>
5:33 pm - Thursday December 6, 4108

የዛሬዎቹ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያን በራሳቸው ወርድና ቁመት ለክተው እንደ ቅርጫ ስጋ ሊቀራመቷት አሰፍስፈዋል....!!! (ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ  አባተ)

የዛሬዎቹ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያን በራሳቸው ወርድና ቁመት ለክተው እንደ ቅርጫ ስጋ ሊቀራመቷት አሰፍስፈዋል….!!!
ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ  አባተ

*…. የኢትዮጵያ ንጉሥ እንደሚሆኑ በእናታቸው ትንቢት  የተነገራቸው ጠቅላይ ሚንስቴር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ማዳን  አልቻሉም!
ኢትዮጵያ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን አሁን  ወደ  አለችበት ምስቅልቅል ትገባለች ብሎ ያሰበ አለ ብየ አላምንም።
ኢትዮጵያ  በዓለም ላይ ካሉ ታልልቅ ሀገሮች
መካከል አንዷ የታሪክ የቅርስ የስልጣኔ  የጠቢባን  እና  የጥበብ ሀገር የነገስታት  ምድር   ነበረች።
ኢትዮጵያ  ዓለም በባርነት በቀኝ ግዛት ስር ወድቆ  ነፃነቱ ተገፎ  አንገቱን ደፍቶ በሄደበት በዚያን   ዘመን  ኢትዮጵያ ማንም ሳይደፍራት ታፍራ ተከብራ የኖረች  የኩሩ  የጀግናና የአርበኞች ሀገር ነበረች።
ሆሜር የሚባል አንድ ጀርመናዊ ምሁር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያኑን  ሲገልፃቸው
ከክርስቶስ ልደት ስድስት መቶ ዓመት በፊት
ኢትዮጵያውያን ደጎች ርህሩሆች እንግዳ ተቀባዮች  ጠይምና መልከ መልካም ሰዎች የሚኖሩባት የጀግኖች ሀገር ነች  ብሏታል።
 አውሮፓውያን አቢሲንያ ይሏታል ።አረቦች  ሐበሻ ይሉናል እኛ ግን ኢትዮጵያውያን ነን ሀገራችንም    ኢትዮጵያ ናት  እንላለን።ኢትዮጵያ  በጣም ጀግኖች ሀገር ወዳድ መሪዎች የነበሯት  ሀገር ነበረች።
በአኩሱም ዘመነ መንግስት አብርሃና አፅብሃ
እንድሁም አፄ ካሌብን የመሳሰሉ ነገስታት ነበሯት።
ወደ   ሮሐ ስንመጣ  ይምርሃነ ክርስቶስ ከባህር ላይ መቅደስ የገነባላት  ጀግና እንደ ቅዱስ ላሊበላ  ያለ ፃድቅ ንጉስ  አለት ፈልፍሎ በድንጊያይ ላይ  ታሪክ የፃፈላት ነበረች።
አፄ ዘራያ  ያዕቆብን አባቱን አፄ ዳዊትን ስንመለከት በሀገር ፍቅር  የተቃጠሉላት ኢትዮጵያውያን መሪዎች ነበሯት።የበጌምድርን ቤተ መንግስት  ስንመለከት  እንደ  አፄ ፋሲል ያለ  ገናና መሪ  እንደ ፃድቁ ዮሐንስ  ለሰው ልጅ ቀርቶ የእንስሳ መብት እንድከበር አዋጅ ያስነገረ  እንደ መናኔ መንግስት ተክለ ሃይማኖት ያለ  ዓለም በቃኝ ብሎ  የመነነ መሪ ነበራት።
ኢትዮጵያ  አሁን ባሉት  አገር ወዳድ ሳይሆኑ  ራስ ወዳድ መሪዎች እጅ ትገባለች ብሎ ያሰበ አልነበረም  ሀገራችን  በደም ባጥንት የተገነባች አባቶቻችን ራሳቸውን ክደው የሞቱላት ዋጋ የተከፈለባት  የአፄ ቴዎድሮስና የአፄ ዮሐንስ የደም ምድር ነች   የዛሬዎቹ ፖለቲከኞች ይህን ስንነግራቸው ሊረዱን አልቻሉም  ኢትዮጵያን በራሳቸው ወርድና ቁመት ለክተው እንደ ቅርጫ ስጋ ሊቀራመቷት አሰፍስፈዋል።
በተለይ   የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች ባለስልጣናት  የህዝብን አደራ ዘንግተው  የተሰጣቸውን ሀላፊነት ወደጉን በመተው በአፋቸው ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ በተግባር ኢትዮጵያ አፍርሰዋታል ።
አክራሪ የኦሮሞ  ዘረኞችና ተረኞች  ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከኖረች  አንድም  አማራ የለለባት ኢትዮጵያ ለመፍጠር ጥረት እያደረጉ  ነው  አማራው  በዘረኛች   ክፉና አክራሪ ብሄርተኞች በተቀነባበረ  ሴራ  ግፍና መከራ እየተቀበለ ነው ። አማራ ሙቶ አላልቅ ካለ ኢትዮጵያን መፍረስ ነው። ራእያቸው
ለዚህ ነው  አሁን ኢትዮጵያ   መንግስት አልባ
ሁና እንደ ነበረችው  ሱማልያ  መሪ አልባ ሁና
ዜጎቿ  እንደ  በግ እየታረዱ  ሰሚ  ያጡት  በኦሮሞ ብሄርተኞች አቀነባባሪነት   ኢትዮጵያ በጥላት ተከባለች  የበጌምድር ግዛት በሱዳን ተወሯል   በመተከል በወለጋ  ህዝብ እየታረደ ነው  የትግራይ ህዝብ አደጋላይ ወድቋል።
የኮንሶ ህዝብ  እያለቀ ነው።  አድስ አበባ ሙሉ በሙሉ በኦሮሞ አክራሪዎች ብሄርተኞች  እጅ ወድቋል  በፌድራል ተቋማትም ሌላው ኢትዮጵያዊ ተገፍቶ ወጥቷል።
ምንጭ     (አሻራ ጥር፣15፣2013 ዓ•ም ባህርዳር)
Filed in: Amharic