>

ከሁለት የተከፈሉት የኦነግ ጽንፈኞች...!!! (ተመስገን ሚካኤል)

ከሁለት የተከፈሉት የኦነግ ጽንፈኞች…!!!

ተመስገን ሚካኤል

ኦነግ ባለፉት 40 ዓመታት ኦሮሚያን ለመገንጠል ሲታገል ኖሯል፡፡ በዚህም አብዘሃኛው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የኦነግ አስተሳሰብ በአጭሩ ካልተቋጨ አገር የሚያፈርስ ነው፤ በማለት ሃሳባቸውን ሲገልጡ ኖረዋል፡፡
አሁን ከለውጡ በኋላ ኦነግ ለሁለት ተከፍሏል፡፡ የመጀመሪያው በምዕራብ ኦሮሚያ በጃል መሮ የሚመራው እና ሽምቅ ውጊያ ከፍቶ ኦሮሚያን ለመገንጠል የሚታገለው የ40 ዓመት እቅዱን እውን ለማድረግ የሚታገለው አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ይሄንኑ አስተሳሰብ ዘመናዊ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው እና በሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የኦነግ ክንፍ ነው፡፡
የሁለተናው እና በኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራው ኦነግ ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ መገንጠልን አይቀበልም፡፡
ነገር ግን አማራ የሚባለውን ብሄር በማጥፋት ኢትዮጵያን ኦሮሚያን /ኦሮሙማ/ኦሮማይዝ/ የማድረግ አላማን ይዞ የሚንቀሳቀስ ስሆን አማራን ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ኦሮሚያን ከመገንጠል ለኦሮሚያ የተሻለ ነው፤ ብለው ያምናሉ፡፡
የአብይ (ሽመልስ) አማራውን የማፅዳት ፕሮጀክት ውጤት ይኼው ነው። ብልፅግና ማለት የኢጣሊያን፥ የወያኔና የኦነግ ፀረ-አማራ ፖሊሲ የካርቦን ግልባጭ ድርጅት ነው። አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ ከ5 ሺህ በላይ አማሮች በማንነታቸው ተጨፍጭፈዋል። ሰውየው አፉ ቅቤ፥ልቡ ጩቤ የሆነ ሰው ነው።
 አማራን ለማጥፋት ተልዕኮ ይዞ፤ የበግ ለምድ ለብሶ የመጣ ተኩላ ነው የሚመስለኝ። ትናንት በህወሓት ሲያመካኝ ነበረ ዛሬ በማን ሊያሳብብ ይችላል?  የመከላከያ አዛዥ፣ የአየር ኃይል አዛዥ፣ የፖሊስ አዛዥ፣ እንዳለ ከላይኛው መዋቅር እስከ ታችኛው እርከን በኦሮሞዎች ተይዟል፥ ጥቃቱ ግን አልቆመም፥ እንዲያውም ከወያኔ ዘመን በባሰ ሁኔታ በአብይ (ሽመልስ) መንግሥት ስፖንሰርነት አማራዎችን እያሸማቀቁ ማሰደድ፤ እያረዱ ማጥፋት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ በጅምላ ተጨፍጭፈው  በዶዘር የተቀበሩት አማሮች ብቻ ናቸው።
ይሄ ጄኖሳይፍ በአብይና መንግስታቸው ጭምር እውቅና አግኝቶ እየተሰራበት ያለ ነው፡፡
ከትህነግ በእጥፍ በአማራ ጥላቻ ያበደው ይህ ቡድን አማራን ከመግደል እና ከማፈናቀል አልፎ አማርኛ ስሞችንም መጠየፍ እና ማጥፋት አንዱ ስትራቴጂው ነው፡፡
ትህነግ የፓርቲ ስሟን /ህወሃት/TPLF/ በማለት ስትጠራ የነበረው ትህነግ የሚለው የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር ተብሎ በአማረኛ ስም ላለመጠራት ነበር፡፡
አሁን ደግሞ የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአማርኛ ርዕሰ መስተዳድር ተብሎ ላለመጠራት ፕሬዝዳንት ብለው እንድጽሁ ለአዲስ ዘመን caption editor ሳይቀር ተግባራዊ እንዲሆን ትዛዝ ሰጥጠዋል፡፡ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳርሮች ለገና በዓል ርዕሰ መስተዳድር ተብለው በአማርኛ ስጠሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፕሬዝዳንት ተብለዋል፡፡
ጥላቻቸው እስከዚህ ዘልቆ ወጥቷል፡፡ እያንዳንዷን ጥቃቅን ነገሮች ሳይቀሩ በኦሮሙያ አስተሳሰብ እንድዋጥ እያደረጉ ነው፡፡
Filed in: Amharic