>

"ሰላማዊ ሰልፍ" ብሎ በሰላም የተቀመጠ ህዝብና ፓርቲ ላይ ጦርነት የማወጅ - መንግስታዊ ሸፍጥ...!!! (ደርበው ብሩክ)

“ሰላማዊ ሰልፍ” ብሎ በሰላም የተቀመጠ ህዝብና ፓርቲ ላይ ጦርነት የማወጅ – መንግስታዊ ሸፍጥ…!!!
ደርበው ብሩክ

*… ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተጻፈ ማሳሰቢያ
 
በቃ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ መቀመቅ እየሄደ እንዳለ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ የተካሄደው  ድጋፍ ሰልፍ ሳይሆን የጦርነት አዋጅ  ምስክር ነው ።
ከትናንት ወዲያ ባልደራስ ጠርቶ የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ የከለከለው ኦህዴድ መራሹ አማራ ጠል ጏይል  ዛሬ በይፋ ደጋፊወቹን ከየትም ሰበስቦ በመጥራት ህጋዊና በሠላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰውን አብንን  ሲያወግዝ  መዋሉ  እንደ አማራ ጦርነት ነው የታወጀብን  ። ሠላማዊ ዜጎችን በጅምላ ከሚገድለውና ከሚያሳድደው ኦነግ ጋር አብንን ማነፃፀር  በእያንዳንዳችን አማሮች ላይ ሰይፍ እንደ ተሳለና አፈሙዝ እንደተነጣጠረብን ነው  የሚቆጠር ።
እሄ ሁሉ ተንኮል የሚጎነጎነው በአብን ላይ እውነት ሠላማዊ ታጋይ መሆናቸውንና ሐገር ወዳድ እንድሆኑ ጠፍቷቸው ሳይሆን ባለጊዜወቹ   የኦሮሞን የበላይነት ለማንገስ ትልቅ እንቅፋት ይሆነናል ብለው በመፍራት እንጅ ።
እናም ዛሬ ኦህዴድ መራሹ ሐገር አፍራሽ ጏይል  በአብን ላይ ብቻ ሳይሆን ጦርነት ያወጀው  በመላው አማራና ብሎም  በሐገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ጭምር ነው ።
 አዲስ አበባን ለመሰልቀጥ እነ እስክንድርን አስረው ምንም ያልተባሉት ደናቁርቶች ናቸው ዛሬም በመላው አማራና ኢትዮጵያን ለማጨለም  እንደዚህ በደመ ነብስ ወጥቶ  ሠላም ለማደፍረስና  ህዝብ ተስፋ ቆርጦ የእራሱን እርምጃ እንዲወስድ ነው እየገፉን ያሉት። እሄ ዕኩይ ጏይል ከሠላም ይልቅ ከግጭት  አተርፋለው ብሎ እንደሚንቀሳቀስ  ያለፈውን ሶስት አመታት ማየቱ በቂ ማሳያ ነው።
ዛሬም በወለጋና በቤን ሻንጉል ክልል አማሮች እየተለዩ የሚጠቁት በኦነግ ሸኔ ብቻ ሳይሆን ዋናወቹ የኦህዴድ መሪዎች መሆናቸውን የሚጠራጠር ካለ የዋህ ብቻ ነው  ።
ስለዚህ ማንኛውም አማራ በውስጥም በውጭም ያለን ሁሉ  አንድነታችን አጠናክረን  እሄን ዕኩይ ጏይል ልክ ማስያዝ ይኖርብናል። በተለይም አዴፓ ከትናንት ታሪኩ ተነስቶ ዛሬም በመላላክ እሄን አማራና ኢትዮጵያ ጠል ድርጅት ጊዜ እንዲሸምት እንዳያደርግ  ጥሪያችን ማስተላለፍ አለብን ።
ኦህዴድ አብንንም ሆነ ሌላ የአማራን ተቆርቋሪ ለመምታት የብአዴን አዴፓን ፈቃድ ካላገኘ እንደማይሆን ይታወቃል  እናም ለአዴፓ መሪዎች መልክታችን መሆን ያለበት ካሁን በኋላ በአብን ላይ የሚካሄደውን ስም ማጥፋት ተከትሎ  ኦህዴዶች  እንደነ እስክንድር  ነጋ ነገም የአብንንም ሆነ ሌላ መሰል የአማራ ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን የሚያስሩ ከሆነ እርሱም ተባባሪ መሆኑን ነው ማወቅ ያለበት
30 አመት ሙሉ በተላላኪነት ሲያስፈፅም የኖረው ይበቃዋል እንጅ ከዚህ በኋላ የወደፊት ተስፋችን እንዲያጨልም የማንፈቅድ መሆኑን የትናንቱ ብአዴን የዛሬው  አዴፓ  ሊያውቅ ይገባል ።
Filed in: Amharic