ዩኒቨርሲቲዎቻችን የተማሩ ወጣቶችን በማፍራት ፈንታ ዱላና ድንጋይ የሚያነሱ ወጣቶችን ካመረቱ ችግር አለ ማለት ነው. . .
ታማኝ በየነ
“… ሰው ያስባል ፤ የተነገረውን ሁሉ ይዘን እንደ ጎርፍ ወደየአቅጣጫው እንሄዳል? ወይንስ ቆይ ለምን እንዴት? መቼ ብለን እንመረምራለን? ይሄንን ማሳየት ከቻላችሁ ነው የተመረቃችሁ የምትባሉት፡፡ አለዛ በሀገራችን ውስጥ ያለው አደጋ በጅምላ መነዳት ነው፤ ማሰብ መቻል አለብን ፤ የተወለድንበትን “ብሔር ብሄረሰብ” የሚባለውን ነገር ማንም በጉልበት አይነጥቀንም ፤ ከኛው ጋር የሚኖር ነው ግን ይሄ የመለያየት ምክንያት ሆኖ በየጊዜው ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩ ወጣቶችን ማፍራት ቀርቶ በየጊዜው የሚደባደቡ ካወጣ ችግር አለ! ለዘመናት ለአፍሪካ አርዓያ የነበረች ሀገር በዚህ መልክ በየአቅጣጫው የሞት መርዶ በየቀኑ ምንሰማበት ከሆነ አገር ከሆነ ራሳችንን ነው መጠየቅ ያለብን፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 1 ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው የነበረው ዛሬ ብዙ ዩኒቨርሲቲ አለ የዛ ሁሉ ዩኒቨርሲቲ ወጣት የምርምር ብቃት ፣ የት ደርሶ ነው? አንዱ ብሔር ካንዱ በየምክንያቱ የሚደባደበው? በየምክንያቱ የሚጣላው? ራሳችንን እንጠይቅ ! እኔ ከውጭ ነው የመጣሁት እኔና መንግስት እንዳማንስማማ ታውቃላችሁ … እና እዚ ጋ ስታዩኝ ይሄ ሰውዬ ብልጽግና ነው ብላችሁ እንዳይሆን .. እመረምራለሁ እጠይቃለሁ … የሚሰማኝን እንደዜጋ እቃወማለሁ፡፡ በጎ ሲሆን ደግሞ በጎ ነው እላለሁ! በልዩነት መኖር እንደሚቻል ማሳየት መቻል አለብን ፡፡
ጥር 2013 ዓ/ም ኢትዮጵያ