጉል ህዝብ መብትና ነጻነት እታገላለሁ የሚል በአብዱለዓብ የሚመራ አንድ የነጻ አውጭ ግንባር ኤርትራ ውስጥ ነበር።
 በስልጠና ማገባደጃ ላይ የተለመደ የእግር ጉዞ ማድረግ የስልጠናው አካል በመሆኑ ከወያኔ ጋር በመመሳጠርና ያንን አሳቻ ሰዓት በመጠቀም ከ400 በላይ የሚሆኑ ወታደሮቹን ይዞ ሱዳን የገባው በ2009 ነበር። ድርጅቱ ባለፉት 5 አመታት ከህወሃት ከፍተኛ የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ  እየፈሰሰለት ያሰለጠናችውና ያስጣተቃቸው ጉምዙዎች ብዛት ከሃያ ሽህ በላይ መድረሳቸውን መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን እርምጃቸውን ይበልጥ አጠንክረው በመግፋት አሁን ደግሞ  ህወሃት  በፈጠራቸው እና ቤንሻንጉል ውስጥ ከፍተኛ ንብረት ባካበቱት “ሃብታሞች” የገዘብ ወጭ ጭምር የሚደጎም ኮንሰርቫቲቭ በሆነ ግምት ወደ አስራአምስት ሽህ የሚገመት ተጨማሪ ሃይል  በወንበራ፣ ድባጤ በረሃዎችና በአላጭስ ፓርክ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከአገር ውስጡ በተጨማሪ ጉባን ተሻግረው ሱዳን ውስጥ “ብሉ ናይል ስቴት” ብዛት ያላቸው ጉምዞች ከተቻለ ነጻ አገር ለመመስረት ካልሆነም ደግሞ ወደ ሱዳን ለመቀላቀል በሱዳን መንግስት ድጋፍ በገፍ እየሰለጠኑ መሆኑን ስንመለከት ችግሩ ጆኦፖለቲካል ወደ መሆን ደረጃ እየተሸጋገረ ለመሆኑ እንደማሳያ መውስውድ ይቻላል።
መተከል ላይ የኦነግን አሰላለፍ በተመለከተ ደግሞ ኦሮሚያ ከመተከል በምትዋሰንበት በካማሽ ዞን ላይ 22 ሽህ የሚደርስ ጦር ከማስፈር አልፎ ዛሬ ኦነግ መተከል ውስጥ ስምንት ቀበሌዎችን በቁጥጥር አድርጎ በራሱ መዋቅር እያስተዳደረ ሲሆን ከአስር ቀናት በፊት ብቻ 4 ሽህ የጉምዝ ጦር ኦነግን ለመርዳት ከካማሽ ተነስቶ ወደ መተከል ገብቷል። በሌላ በኩል ይህንን ሁሉ ከበባና ሁካታ “እከላከላለሁ” ብሎ የገባው የመከላከያ ሃይል ከላይ ተጠሪነቱ ለጠሚሩ ቢሆንም ኮማንድ ፖስቱን የሚመራው አለሙ ሰሜ የተባለ ኦህዴድ እንዲሁም ጌታሁን አብዲሳ የተባለውን የቤንሻንጉል ጉምዝ ምክትል አስተዳዳሪን ጨምሮ ወታደራዊ ኮማንዱ ላይ በየደረጃው የተመደቡት ጀነራሎች  አፍቃሬ ኦነግ ኦሮሞ መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አንዱ መገለጫ ከሙትና ቁስለኛ የተረፈ እና በየግዜው እየተመናመነ ያለ ነገር ግን የጠነከረ ወታደራዊ እርምጃ እንዳይወስድ በቢሮክራሲያዊ እዝ ሰንሰለት የታሰረው አንድ ክፍለጦር የማይሞላ ሃይል አይኑ እያየ ንጹሃን በየቦታው ሲታረዱ ይውላሉ፤ያድራሉ። ነገር ግን ምንም አያደርግም። በሌላ በኩል ግን በተቃራኒው ገና ለገና “የአማራ ልዩ ሃይል ይገባል” በሚል ምክንያት አለሙ ሰሜ የሚያዝበት ኮማንድ ፖስት መሃሉን ለአራጆች አስረክቦ የመተከልና የአማራ ክልል ድንበር ላይ ገዥ መሬት ይዞና ከባድ መሳሪያ ጠምዶ ከአማራ ልዩ ሃይል ጋር ፊት ለፊት ተፋጦ መገኘቱ ነው መራሩ እውነት።
ከ200 አመታት በላይ ለሆነግዜ በኦቶማን ቱርክ፣ ራሺያና ምእራባውያን መካከል ቁልፍ የውጥረት ማእከል ሆና የኖረችው ክሬሚያን ስታሊን በሞተ በዓመቱ አልጋ ወራሹ ክሩስቸቭ የልደት ቀኑን አስመልክቶ ለዩክሬናውያን በስጦታ መልክ ነበር ያበረከተላቸው። ዘመን ተቀይሮ የሶቪየት ሕብረት ሲፈራርስ ደግሞ ክሬሚያ በዩክሬን እጅ ባለችበት ሁኔታ በሂደት የዩክሬን ተመልሳ አፍቃሬ ናዚ በሆኑት የባንዶቹ የልጅ ልጆች እጅ መውደቋ ለራሺያ የባህር ሃይል የደምስሩን የመዘጋት ያህል በመሆኑ ጉዳዩ ቀላል አልነበረም።
እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ቁልፍ ነጥብ ያ ወቅት ማለት ራሽያ ያዘጋጀችው የሶሽ ኦሎምፒክ የሚካሄድበት ወቅት ሲሆን ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም ወዲህ “በዘመናዊት ዩሮፕ ውስጥ አንድ አገር ሌላኛዋን በመውርውር የድንበር ማስፋፋት ልታደርግ አትችልም” የሚል አጉል ፍልስፍና ላይ ወድቀው በተጻራሪው በሶሽ ኦሎምፒክ ላይ ድርሽ እንዳይሉ ስለታገዱባቸው በሞራል የላሸቁ ሶዶማውያን መብት ቀን ከሌት በመጮሕ ላይ አተኩረዋል። በሌላ በኩል በሶሽ ኦሎምፒክ የክብር እንግዳ ሆኖ የተገኘው ፑቲን ሁለት አማካሪዎቹን ጠርቶ “ማእቀብ ቢጣልብን ያለን የወርቅ ክምችት ምን ያህል አስተማማኝ ነው?” የሚል አጭር ጥያቄ ይጠይቃል። መልሳቸው ጤናማ ነበር። በዚያው ቅጽበት ፑቲን በሰጠው ቀጭን ትእዛዝ የኑክሌር ሮኬቱን ጠምዶ ክሬሚያን ሰለቀጣት። ይህን ኩነት አስመልክቶ አንድ አሜሪካዊ ጀነራል በሰራው አንድ መቶ አምሳ ገጽ ዝርዝር ሪፖርት ላይ በቁጭት እንዳስፈረው “ምራባውያን የፖለቲካ መሪዎች በሊበራል አይዲዮሎጅ የደነዘዙ ነፈዞች ሲሆኑ ፑቲን ደግሞ ማንም ሰው ማሰብ ከሚችለው በላይ ሪያሊስቲክ መሪ ነው” ነበር ያለው። በእኛም አገር ወቅታዊ ጉዳይ ውስጥ ብቸኛውም ባይሆን አንዱ ችግር የልሂቃኑ፣ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮችና በእራሱ በመንግስት መዋቅር ዋጥ ያሉ ሰዎች በዚሁ በነፈሰበት የሊበራል አይዲዮሎጅ መንሳፈዛቸውና መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ቀርቶ ብብታቸው ስር የሚንተከተከውን አደጋ ማሸትት አለመቻላቸው ዛሬ ከመተከል እስከ ሱዳን የተዘረጋውን እምቅ አደጋ አሻግረው እንዳያዩ አድርጓቸዋል። መሬት የረገጠ ሪያሊስቲክ አመራር በቶሎ ካልተፈጠረ ሁኔታው ከሱዳን ወረራ ጋር ተቀናጅቶ በጥቂት ግዜያት ውስጥ ሚሊዮኖች የሚያልቁበትና የሚፈናቀሉበት የሞት ሸለቆ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው።
በተጨማሪ የአማራውን ክልል በተመለከተ ክልሉ ዛሬም ድረስ ከአሸክርነት ስነልቦና ወጥተው እራሳቸውን ችለው መቆም በማይችሉ አራተኛ ደረጃ(4th rate)ካዴሬዎች እጅ ታንቆ የተያዘ በመሆኑ ከጅምሩ መተከልም እንደ ወልቃይትና ራያ ወደጥንተ ርስቱ መመለስ ሲገባው በዝምታ መታለፉ አልበቃ ብሎ ጭራሽ ሰባ በመቶ የሚሆነው ነዋሪ አማራና አገው በሆኑበት ሁኔታ አዴፓ ነገሩን የውክልና ጉዳይ አድርጎ መውስውዱ መፍትሔውን አርቆ ሰቅሎታል።
ስለዚህ ከማንም በላይ ህዝባዊ ሃላፊነቱን የተረከበው  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእርግጥም  ዛሬን መሻገር ከፈለገ ከገባበት ፋንታሲ ወጥቶ አይኑን ለእውነት በመግለጥ መተከል ላይ እስከ ጥፍሩ የተነከረው መርገምት ላይ እርምጃ ለመውስድ እንዲያስችለው ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ በየደረጃው አንጥሮ በማውጣም ይሁን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ወደ መተከል እንዲገባ ፈቃድ በመስጠት አስቸኴይ እርምጃ ወስዶ  ንጹህንን እንዲታደግ ታሪካዊ ሃላፊነት ቀርቦለታል።
እንደ ማሳሰቢያ;
እባካችሁ የወንድማችንን ብዙአየሁ ካሴን የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ዳር እእናድርስ
Bizuayehu Mekonnen Kassie
የኢትያጵያንግድባንክ
Acc.No=1000 26800 6498
የብዙአየሁን የእጅ ስልክ ለምትፈልጉ
(0904573895)
Filed in: Amharic