>

አዎ ጊዜው አሁን ነው....!!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

አዎ ጊዜው አሁን ነው….!!! 

አቻምየለህ ታምሩ

በሕወሓት ዘመን የሕወሓቱን ፍጡር ብአዴንን ስንቃወም ከሁሉ በፊት የሚዘምቱብን የሕወሓት ካድሬዎቹ እነ ዳንኤል ብርሀነ፣ ወንድሙ ፍጹም ብርሀነ፣ ሰናይት መብርሀቱ፣ ዘርዓይ ኃይለ ማርያም፣ ወዘተ ነበሩ። እነ ዳንኤል ብርሀነ ፍጡራቸውን ብአዴን ስንቃወም ከብአዴን ግብረ በላዎች ቀድመው ይቃወሙን የነበሩት ብአዴን የሕወሓት ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ የአማራ ድርጅት እንዳልነበር ስለሚያውቁ ነው። ዘንድሮም የአማራ ልጆች በሚያደርጉት ማናቸውም ነገር ከባለበቱ ከብአዴን ቀድመው እየበረገጉ የሚገኙት ተረኞቹ የኦሮሙማ አስኳዶች ሆነዋል።
በርግጥ እውነት አላቸው። ያለ እረፍትኢትዮጵ ያን ለመሰልቀጥ ሲሰሩ confuse እና convince እያደርጉ ቁማር የሚጫወቱበት ጉዳይ አስመጻሚያቸው ሲነካባቸው ዝም ብለው ሊያዩ አይችሉም። እነሱ ሙሉጊዜያቸውን አማርኛ የማይነገርባት፣ ኢትዮጵያን የምታክል ኦሮምያና ኦሮሞን የምትመስል ኢትዮጵያ ለመፍጠር እስከ ጥግ ድረስ ሲሰሩ ጠላት ያደረጉትን አማራ ትግል ወደ ኋላ የሚጎትትና የተሻለ መሪ እንዳይወጣ አንቆ የሚይዝ በአማራ ስም የሚጠራ ድርጅት ያስፈልጋቸዋል።
ለዚህም ነው confuse እና convince አድርገን ቁማር በላነው ሲሉ የተሳለቁበትን ድርጅት በቀዳሚነት የሚመለከት ጉዳይ በተነሳ ቁጥር ሰማዩንም ምድሩንም ሲጠቀልሉ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ቆጥቦ ያሰራቸውን ኮንዶ ቤቶች  ከ15 ዓመታት በላይ ተመዝግቦ ሲጠባበቅ በነበረው አዲስ አበቤ ላይ ቁና ደፍተው ከክልላቸው ወደ አዲስ አበባ በገፍ እያስገቡ ለሚያሰፍሩት የነገዳቸው ተጋሪ በአስር ሺዎች  የሚቆጠሩ ቤቶችን ሲያስተላልፉ፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ የአማራ ቤተሰቦች ብቻ እየተመረጡ ቤታቸው ሲፈርስ፣ የአዲስ አበባና የፌዴራል መንግሥት ተብዮው ሹመቶች በባለጊዜዎች ሲሞሉ፣ የአዲስ አበባን ዴሞግራፊ ለመቀየርና ታሪክ ለማጥፋት በፍጥነት ሲሰሩና የፈለጉትን ሲያደርጉ ዝም ብሎ በማየት የሚተባበራቸውን ድርጅት ከሱ ቀድመው ቢከላከሉት አይፈረድባቸውም።
እኛ ግን እንዲህ እንላለን! ሕገ መንግሥት ተብዮው እየተተገበረ በኢትዮጵያ ምድር ተበርግዶ  የከፈተውን የሲኦል በር ገብረብ ለማድረግ፤ በአለማችትን በአጠቃላይ ታይቶ የማያውቀውን በአማራ ላይ  በየቀኑ እየተፈጸመ የሚገኘውን የፍጅት፣ የጭካኔ እና የዘር ማጥፋት አይነት የሚቆምበት፤ እናቶች፣ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች በማንነታቸው ተለይተው ለመስማትም ለማየትም በሚዘገንን መልኩ ማሕጸን ተቀዶ ጽንጽ ሜዳ ላይ የሚጣሉበት፣ ስጋቸው የሚበላበት፤ ገበሬዎች በማሳቸው ላይ የሚገደሉበት፣ እናቶችና ሕጻናት ቤታቸው በተቀመጡበት በዐይናቸው፣ በአፍንጫቸውና በጀርባቸው ላይ በመርዝ በተነከረ ክርክር ያለው ቀስት እየተቀደዱ በምድር ላይ ተፈጽሞ የማያውቅ የጅምላ ፍጅት በየሰርኩ እየተፈጸመባቸው እንደ ቆሻሻ በግሬደር ተዝቀው በጅምላ የሚቀበሩበት፤ ጽንስ ተቀዶ እየወጣና የሰው ስጋ እየተቆረጠ እንዲበላ የሚያደርግ ወይም ማስቆም የማይችል የጭካኔ አገዛዝ በመንግሥትነት የተሰየመበት፤  አገራችሁ አይደለም ውጡ እየተባሉ ሜዳ ላይ የሚጣሉበትና ዋና ከተማችን በዘውግ በተሰባሰቡ ወሮበሎች የሚዘረፍበት ዘመን የሚገታበት፤ የኦሮሙማ ፖለቲካ ያስከተለው አገራዊ ቀውስ የሚቆምበት፤ የወጀለኞች፣ የቀማኞችና የግፈኞች አገዛዝ እድሜ የሚያጥርበት፤ ተረኞች፣ ሰልቃኞች፣ አራጆችና ጨፍጫፊዎች ከነቄስ ሞገሴዎቻቸውና ውታፍ ነቃዮቻቸው  ጋር ወደ ሕግ የሚቀርቡበትና ኢትዮጵያ በቀደመ እውነቷ የምትድንበት ጊዜው አሁን ነው!
Filed in: Amharic