>

በኢትዮጵያ ተቃዉሞ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠዉ  የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት ያዘጋጀዉ አለም አቀፍ ዉይይት...!!!

በኢትዮጵያ ተቃዉሞ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠዉ  የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት ባዘጋጀዉ አለም አቀፍ ዉይይት…!!!
ሸንቁጥ አየለ
 
እስክንድ ነጋ በፕሬዝዳንትነት :  እንዲሁም ማሙሸት አማረ  በም/ፕሬዝዳነት የሚመሩት የመኢአድ ባልደራስ  ቅንጅት በኢትዮጵያ ተቃዉሞ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠ እንቅስቃሴ ያለዉ ነዉ:: ለሞራል የበላይነቱም ሁነኛ ምክንያቶች አሉ:-
1ኛ. ለሰላሳ አመታት  ለኢትዮያ ዲሞክራሲ ፍትህ እና ለዜጎች እኩልነት አንድም ቀን ግንባሩን ሳያጥፍ የታገለዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት -መኢአድን ያካተተዉ የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት ከመሃል አዲስ አበባ እስከ መላዉ ኢትዮጵያ ጠረፎች ኢትዮጵያዉያንን በጋራ የማንቀሳቀስ መሰረትም  ያለዉ ነዉ:: ከመህድ እስከ መኢአድ: ከመኢአድ እስከ ቅንጅት የዘለቀዉን የዲሞክራሲ የእኩልነት: የፍትህ እና የአንድነት ጥያቄ አንግቦ በዘረኞች እና በአምባ ገነኖች ፊት የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ ነዉና ኢትዮጵያዊ ሁሉ እኩል ፍትህ ዲሞክራሲ ነጻነት ብልጽግና ይገባዋል ብሎ ለሰላሳ አመታት ዘረኝነትን:አምባገነንነትን: ጸረ ኢትዮጵያዊነትን የታገል ታላቅ የህዝብ ድርጅት የሆነዉ መኢአድ ፍትህ እና ዲሞክራሲ በተጠሙ ኢትዮጵያዉያን አይን ሁሉ በታላቅ አክብሮት የሚታይ ድርጅት ነዉ:: መኢአድ ከፕሮፌሰር አስራት እስከ ኢ/ር ሀይሉ ሻዉል የደከሙበት ዜጎች በነገዳቸዉ የማይገፉበት ስርዓት: እኩልነት: ፍትህ : ዲሞክራሲ: ነጻነት : ብልጽግና እዉን ሳይሆን ከቶም እንቅልፍ አይወስደንም ሲሉ የተማማሉ እና አሁንም በጽናት የቆሙ ጀግኖች ድርጅት የተሰባሰቡበት ነዉ::
2ኛ. የመሪዉ የባልደራስ መስራች እስክንድር ነጋ ጽኑ ተክለ ሰብዕና  ብሎም መስዋዕትነት ለመክፈል ያለዉ ወደኋላ የማይል ቁርጠኝነት ሌላዉ የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅትን በኢትዮጵያ ተቃዉሞ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠ እንዲሆን መሰረት ሰጥቶታል::ምንም እንኳን ዘረኛዉ የኦነግ/ኦህዴድ መንግስት የ እስክንድር አለማቀፋዊ ቅቡልነት እና የገዘፈ ተክለ ሰብዕና እረፍት ነስቶስ እስክንድርን ወደ እስር ቤት ቢያስገባዉም የእስክንድር ህዝባዊ ቅቡልነት ከቀን ቀን እየጨመረ መጣ እንጂ ከቶም ዘረኖች እንዳሰቡት ትግሉን ማሰር አልቻሉም:: ሌላዉ ባልደራስ አንግቦት የተነሳዉ አላማም የዚህ እንቅስቃሴ መሰረታዊ የሞራል የበላይነቱ መገለጫ ነዉ:: የኢትዮጵያዉያን ሁሉ መናህሪያ ዋና ከተማ የሆነችዉ አዲስ አበባ የኢትዮጵያዉያን አጽመ ርስት እንጂ ኦነግ/ኦህዴድ እንደሚለዉ የአንድ ነገድ ሀብት አይደለችም ብሎ በግልጽ በፕሮግራሙ ማስቀመጡ ለዘረኛዉ እና የነገድ ፖለቲካ አራማጁ ኦህዴድ/ኦነግ የእግር እሳት የጫረበት ጉዳይ ነዉ::
3ኛ.በአሁኑ ኢትዮጵያ የገባችበት መዉጫ ቀዳዳ ያጣዉ የአክራሪ የነገድ ፖለቲካ ስንኩል ህሳቤ ሀገሪቷን ሊያፈርሳት በሚንጥበት ወቅት የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት ለኢትዮጵያዉያን ተስፋ የሚሆን ራዕይን ያነገበ እንቅስቃሴ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ራዕይም  ታምኖ የቆመ ስብስብ መሆኑ የመኢአድ-ባልደራስን ቅንጅት የሞራል የበላይነት ያስረግጥለታል::መኢአድ-ባልደራስ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ ነዉ:ኢትዮጵያም አንዲት ሀገር ነች ዳር ድንበሯም ከቶም መደፈር የሌለበት ነዉ ሲል በጽናት የቆመ ሀይል ነዉና ኢትዮጵያዉያን የሀገራዊ ተስፋን ከመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት ዉስጥ ሲፈልቅ በደስታ ያስተዉላሉ::
በመሆኑም በኢትዮጵያ ተቃዉሞ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠዉ  የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት  Saturday/ January23/2020 ከጠዋቱ 11:00 AM  EST (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የካቲት 23/2013 ዓም ከምሽቱ አንድ ሰዓት) ጀምሮ ባዘጋጀዉ አለም አቀፍ ዉይይት እና የድጋፍ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል:: የስብሰባዉን የዙም ሊንክ ቀኑ ሲደርስ እናሳዉቃለን
ሀ.የዉይይት ርዕሶች
————
1. የአቢይ መንግስት ምርጫዉ ወደሚል ቀልድ ከመግባቱ በፊት የመኢአድ ባልደራስ መሪን እስክንድር ነጋን እና አጠቃላይ የባልደራስ  አመራሮችን እና አባላትን የመፍታት ግዴታ አለበት
2.በአማራ/አገዉ ማህበረሰብ ላይ በመተከል በወለጋ የሚደረገዉ የዘር ፍጅት በአስችኳይ ሊቆም ይገባዋል::
3.ከመተከል እንዲሁም ከወለጋ የተፈናቀለዉ የአማራ/አገዉ ማህበረሰብ በአስቸኳይ የመልሶ ማቋቋም እና እርዳታ ሊደረግለት ይገባል
4.የኢትዮጵያን ሀገራዊ ልኡዋላዊነት አስደፍሮ የኢትዮጵያን መሬት በራሱ ፈቃድ ለሱዳን መንግስት አሳልፎ የሰጠዉ የአቢይ መንግስት ያደረገዉን ከተጠያቂነት አያመልጥም
ለ. ድጋፍ ማሰባሰብ ፕሮግራም
———-
 መኢአድ ባልደራስን ይደግፉ
ትብብር
——
ይሄን ማስታወቂያ በስፋት በማሰራጨት ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ግብዣዉ እንዲደርሳቸዉ እንዲያደርጉ ትብብርዎትን እንጠይቃለን !
Filed in: Amharic