>

ኢዜማን ለምን ጠላሁት ?! (አሳዬ ደርቤ)

ለኢዜማ ያለኝ ጥላቻ የሚመነጨው ለአብን ካለኝ ፍቅር .፤ ለብልጽግና ካለኝ ድጋፍ ከመሰላችሁ አልተገናኘንም… !!!

አሳዬ ደርቤ
 
*….እኔ  የየትኛውም ድርጅት ካድሬ ሆኜ አላውቅም፡፡ ይልቅስ እንደ አንድ ግለሰብ ኢዜማዎችን የጠላኋቸው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡
➺ፓርቲው የብልጽግና ሃይ ኮፒ በመሆኑ
➺ከቅንነት ይልቅ ሤረኝነት፣ ከሥም ይልቅ ጥቅም ስለሚገዛቸው
➺የአማራ ሕዝብ ሲገደልና ሲፈናቀል ድምጽ በመሆን ፈንታ ድምጹን እንዲሰጣቸው ብቻ የሚፈልጉ መሆናቸው
➺ባልደራስን እያወገዙ ከንቲባውን ሲያግዙ ከርመው እስክንድር ሲታሠር ጩኸቱን እና ልፋቱን ሰርቀው ትርፋማ ለመሆን ሲዳክሩ መታየታቸው
➺አንድ አማራ በሕይወት ሲኖር ኢትዮጵያዊ፣ ተገድሎ ሲቀበር ግን አማራ ይሆናል›› በሚል አስተሳሰብ በዝምታ ማለፋቸው እንዳለ ሆኖ፣ ጥቃቱ ዝም ለማለት የማይመች ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በማንነቱ የተገደለን ሕዝብ ዜጎች በሚል መጋረጃ መሸፋፈናቸው፣
➺አገር ከሚያፈርሰ እና ደም ከሚያፋሰሰ ፓርቲ ይልቅ በምርጫ ይፎካከረናል ወይም ደግሞ ሕዝቡን ያስከዳብናል ብለው የሚያስቡትን ፓርቲ (አመራር) በጠላትነት የሚመለከቱ መሆናቸው፤
➺አቅም ካለው ፖለቲከኛ ይልቅ ጥቅም ከሚያስገኝላቸው ደላላ ጋር የሚሻረኩ መሆናቸው…
➺አገር አላከማል ስትሆን እያዩ በፍርሐትና በጥቅመኝነት ተተብትበው ዝም ማለታቸው እንዳለ ሆኖ ይሄን ዝምታቸውን አገር የመታደጊያ ስልት እና አርቆ አሳቢነት አድርገው ማቅረባቸው
➺ኢትዮጵያን ለጠራለት ሁሉ ልቡን እና ገንዘቡን የሚሠጠው ሕዝብ አላግባብ ሲጠቃ ጠበቃ ሆነው ሊደርሱለት ሲገባ፣ ፓርቲያቸው ለአደጋ ሲዳረግ ነፍጡን ተሸክሞ አብሯቸው ወደ በረሃ እንዲገባ፣ ፓርቲያቸው ሲመቸው ደግሞ እነሱን አዝሎ ቤተ መንግሥት እንዲያስገባ የሚፈልጉ መሆናቸው
➺በዝምተኛ እና በሤረኛ መንግሥት የሚቀነባበር ጥቃትን ለማስቆም ከፍተኛ ጩኸትና ውግዘት አስፈላጊ መሆኑ እየታወቀ በጅምላ የተገደለ ዜጋ ክብሩን በማይመጥን መልኩ እንደ ውሻ በተቀበረበት ቀን የፓርቲው የፌስቡክ ጦርና አመራር ከመንግሥት ጋር በመተባበር በሰበር ዜና እልቂቱን ለማዳፈን የሚጥሩ መሆኑ…
➺የሚመራትን አገር ለከባድ ችግር የሚያዳርገውን መንግሥት ለችግር መዳረጉን አምነው በአገራቸው ሕልውና ፈንታ የመሪዋን ሥልጣን ለመታደግ የሚጥሩ መሆናቸው…
➺የዘር ፖለቲካ ከመስፋፋትም አልፎ ሌላውን ወደማጥቃት ወደተሸጋገረባቸው አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ዜግነቱን እና ዜጎችን የሚያከብር ዜጋ ከመፍጠር ይልቅ በዜግነቱ (በማንነቱ) የሚገደለውን ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ስብከት እያደነዘዙና እየበዘበዙ ለመኖር ማሰባቸው…
➺የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ካደረጉት ልብ ላይ ቀስት ሳይጨምሩ መቅረታቸው…
Filed in: Amharic