>

የካይሮ  ወርቅ  ማውጫ  በቤኒሻንጉል... ወርቁን ይዝቃል.... ግድቡን ይሰልላል....!!! (እስሌማን አባይ)

የካይሮ  ወርቅ  ማውጫ  በቤኒሻንጉል… ወርቁን ይዝቃል…. ግድቡን ይሰልላል….!!!

(እስሌማን አባይ)

ካይሮም በቤንሻንጉል ያስቀመጠችው የወርቅ አምራች ቡድን:-
➺ህዳሴን በቅርብ እርቀት ይሰልላል
➺መረጃ ይሰጣል
➺ባለው ሀብት ገዳዮችን በመግዛትና በማደራጀት አካባቢውን ረፍት ለመንሳት እና ካይሮ በምትፈልገው ፎርማት ለማመቻቸት እድሉን ያገኛል።
* ካይሮ በቤንሻንጉል ግዙፍ የወርቅ ማውጫ እንዳላት አላውቅም ነበር።አሁን ግን ነገሩ ሁሉ ግልፅ ሁኖልኛል።
ሱር ኮንስትራክሽን መንገድ ስራን እንደ ሽፋን እየተጠቀመ መሳሪያ እያስታጠቀ፣ገዳዮችን ከቦታ ቦታ እያዘዋወረ የሚፈለጉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ሲስገድልና ሲያሳፍን  መቆየቱን በመጨረሻው የወልቃይት ሁመራ ኦፕሬሽን መንግስትም አምኗል ከመሸ ቢሆንም።የጎንደር ህዝብ ግን ሱር ምን እየሰራ እንደሆነ ቀድሞም ያውቅ ነበር።
በኢትዮጵያ ታሪክ ከተገኘው ሁሉ የላቀ የወርቅ ክምችት በግብፁ ኩባንያ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የመገኘቱ ዜና 6 ዓመት ሆኖታል። አስኮም ማይንኒግ የኩባንያው መጠሪያ ነው።
በወቅቱ የማዕድን ሚኒስትር የነበሩት አቶ ቶሎሳ ሻጊ ለሪፖርተር ጋዜጣ  “አስኮም ያገኘው የወርቅ ክምችት እስከዛሬ ከተገኙ ክምችቶች ሁሉ የላቀ ነው” ብለው ነበር።
አስኮም በቤኒሻንጉል ያገኘው ወርቅ አለማቀፍ መነጋገሪያ ነበር። ይሁንና ምኒስትሩ የግብፁ ኩባንያ ያገኘው የወርቅ ክምችት መጠን ምን ያህል እንደሆነ በአኃዝ ከመግለጽ ተቆጥበው እንደነበር ይታወሳል፡፡
‹‹እስከዛሬ ስናወራ የነበረው ስለ 30 እና 40 ቶን የወርቅ ግኝት ነበር፡፡ አስኮም ያገኘው ከዚያ በእጅጉ የሚበልጥ ነው፤›› ብቻ ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
የግብፁ ኩባንያ ወርቁን ባገኘ ከሁለት አመት በኋላ ደግሞ የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች ለወርቅ ልማት በቤኒሻንጉል መስፈራቸው ተዘግቦ ነበር።
ኢሳት በመስከረም 9፥ 2009 ዘገባው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጊዛን ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ የህወሃት ወታደራዊ አመራሮችና አባላት በአካባቢው ለወርቅ ልማት በሚል መስፍራቸው በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ በመቀስቀሱ 300 የሚጠጉ ሰዎች ወደ አሶሳ እስር ቤት ተወስደዋል ብሎ ነበር። ድርጊቱን ከተቃወሙት ውስጥም ከ10-20 የሚሆኑት መሞታቸውንና የህወሃት ባለስልጣናት አንድ ኮሎኔል ጦር ይህንኑ ድርጊት ለመቆጣጠር በስፍራው እንዲሰማራ ማድረጉን ኢሳት ዘግቦት ነበር።
ከቤኒሻንጉል እስከ መተከል የተስፋፋው ወንጀለኛ ሃይል በአብዛኛው በብሔር አንዳንድ ጊዜም መቱን የፈፀመው ዘግናኝ ግድያ አልተገታም። አካባቢው የህዳሴ ግድቡ መገኛ ነው። ሲቀጥልም ወርቅ ያውም በከፍተኛ መጠን የተገኘበት አካባቢ ነው። በእንቅርት ላይ ደግሞ የካይሮው አስኮም ኩባንያ ወርቃማው መሬት ላይ ተተክሏል። ሱዳንም የቤኒሻንጉልን ስም የኔ ነበር በማለት በፍቅር ስታዜም እየሰማናት ነው።
አስኮም ማይኒንግ አሁንም አለ?
ባሳለፍነው ጥቅምት የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉምዝ የሚገኙ ማዕድን ፈላጊ ኩባንያዎችን ጎብኝቷል። በወቅቱ ከተጎበኙት ኩባንያዎች ውስጥ አስኮም ማይኒንግ አንዱ ነው የሚል ዘገባ ተከታትለን ነበር። ዘገባው ግን “የግብፁ” የሚል መረጃ ባያካትትም።
Filed in: Amharic