>
5:33 pm - Thursday December 6, 3027

ከሱዳን የጦር ጀኔራሎች በስተጀርባ ያሉ የአረብ ነጋዴዎች አካሄድን በጥንቃቄ  በመከታተል አፋጣኝ አፀፋ መውሰድ ያስፈልጋል!!!! (ጋዜጠኛ ሥለዓባት ማናየ)

ከሱዳን የጦር ጀኔራሎች በስተጀርባ ያሉ የአረብ ነጋዴዎች አካሄድን በጥንቃቄ  በመከታተል አፋጣኝ አፀፋ መውሰድ ያስፈልጋል!!!!
ጋዜጠኛ ሥለዓባት ማናየ

ከሰሞኑ ሱዳን ትሪቡን እና ፋይናሽያል ታይምስ ጋዜጣ ይዘውት እየወጡ ያለው ዘገባ አንድ ትልቅ ጉዳይ የሚያስገነዝብ ነው።ሁለቱም ጋዜጦች እያፍታቱት ያሉት ካርቱም በግብርናው ዘርፍ አዲስ አቅጣጫ እየተከተለች መሆኗን ነው።
ይህ የግብርና ዘርፍ ደግሞ በዝናብ እና በመስኖ የታገዘ ቅይጥ ስትራቴጂ ነው።የካርቱም ጀኔራሎች የዳቦ ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎቻቸው የተቃውሞ ድምፆችን በዘላቂነት ለመመለስ ባይችሉም በአጭር ጊዜ እፎይታ ለማግኘት ግን የግብርና እቅዳቸውን ይፋ ማድረግ እና ወደ መሬት የመውረድ ጅማሮ በማሳያት የተስፋ ዳቦ ችርቻሮ ላይ ናቸው።
መታዬት ያለበት የካርቱም የጦር ጀኔራሎች በስተጀርባ እነማን አሉ የሚለው ጉዳይ ነው??ከሁለት ዓመት በፊት የወጣ አንድ በአረብ ብሔራዊ የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ላይ የሚያጠነጥን ዘገባ እና ሪፐርት እንደሚያሳየው አረቦች በግብፅ እና በሱዳን ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን በረዥም ጊዜ ኮንትራት እየተስማሙ ማልማት ይፈልጋሉ።
ካርቱምም የዚህ ግዙፍ ቀጣናዊ ስትራቴጂ አንዷ አካል ናት። የኢትዮጵያን መሬት በሃይል ወረራ በማካሄድ እያደረገቸው ያለው እንቅስቃሴን በአጭሩ መቀልበስ ይግባል። እየዋለ ካደረ ነገሩ ወደ ቀጣናዊ ጉዳዮች እየሰፋ መምጣቱ አይቀሬ ነው።
ሰሞኑን ሱዳናዊው የካርቱም ዩኒቨርሲቲ የምህድስና ምሩቅ እና አሁንም በዚያው እያስተማሩ  ያሲር ዚዳን  African arguments ላይ ባሰፈሩት የካርቱም የፖለቲካ ሽንቁሮች በሚል ሰፋ ያለ አስተያየታቸው፤አሁናዊው የካርቱም ፖለቲካ በሁለት ክሮች ላይ የተንጠለጠለ ነው።
አንደኛው ሲቪል መራሹ የእነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላህ ሀምዶክ ሲሆን ሁለተኛው ክር ላይ ያሉት ደግሞ የመለዮለባሾች የእነ ጀኔራል አል ቡርሃን ክንፍ ነው።
እን ሀምዶክ ከምዕራባዊያን እና ከኢትዮጵያ ጋር በተሻለ ደረጃ በሚባል መልኩ መቀራረብ የሚፈልጉ ሲሆን ፤
ጀኔራሎቹ ደግሞ ከግብፅ ፣ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር የተሻለ መቀራረብ ይፈልጋሉ ባይ ናቸው።እንደ ያሲር አስተያየት እነዚህ ሁለት የተቃርኖ ክንፎች በህዳሴው ግድብ እና በድንበር አካባቢ ባለው ሁኔታ ላይ ሱዳን እንደ ሀገር አንድ አቋም እንዳትይዝ አድርጓታል።
 ትልቁ ካርታ ግን የባህረ ሰላጤው ሀገራት የካርቱም ራዳር ነው!!!!
በካርቱም ሰፋፊ የእርሻ ማሳዎች የራሳቸውን የምግብ ዋስትና የማረጋጋጥ የረጅም ጊዜ እቅድ በሽግግሩ ወቅት ለማስግባት መፍጠን ።በዚህ አካሄዳቸው ደግሞ  ለጀኔራሎቹ በገፍ በርካታ ቢሊዮን ዶላር እየሰጡ(Cash Diplomacy)መሆኑ ነው በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ይነገራል።
ሁሉም የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያ የአረብ ሀገራት ከሱዳን እና ግብፅ ሰዎች ጋር በእርሻ ስራ ላይ የሚካሄድ በተለይም ዓባይን መሰረት ያደረገ የልማት ትብብርን በአንክሮ መከታታል እና አፋጣኝ የፖሊሲ እርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
ያ ካልሆነ ተቀምጠን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ አቃተን ይሆናል ነገሩ። የካርቱም ጀኔራሎችን በጥንቃቄ መከታተል እና አማራጭ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ከወዲሁ ማዘጋጀት ሳያስፈልግ አልቀረም።
በተለይ በሱዳን እና በግብፅ በናይል ወንዝ ተፋሰስ ዙርያ ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎችን በማጋበስ ላይ የሚገኘውን ድርጅት በቅርብ መከታተል ተገቢ ነው። Arab Organization for Agricultural Development (AOAD)።
ከ1970ዎች ከአውሮፓዊያን የዘመን ቀመር ጀምሮ አይኑን እኛው ቀጣና በተለይም ዓባይ ናይል ተፋሰስ ላይ አድርጎ የሚሰራ ነው። በአረቦች ረብጣ ዶላር የሚደገፍ ።
በዚህ ዙሪያ  በቀጣይ ቀናት የምለው የኖራል …
Filed in: Amharic