>

ተረኛ አትበሉን!!! (ግርማ ካሳ)

ተረኛ አትበሉን!!!

ግርማ ካሳ

* … የእኛ ሃገር ፖለቲከኞች ግብሩን እየፈጸሙ ስሙን ይፀየፉታል….!!!
 
*…. ትላንት ህወሃት የትግሬ የበላይነት የለም ምንም አድሎ አልፈፀምኩም ይለን ነበር ግን በማዕከላዊው (federal)  መስሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን በክልል መንግስታትም ውስጥ አድራጊ ፈጣሪዎቹ እነርሱ እንደነበሩ አሳምረን እናውቅ ነበር ።
ለእነ አባተ ኪሾ እነ በላይ ቢተው ለእነ አብዲ ኤሌ እነ ኳርተር በሁሉም ክልል ቁልፉን ስራ የሚሰሩት የትግራይ ተወላጆች ነበሩ ።
በሠራዊቱ ቤት የሌላ ብሄር ኮለኔሉን የትግራይ አሥር አለቃ ያሸማቅቀው ነበር።
ዛሬ ያ በክልሎች ያለው እንዳለ ማስቀጠል ባይቻልም አዲስ አበባና ማዕከላዊ መንግስትን መለኪያው ዕውቀት ባልሆነ ዘረኝንት አሳፋሪ በሆነ መንገድ ሲመደብበት ማየት እየተለመደ ነው በዘመነ ህወሃት በቲቪ ጋዜጠኛው የምናምን ጉዳይ ኃላፊ ብሎ ስም ሲጠቅስ እዚያው ክልል አንድ ነበር አሁን ልክ በዚያው መስመር ስሙ የሚያመላክተው ወደነ አዳነች አቤቤ አካባቢ ሆኗል።
ማረጋገጫ ከፈለጋችሁ አሥሩም ክ/ከተሞች ሂዱና ከዋና ሥራ አስፈጻሚው እስከ ቀበሌ ሥራ አመራሮች ቁልፍ እንደ መሬት አስተዳደር አነስተኛና ጥቃቅን ገቢዎች የመሳሰሉትን ብትመለከቱ መልሱን ታገኙታላችሁ ።
ግን አፍጠው የምን ዘረኝነት ይሉናል ።
የሚያሳዝነኝ የህወሃትን መጠቀም ያየ የህወሃትን ውርደት ያለማየቱ ነው ።
ባልጠቅሰው ይሻለኝ ነበር እኛ ብዙ ስለሆንን ማንም አይደፍረንም ይላሉም ።
አንቃ ለአንቃ ቢደጋገፍ
ተያይዞ ዘፍ እንዲሉ ።
በ21ኛው ክ/ዘመን ይህ አካሄድ ውድቀት ያፋጥን እንደሁ እንጂ እድገትን እንደማያመጣ ጎረቤታችን ሱማሊያ ምስክራችን ናት ።
ሶማሊያ አንድ ቋንቋ አንድ ሃይማኖት ነበራቸው ግን ያን ለዓለም ዓይን የሆነ ዙሪያ ገባው የዓለምን የንግድ እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚችል ቦታ ሳይጠቀሙበት በቀውስ ይኖራሉ ዓለምንም በተቃራኒው በእውክታ ይንጧታል ።
ብናውቅበት ያገኘነውን ይዘን ለመፈርጠጥ ከምንመኝ ከእኔ ለእኔ የእኔ ከምንልም ውድቀታችንን ከምናፋጥን አብረን ክንዳችንን አጠንክረን ብንሰራ የተሻለ ይሆን ነበር።
ለረጅም ዘመን ያለፉትን ባለዘመን ተረኞች ስንመክር እኛ ሥራ ላይ ናን ይሉን ነበር እንዲህ ዛሬ እንዳናዝን ሲያሳዝኑ ግራ ሊያጋቡን።
  ወንድሞቼ የዛሬው አፍላ ባለግዜዎች ይህ አካሄድ ፍጹም ያጠፋችኋል እባካችሁ ትንሽ ተረጋጉ ።
በጣምየሚገርመኝ ደግሞ ፍጥነቱና ፈጠቱ እናንተ ላይ ሜካፑም አልሰራም ግጥጥ ብሎ ነው የሚታየውና ይኸ ፍጥነታችሁ አግችቦ በአጭር ነው የሚያስቀራችሁ።
ዛሬ ብዛትን እንደ መስፈርት የምትመኩበት ያጠፋችኋል ነገ በክ/ሃገር በሃይማኖት በጎሳ ጦር ትሳበቃላችሁ።
በጠቅላላው የሚያጠፋ መንገድ መርጣችኋል ። ሃገር የጋራ ነው ተረኝነት ሞኝነት ነው።   ተረኝነትማ ግጥም አድርጎ አለ።
Filed in: Amharic