>
5:29 pm - Wednesday October 10, 0632

የኦሮሞ ጦር (ልዩ ሀይል) ከእንጦጦ ተራራ ጀርባ የሰፈረው ለምን አላማ ይሆን??? (መርእድ እስጢፋኖስ)

የኦሮሞ ጦር (ልዩ ሀይል) ከእንጦጦ ተራራ ጀርባ የሰፈረው ለምን አላማ ይሆን???

መርእድ እስጢፋኖስ


ከ2011ዓ.ም መገባደጃ ጀምሮ አዲስአበባ ከተማ ዙሪያዋን ከብቦ የሰፈረው የኦሮሞ ጦር ይበልጥ ወደ መዲናዋ መቅረቡ ነዋሪዎችን እያሳሰበ ነው።
በተለይ በእንጦጦ ጀርባ በሽዎች የሚቆጠር የኦነግ ጦር ከሰፈረ አንድ አመት አልፎታል ያሉት በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ናቸው።

የወንጭፍ ምንጮች እንዳረጋገጡት በእንጦጦ ተራራ ጀርባ ለሰፈረው ጦር በየቀኑ ከአስር በላይ ሰንጋ በሬዎች እርድ እንደሚፈፀም እና የቄራ መኪኖችም በየቀኑ እንደሚመላለሱ ተመልክተናል ብለዋል።
እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ይህ በየተራሮችና ጫካዎች እየተቀለበ የሚገኝ ጦር ሰሞኑን በየካና እንጦጦ ተራሮች ላይ መታየት መጀመራቸው በቅርቡ አዲስ አበባ ነዋሪዋች ስጋታቸውን ገልጸዋል ።
የኦሮሚያ ክልል ከ30-35ሽህ ልዩ ሀይል በ34 በሆነ ዙር እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም በሽዎች የሚቆጠር አዲስ ወታደሮች ማስመረቃቸውን ከሰሞኑ አስታውቀዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ ሃገራት ኤምባሲዎች ለዘጎቻቸው ጥብቅ የሆነ የደህንነት መልዕክት ማስተላለፍ መጀመራቸው ተሰምቷል። በተለይ የአሜሪካ የእንግሊዝ የእስራኤል ኢምባሲዎች “አዲስ አበባ ዙሪያ የሰፈረ ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ጦር አለ። ጦሩ በማን እንደሚመራም አይታወቅም። እናም እንጦጦን ጨምሮ ማንኛውም የውጭ ሃገር ዜጋ ለጊዜው ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳይንቀሳቀስ። በእንጦጦ ጫካም ለጊዜው የእግር ጉዞ እንዳያደርግ” የሚል መልእክት ለዜጎቻቸው በኢሜይል ማስተላለፋቸው ነው የተሰማው።

Filed in: Amharic