>

ሙታንስ ሙታንን ይቀበሩ ዘንድ ተዋቸው...!!! ( መስቀሉ አየለ ዘብሔረ ደሴ)

ሙታንስ ሙታንን ይቀበሩ ዘንድ ተዋቸው…!!!

( መስቀሉ አየለ ዘብሔረ ደሴ)

በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት እንዳለፉበትና እንደሚኖሩበት ነባራዊ ሁኔታ የማህበረሰብ ግንባታ ስትራቴጅ ይኖራቸዋል።ያ ማለት ግን በጥቅሉ እንደው ድምጹ የማይሰማ፣ ኮሽ የማይል እንደ ድመት ጸጉር የለሰለሰ ዜጋ ቀርጾ ለማውጣት ይሰራሉ ማለት አይደለም።ነገር ግን ሃላፊነት የሚሰማው፣ በታሪኩ የሚኮራ፣ “ጨዋ” ለመባል ሲባል ብቻ ጥቃትና ውርደትን “አሜን” ብሎ እንደ ኒሻን አጎንብሶ የማይቀበል፣ ከምንም በላይ በአገሩ ህልውና እና በማንነቱ የማይደራደር እና ለዚህም እስከ ሲዖል ዳርቻ ከመሄድ የማይመለስ ቆፋጣና ትውልድ ቢኖራቸው አዋጭ መሆኑን አይስቱትም። ታሪክ በደማቁ አስምሮት እንዳለፈው የማህበረሰባቸው የውሃ ልክ በመሆን ክፉ ቀን ሲመጣና ድቅድቅ ጨለማው ሲያጠላ በሰው ልጆች ህልውና ላይ የተቃጣውን ጥፋት በመቀልበስ እረገድ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚን አከርካሪ ሰብሮና ድፍን አውሮፓን ሳይቀር ከናዚዝምና ከፋሽዝም የደታደገው የቀዩጦር መሪ ፊልድ ማርሻል ዙኮቭ አይነት የጦር መሪን አለማችን አይታለች። የታሪክ ጸሃፊዎች ይህንን የወንድ ቁና “እንደ ተራራ በገዘፈ ማእበል ላይ ተረጋግቶ የሚራመድ”  ሲሉ ይገልጹታል።
ወደ አገራችን ስንመጣ እረጅሙ ታሪካችን የጦርነት ታሪክ የመሆኑን ያህል በዚያው ልክ ደግሞ “ጀግና በክፉ ቀን ይወለዳል” እንዲሉ በየዘመኑ ድንበር እየተሻገረ የመጣውን ጠላት ሁሉ አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ ብሔራዊ ክብራችንን ያስመለሱ እልፍ አእላፍ ወትእልፊተ ምልፊት ጀግኖች ለሶስት ሽህ አመታት እንደ አባይ ወንዝ ሲፈሱባት ኖረዋል።
በዚያው ልክ ደግሞ ከደገኛው ታሪካችን ጋር የተጣሉ የባንዳዎቹ የልጅ ልጆች በታሪክ አጋጣሚ መሃሉን ለመያዝ በቻሉበት ባለፉት 3 አስርተዓመታት ህዝባችን ለዘመናት ያዳበረውን የአቸናፊነት ስነልቦና ከተቻለ ለእራሳቸው ለመውሰድ ካልሆነም ድግሞ ለመስበር ሲሉ በፖሊሲ ደረጃ ሳይቀር ቀርጸው ተግባራዊ ለማድረግ ያልሞከሩት ነገር አልነበረም። ለዚህም ማእከላዊ የተባለው ቤተሙከራ አንዱ ምስክር ነው። ለምሳሌ አፉን በቅጡ ያልፈታ አጋዚ ማእከላዊ ውስጥ ሲያገኝህ መጀመሪያ የሚጠይቅህ ዘርህን ነው። “ስምህ ማነው?” ይለሃል። ምናልባት ደመላሽ፣ ግዛቸው፣ ድፋባቸው ምናምን ካልከው አይንህ እያየ ፊቱ ሲቀያየር ታየዋለህ፤ ከዚያም ትንፋሹን ሰብሰብ አድርጎ ቀበቶውን ማጠባበቅ ይጀምራል። “አሃ፤ አማራ ነህ ማለት ነው!” ይለሃል። ያንተን መልስ አይጠብቅም። ይዘምትብሃል አይገልጸውም፤ ጨካኝነት አውሬነት እንጅ ጀግንነት ማለት እንዳልሆነ ያልተረዳው አጋዚው ገሃነምን ጨልፎ እስር ቤቱ ድረስ ይዞልህ ይመጣል። በዚህ ሁሉ ማቃሰት መሃል በጆሮህ ውስጥ የሚልክልህ መልእክት አለ። “ስማ!” ይልሃል፤ “ህወሃትን መግፋት ተራራ እንደ መግፋት ነው” ይልሃል። “አንተ ብሎ የጀግና ዘር፤ ገና ቀሚስ አልብሰን ዘር ማንዘርህን ሁሉ የወጥ ቤታችን ሰራተኛችን ነው የምናደርጋችሁ” ይልሃል። ሲፈቅድ ደግሞ በውድቅት ሌሊት ሰናይት መብራቱን ጢምቢላዋ እስኪዞር ድረስ አረቂ ግቶ ያመጣና አንተን መሬት ላይ አንጋሎ አፍህ ውስጥ ሽንቷን እንድትሽናብህ ያደርጋል።
ይህ እንግዲህ የአንድ መርማሪ ተብዬ ብልግና ሳይሆን ህወሃት እራሱን “ጀግና” ሌላውን “ፈሪ” ለማድረግ በእስትራቴጅ ደረጃ ሲጠቀምበት የቆየው የዘመቻው አካል ነው። ህወሃት ደግሞ ይህንን የሚያደርገው ከሜዳ ተነስቶ አይደለም። የዚህች አገር የማእዘን ድንጋይ በሆነው የገጠሩ የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ ጀግንነት እንዴት እንደሚሰፈር በአሻጋሪም ቢሆን ስላየ ነው። ጥቃትን የሚቀበል የመንፈስ ልምሻ ያየዘው ሰው ሲፈጠር እቤቱ ድረስ የሴት ቀሚስ እንደሚላክለት፤ “ከማጀት ቁጭ ብለህ ጥጥህን ፍተል” እንደሚባል  ስለሚያውቅ ነው።
በመሆኑም ግዜውን ጠብቆ የወልቃይት አብዮት በ2008 ሲፈነዳ የደባርቅ ገበሬ የማረካቸውን የአጋዚ ወታደሮች ቀሚስና የሴት ኮንጎ ጫማ እያለበሰ እንዴት አንበርክኮ እንደ ገደላቸው እነ አባይ ወልዱ ጥንቅቅ አድርገው  የሰሙ ቀን “ተራርውን ያንቀጠቀጥኩት እኔ ነኝ” ከሚል እንቶ ፈንቶ ትርክት እስከ ማእከላዊ ድረስ የዘለቀው የነፍጠኛውን የአቸናፊነት ስነልቦና የመስበሩ አብዮት ገና ሳይወለድ እንደ ጨነገፈ ውስጣቸው አውቆታል።ከዚያ በኌላማ የተኴረፉት ሁሉ ተጠራርተው ከሰዬ አብርሃ እስከ ሞንጆሪኖ፣ ከደብረ ጽዮን እስከ ጻድቃን ገብረተንሳይ  “ጦርነት ማለት የትግራይ ህዝብ የሚያፏጭበት አርሞሪካው” እንደሆነ ሊነግሩን የሞከሩ ቢሆንም መሬት ላይ የቀረውን እውነት ግን በፍጻሜው ጦርነት ላይ ታይቷል።
ሰሞኑን የተለቀቁት የህወሃት ዞምቢዎች የአስከሬን ፎቶግራፍ ላይ እንደታየው እነ አይተ ስዩም መስፍን
ጠመንጃ ሳይሆን ከዘራ ይዘው፣
የወንድ ቀበቶ ታጥቀው ሳይሆን ጠጅ ቤት ውስጥ ያመሸ ደላላ አለባበስ ለብሰው፣
የእግር ኮቴያቸው እንዳይሰማባቸው ጫማቸውን አውልቀው፣  በባዶ ካልሲ እንደ ሽኮኮ እንደ ተጨበጡ ግንባራቸው ላይ ጥይት  ሲቆጠርባቸው ከፊሎቹ  ደግሞ ከተደበቁበት የጅብ ጎሬ ውስጥ እንደ ህጻን ልጅ በአንሶላ ጭምር እየታዘሉ ሲወርዱና እጃቸውን ሰጥተው ቀሪ ዘመናቸውን ደግሞ ስንቱን ባኮላሹበት እስርቤት ቤት ውስጥ ገብተው “ማምሻም እድሜ ነው” ለማለት እንዳላመነቱ ነው ያየነው። በትንቢተ ሆሴዕ እንደተነገረው “እግዚአብሔር ለምን ይታገሳል?” ቢባል “መጨረሻ የሚያደርገውን ስለሚያውቅ ነው” ተብሎ ተጽፏል።  በዚህ አጋጣሚ አልሞ ተኳሹና ብድር መላሹ ማን እንደነበር ለተወዛገቡ ወገኖቻችን አስከሬኖቹ አጠገብ የቆመውን የነፍጠኛ ዩኒፎም ማየት ነው። የአማራ ልዩ ሃይል ይባላል።
እዚህ ላይ የግድ ሳንጠቅሰው ማለፍ የሌለብን  አሳፋሪ የታሪክ ምእራፍ ቢኖር ስብሃት ነጋና ኩባንያው በዚህ እድሜው ዳግም ወደ በረሃ ወርዶ ዋሻ ውስጥ ሲቀመጥ ብዙዎች እንደሚያስቡት በሃያና ሰላሳ ወታደሮች ታጅቦ አልነበረም። ነገር ግን  እንደ ሮቦት ጠፍጥፎ በዘረኛ አይዲዮሎጅ ያጠመቃቸውና እንደ ፊኛ በከንቱ ውዳሴ የወጠራቸውን አስር ሽህ (10,000) ያህል ዲንጋይ ራሶችን ይዞ ከወረደ ቦሃላ ለቀናት ያህል በተደረገው ከበባ በሃሽሽ ናላቸውን አዙሮ ሁሉንም በሚባል ደረጃ ካስፈጀ በኋላ በመጨረሻም ግን ዳግሞ ህይወት ሊዘራ የጨረጨሱ ዘመዶችን ብቻ ይዞ በወጣቶቹ አስከሬን ላይ ተረማምዶ እጁን ለመስጠት ሲስማማ እሱን ብለው ዋጋ ስለከፈሉት አስር ሽህ ወጣቶች ህይወት ቅም ያለው ነገር አልነበረም።
 ከዚህ በተረፈ ግን እነ አባይ ጸሃየም ቢሆኑ እሳት ውስጥ እንደ ገባ ላስቲክ ተኮራምተው የተገደሉ፣ በላይ ዘለቀን፣ መይሳውን፣ አበበ አረጋይን፣ አበራ ጎባውን፣ መልኬ ጎቤን ወዘተ ለመሆን እንደተመኙ ከጀግንነት አጠገብ ሳይደርሱ የመከኑትን ስልባቦቶች እንደው ልክ ተራራ ላይ እየተንጎማለሉ መትረጌስ ሲተኩሱ የሞቱ ይመስል “ምንም ይሁን ምን ላመኑበት አላማ እስከ መጨረሻው ድረስ ተዋግተዋል” የሚለው የወያኔ ፍርስራሾች  የሰሞኑ ልፍለፋ አሁንም “ያለእኛ ጀግና ማነው?!”  የሚለው ያለፈው ዘመን የጨነገፈ ትርክት ቅጥያ ነው።  ለማንኛውም የአቸናፊነት ስነልቦናውን ከነፍጠኛው የመንጠቁ አብዮት በውርደት ተጠናቆ ምእራፉን ዘግትን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል። አገርን የመታደጉ ሂደት ግን በሌላ መልኩ ይቀጥላል። የሰሜኑን በምስራቅ።
Filed in: Amharic