>
5:09 pm - Sunday March 3, 9501

ኢዜማ... እጅግ እሥስታዊ ባህሪ  ብሎም የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ የሚዳክር  ስብስብ...(ሸንቁጥ አየለ)

ኢዜማ… እጅግ እሥስታዊ ባህሪ  ብሎም የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ የሚዳክር  ስብስብ…

ሸንቁጥ አየለ

1-የአዲስ አበባ ህዝብ ሲፈናቀል ሲገደል እና ሲታሰር ድምጽ ያላሰማዉ ተቃዋሚ ኢዜማ ነው
2-  የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በግፍ በጅምላ ሲታስሩ ብቻ ሳይሆን በግፍ ሲቀጠቀጡ የመቃወም ድፍርት ያጣዉ ኢዜማ ነዉ
3- የአዲስ አበባ ህዝብ እራሱን በራሱ እንዳያስተዳደር የሚቃወም : የአዲስ አበባ ህዝብ የግድ በኦነግ/ኦህዴድ መተዳደር አለበት ብሎ ያወጀ ኢዜማ ነዉ
4-በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የመሬት ወረራ የድሆች መፍናቀል የኮንዶሚኒየም ዘረፋ ሲፈፅም  ምንም አልተፈጠረም ብሎ ያለፈ
5-ለአዲስ አበባ ህዝብ መብት የቆመዉን እስክንድር ነጋን በአክራሪ አማራነት የከሰሰ
6-እነ አሳምነዉ ጽጌ እና የአማራ ክልል ፋኖዎች መደምሰስ አለባቸዉ ብሎ የቀሰቀሰ
7-ኦነግ/ኦህዴድ 35 ዙር ልዩ ሚኒሻ ሲያሰለጥን እጁን እያወጣ የሚያጨበጭብ : የአማራ ክልል ግን ገና አንዱ ዙር ሚኒሻ አሰለጠነ ብሎ የአማራ የበላይነት ሊመለስ ነዉ ብሎ እየዬ የሚቀመጥ
8-የአማራ ህዝብ በጅምላ በመላ ሀገሪቱ የዘር ፍጅት ሲደረግበት በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት አልተደረገበትም ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣ
8-የተዋህዶ እምነት ተከታይ በጅምላ በመላ ሀገሪቱ የዘር ፍጅት ሲደረግበት በተዋህዶ እምነት ተከታይ ላይ የዘር ፍጅት አልተደረገበትም ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣ
9-አንዲ ሚሊዮን የጌዴዎ ማህበረሰብ ከቀዬዉ የዘር ጭፍጨፋ ተደርጎበት ሲፈናቀል በሽግግር ወቅት የሚከሰት ነዉ ሲል የተሳለቀ
10-   በውሸት ክስ ዜጎች ሲታስሩ ፍርድ ቤቶች በረጅም ቀጠሮ ሰው ሲያጉላሉ የፍትህ ስርእቱ ተሻሽሉዋል ብሎ በመሪዉ በብርሃኑ ነጋ በኩል መግለጫ የሰጠ
12-  ለፍርድ መቅረብ ያለበትን ታከለ ኡማን አምነዋለሁ አዲስ አበባን ሊመራ የሚገባዉ እሱ ብቻ ነዉ ሲል የሀሰት ምስክርነት የሰጠ
13-  ሰባ አመታት የአማራን ህዝብ እና የተዋህዶን ክርስቲያን ሲያርድ ከነበረዉ ኦነግ ጋር የጋራ  ንቅናቄ የፈጠሩ መሪዎች የሚመሩት
14-  በቄሮ/ኦህዴድ/ኦነግ/ኦነግ ሸኔ ለሶስት ተከታታይ አመታት የዘር ፍጅት በኢትዮጵያዉያን ላይ ሲደረግ የማይቃወም ኢዜማ ነዉ::
15-በሶስት አመታት ዉስጥ ብቻ ከአራት ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን ዜጎች በላይ ሲፈናቀሉ:ከቀያቸዉ ሲሰደዱ እየተሳለቀ ይሄ የሽግግር ሂደት መገለጫ ነዉ የሚል መግለጫ ያወጣ
16-በአሁኑ ሰዓት በመተከል እና ወለጋ በአገዉ/አማራ ማህበረሰብ ላይ የሚደረገዉን የዘር ፍጅት በስሙ ለመጥራት የማይደፍር
17-ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ተፈጥራለች የሚል የፖለቲካ ፍልስፍና ይዞ የሚዞር ኢዜማ ነዉ::በዚህም አማራ እና ትግሬ ቅኝ ገዥ ናቸዉ ብሎ የሚያምን ብቻ ሳይሆን ካሁን ብኋላ ስልጣን ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ መሄድ አለበት የሚል እጅግ አደገኛ እና ዘረኛ አስተምህሮት የሚዘራ በኢትዮጵያዉያን መሃከል እልቂትን የሚያስከትል የፖለቲካ ፍልስፍና የሚከተል ድርጅት ኢዜማ ነዉ
18-ኦርቶዶክስ ጨቋኝ እምነት ነበረች ብሎ የሚሰብክ ድርጅት ኢዜማ ነዉ::ኢዜማ እንደ ቀደሙት ሸዉራራ አክራሪ ሶሻሊስት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም እንደዚህ ዘመን የአክራሪ የጎሳ ፖለቲካ ፓርቲዎች እጅግ አደገኛ የሆነ የጸረ አማራነት የጸረ ኦርቶዶክስነት ፍልስፍና የሚያራምድ ነዉ::
19-ለክስ እና ለወቀሳ እንዲሁም አማራዉን ለማሳረድ ሲሆን ኢዜማ የአማራ ነገድ ጨቋኝ ነገድ ነዉ:ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ተፈጥራለች ብሎ ይቀሰቅሳል::ሆኖም አማራዉ ሊደራጅ ሲሞክር ደግሞ አማራ የሚባል ነገድ የለም ብሎ መጽሀፍ ጽፎ ያሰራጫል::
20-ኢዜማ ማለት እንደ አንዳርጋቸዉ ጽጌ አይነት የማንነት ቀዉ ባላቸዉ ሰዊች እንደ ብርሃኑ ነጋ አይነት ሁሉን ነገር በመሸጥ እና በመግዛት የሚያምኑ መርህ በሌላቸዉ ሰዎች የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ር ዕዮተ አለሙም በግራ መጋባት ላይ የቆመ ድርጅት ነዉ::ይሄ ስም ማጥፋት አይደለም::
ሁለት ምሳሌዎችን ብቻ እንጠቀስ::
21_አንዳርጋቸዉ ጽጌ አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ መጽሃፉ “እኔ አማራ ነኝ” ሲል ምስክርነት ሰጠ:: በሁለተኛ መጽሃፉ “ነጻነት የማያዉቅ ነጻ አዉጭ ” በሚለዉ መጽሃፉ ደግሞ “እኔ ከሸዋ ኦሮሞ እና ከሸዋ አማራ ነገዶች የተገኘሁ ነኝ” ሲል ምስክርነት ሰጠ::በሶስተኛዉ መጽሃፉ ደግሞ “አማራ የሚባል ነገድ የለም ሲል ምስክርነት ሰጠ::ይሄ ሰዉ የጻፋቸዉን መጽሃፎች አንብቧቸዉ::እንዲህ አይነት የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ የገባ ሰዉ ለሽህ ዘመናት ስነ መንግስት መስርቶ የኖረዉን የአማራ ህዝብ ሲራገም እና ጨቋኝ ነዉ ሲል የሚዉል ሰዉ ነዉ::የአማራ ህዝብ ጨቋኝ ነዉ:ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ነዉ የተፈጠረችዉ ሲል ማብራሪያ የሰጠዉ አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ መጽሃፉ ነዉ::አቢይ አህመድ እንኳን ሁለት ጊዜ ብቻ ነዉ የማንነት ክህደት ሲፈጽም የታዬዉ::በአንዱ መረጃዉ እናቴ ክርስቲያን አማራ ነች አለ::ሁለተኛ ባሰራጨዉ መረጃ ደግሞ እናቴ የሸዋ ኦሮሞ ነች አለ::አንድዳርጋቸዉ ጽጌ ግን ሶስት ጊዜ በራሱም ላይ በአማራ ህዝብ ላይ የማንነት ክህደት ሲፈጽም ተስተዉሏል::
22-ብርሃኑ ነጋ ንግድና ፖለቲካን የሚቀላቅል ደፋር ከመሆኑ የተነሳ እነ ኢሳያስ እንዳስጠኑት እና ወያኔዎች  የሚነፉትን ፕሮፖጋንዳ መሰረት አድርጎ ግ7 ሲመራ በነበረበት ወቅት በድፍረት “አማራ የሆናችሁ ወደ ኋላ ተደበቁ::ምክንያቱም  ወያኔ አማራ መጣብን እያለች ፕሮፖጋንዳ ትሰራብናለች::ስለሆነም አማራ ወደ ግ7 አመራር መምጣት የለበትም” ሲል መመሪያ ያስተላለፈ ሰዉ ነዉ::ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያን መንግስት አግኝቶ ምን አይነት መሪ ሊሆን እንደሚችል መገመት ነዉ::ብርሃኑ ነጋ የሀገሪቱን ቁጥር አንድ ብዛት የአለዉን የአማራ ነገድ ሻቢያ ስላዘዘዉ ወይም ወያኔ ፕሮፖጋንዳ ስለምትሰራበት ሀገር ሊመራ አይገባዉም የሚል የተቃወሰ የስነልቦና ጭብጥ ተሸክሞ የሚዞር ፖለቲከኛ ነዉ::
23-ኢዜማ ለአዲስ አበባ ህዝብ ድምጽ በመሆን ከፍተኛ እዉቅና ያገኘዉን እስክንድር ነጋ መታሰር አለበት ሲል ከፍተኛ ቅስቀሳ ያደረገ ድርጅት ነዉ::ይባስ ብሎም ቄሮ የሚባለዉን ሀይል ሳይቃወም እስክንድር ነጋን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ መወገድ ይገባዋል ሲል በአደባባይ የቀሰቀሰ ሀይል ነዉ::
24-ኢዜማ አሁን ያለዉ የወያኔ ህገመንግስት እንዳለ እንዲቀጥል የተከራከረ : ምርጫዉም በዚሁ  ህገመንግስት እንዲከናወነ ሲከራከር የነበረ  እንዲሁም ኦነግ/ኦህዴድ አሁን ያለዉ ህገመንግስት ይቀጥሉ እስካሉ ድረስ በዚሁ ህገመንግስት ለመተዳደር እስማማለሁ ብሎ ቃሉን በአደባባይ የሰጠ የኦነግ/ኦህዴድ ጉዳይ አስፈጻሚ ሀይል ነዉ
እንግዲህ ምርጫ የሚባለዉ የአቢይ ቀልድ ሲደረግ  ኢዜማን የምትመርጥ ሁሉ የምትመርጠዉ ከኦነግ/ኦህዴድ የከፋ ዘረኛ ሀይልን ብቻ ሳይሆን እጅግ እሥስታዊ ባህሪ  ብሎም የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ የሚዳክር  ስብስብን መሆኑን እወቅ::
Filed in: Amharic