>

የጨለማው ሶስትዮሽ ቀውስ (The Dark Triads)  Narcissism, Machiavellianism & Psychopathy (ደረጄ ከበደ)

የጨለማው ሶስትዮሽ ቀውስ (The Dark Triads)  Narcissism, Machiavellianism & Psychopathy

ደረጄ ከበደ
 
የጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ ማንነት 

ባለፉት 3 አመታት ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ያሳዩዋቸው ከተለመደው ወጣ ያሉ፣ ሰብአዊነት የጎደላቸው ባህሪዎች፣ በስብእና፣ በባህሪይ ቀውሶችና በአእምሮ ኬሚካሎች አለመመጣጠን ችግር በሚሰቃዩ ግለሰቦች የሚታዩትን ይመስላሉ። ሰውየው የአእምሮ ኬሚካሎች አለመመጣጠን (Brain Chemical imbalance) ችግር እንዳለባቸው የሚጠረጥሩ በርካቶች ጠ/ሚኒስትሩ በሳይኪያትሪስቶችና በሳይኮሎጂስቶች  ምርመራ ቢያደርጉ እያሉ እስከመመኘት የጀመሩበት ሁኔታ ነው ያለው።
እኝህ ሰው፣ በምን ምክንያት እንዲህ፣ ለሞቱ የማያዝኑ፣ይቅርታን የማይጠይቁ፣ የሚታዩና የሚሰሙ ነገሮችን እንዳላዩና እንዳልሰሙ የሚክዱ፣ የዜጋዎች ሰቆቃ የማይሰማቸው፣ በካሜራ ፍቅር የተነደፉ፣ ጉራ የሚያበዙ፣ ጠዋት ሲነሱ ውሸትን የአፋቸው ማሙዋሻ ያደረጉ፣ ከችግር የሚሸሹ፣ ህዝብን ለገዳዮች ዱላና ካራ እየተው የሚሄዱ፣ ለሙዋቾች መፅናናትን የማይመኙ፣ የሃገር መሪነት ላይ ተቀምጠው ብሄርን ከብሄር የሚያናክሱ፣ ሃላፊነታቸውን አለመወጣታቸው ምንም የማይቆረቁራቸውና የማያሳፍራቸው፣ ሃገርን የሚያህል አለኝታ በውጪ መንግስት የሚያስደፍሩ፣ ህዝብን ለአንበጣ ትተው በለመለመ እርሻ የሚኩራሩ፣  አማራው በጄኖሳይድ እየታረደ ስለመናፈሻ የሚያወሩ ነውረኛ ሰው ሊሆኑ ቻሉ?
ለጠ/ሚኒስትሩ ግራ የሚያጋባ ባህሪይ ሶስት መነሾዎችን እጠረጥራለሁ
1/ ከአእምሮ ኬሚካሎች (ሴራቶኒን (Serotonin)፣ ዶፐሚን (Dopamine) ኖርኤፒነፍሪን (Norepinephrin) ወዘተ.  አለመመጣጠን፣ ከአካባቢና ከአስተዳደግ ወይም ከውርስ (Hereditary) የመጡ የባህሪይ፣ የስነልቦና፣ የስብእና ቀውሶች
2/ የብልፅግና ወንጌልና የቃል እምነት (Prosperity Gospel & word of Faith) ያመጡዋቸው የምናብ ምኞቶች፣  የቀን ህልሞች፣ ውነታውን የመካድ፣ የግንዛቤና የአሰተሳሰብ ቀውሶች
3/ ቁጥር አንድ ላይ የተጠቀሱትና ቁጥር ሁለት ላይ የተጠቀሱት
    ድብልቅ።
ጠ/ሚኒስትር አቢይ ከህዝብ ጋር ካላቸው ግንኙነት፣ ከአስተዳደር አጋሮቻቸው ጋር ከሚያደርጉት ህብረት፣ ተፃራሪዎቻቸውን ከሚያሞኙበትና ከሚቀጡበት፣ ህዝቡን ዋሽተው ምንም የመሸማቀቅ ገፅታ ሳያሳዩ ከመቀጠል ችሎታቸው፣ ገና ምንም ሳይሰሩ ራሳቸውን በብዙ አመታት ውስጥ ተፈትነው በአለም ህዝብ ዘንድ አድናቆትን ካተረፉ መሪዎች ጋራ ከማወዳደር ድፍረታቸው፣ ለመታየት ለመደነቅ የማይቆፍሩት ጉርጉዋድ እንደሌላቸው ከማወቅ፣ ከገሃድ ውሸቶቻቸው፣ ለጥቅማቸው፣ለዝናቸው፣ ለስልጣናቸው የማይሰዉት ምንም ማንም እንደሌለ ከማወቅ፣ የሌሎችን ስራ የመኮረጅና የራሴ ብለው የማቅረብ ነውራቸውን ከማየት፣ የራሳቸውን የግል ህይወት እንደልዩ አድርጎ እንዲህ ተብዬ ነበር፣ እንደዚህ ተፈጥሮ ነበር እያሉ አዳንቀው ከሚያወሩት ወሬ በመነሳት፣ እኝህ ሰው ፈረንጆች The Dark Triad የተባለውን የሶስት ባህሪዎችና ስብእና ቀውሶች፣ ማለትም፣ ናርሲሲዝም (Narcissism)፣ ማክቬሊያኒዝም (Machiavellianism) ና ሳይኮፓቲ (Psychopathy) ምልክቶች አብዛኛዎቹ የሚታዩባቸውና በየቀኑ በአእምሮ መድሃኒት ሊረዱ የሚገባቸው ሰው መሆናቸው ግልፅ ነው ። ያ አልበቃ ብሎ ደግሞ የተጣመሙ የሃይማኖት ዶክትሪኖች ለምሳሌ እንደ ብልፅግና ወንጌልና የቃል እምነት (prosperity Gospel and Word of Faith) አይነቶች  ሰለባም ናቸው
ናርሲሲቲክ (Narcissistic) መሪ የሚያሳየው ምልክቶችና መለያዎች እኚሁላችሁ። ጠ/ሚኒስትሩን በዛ ውስጥ ታዩዋችሁዋላችሁ
ራስን ወዳድ መሪ (Narcissistic Leaders) ሁልጊዜ በሌሎች መሞገስን ይፈልጋል፣ ነቀፌታን ፍፁም አይሰማም፣ ሌሎች የሚሉትን መስማት አይፈልግም፣ የሚፈልገውን ለማግኘት እንባ አውጥቶ እስከማልቀስ ይደርሳል፣ በሌሎች ጫማ ውስጥ ራስን አድርጎ የማዘን ነገር አይታይበትም፣ የማይረሳና ስሙን የሚያስጠራለትን ትልቅ ስራ ለመስራት ይመኛል (የ5 ሚሊዮን ብር የሚኒሊክ ቤተመንግስት ግብዣ፣ የአለም የጊኒስ መፀሃፍ ሬከርድ በችግኝ ተከላ ወዘተ)፣ ራስን ማግዘፍ (ጉረኛነት) የየእለት ተግባሩ ነው፣ ከሌሎች ሁሉ ትልቅ እኔ ነኝ ብሎ በማሰብ ሌላውን መደፍጠጥም አለ፣ ስለራስ ብቻ መጨነቅ ይወዳል ለሌሎች ግድየለውም፣ የይገባኛልና የባለቤትነት መኩራራት ደግሞ የተለመደ ነገሩ ነው (Simmons, 2020)።
ማኪያቬሊኒዝም (Machiavellianism)
ጠ/ሚኒስትር አቢይ የማክቬሊየን ባህሪይ ያሳያሉ ያልንባቸው ባህሪዎቻቸው የሚከተሉትን ይመስላሉ።
በራስ ምኞትና ውጥን ላይ ብቻ አተኩሮ ሌሎቹን መደመሰስ፣ ከሰብአዊ መቀራረብና ከፍቅር ይልቅ ስልጣን ላይ ማተኮር፣ ቅጥ ያጣ በራስ የመተማመንና የአማላይነት ዝንባሌ፣ ሌሎችን መጠቀሚያ በማድረግ በሌሎች ትከሻ ላይ በመንጠላጠል ማደግ፣ ቢያስፈልግም አታሎና አጭበርብሮ የሚፈልጉትን ማግኘት፣ ሰዎችን ለማግባባት በውሸት ማሞገስና ሞቅ ሞቅ ማድረግ፣ መረሆና ዋጋ ማጣት፣ አንዳንዴ ደግሞ ራሳቸውን መሸሸግና ቸልተኞ መምሰል (ብዙ ጊዜ የሀዱበትን ሳይናገሩ መደበቃቸውን እናስታውስ)፣ በሞራልና ጨዋነት እምነት ማጣት፣ ለራስ ጥቅም ሌሎችን እስከመጉዳት መሄድ፣ ለሌሎች አለማዘን፣ የሚያደርጉትን ነገር አስከፊ መዘዝ አለመገንዘብና ሌሎችን ከልብ በመነጨ ፍቅር አለመቀበል ወዘተ። በተለያዩ ወቅቶች እንርኝህን ባህሪዎች አሳይተዋል (Tayler, 2016)
የአእምሮ ቀውስ/ሳይኮፓት/ሶሺዮፓት (Psychopath/Sociopath):
ጠ/ሚኒስትሩ አእምሮአቸው ትክክል አይሰራም  የሚያሰኛቸው ብዙ ባህሪይ አላቸው። ከነዛ ውስጥ የማያቁዋርጥ ውሸታቸው፣ አጭበርባሪነታቸው፣ የመፀፀት ስሜት ምንም የሌላቸው መሆናቸው፣ ግድየለሽነትና በሌሎች ሰዎች ጫማ ውስጥ ራሳቸውን አስገብተው ለመረዳት አለመሞከርና ራስን መቆለል፣  በራስ መኩራራትና ከልካይ ማጣት/መረንነት በየቀኑ ይታይባቸዋል።
የብልፅግና ወንጌል ተፅእኖ
ከሃዘንና ለቅሶ መሸሽ፣ ህዝብ አልቆ አገር ከማፅናናት ይልቅ ወደመናፈሻ መሄድ ወይም ስለ መናፈሻ ማውራት፣ አንበጣ ሃገሪቱዋን ወሮዋት እሳቸው ጎ ካርት መንዳት፣ ህዝብ ተፈናቅሎ አልሰማሁም አላየሁም ማለት፣ የሰላሳ አመት እቅድ አውጥተናል ኢትዮጵያ ከሁለት የአለም ሃያላን አገሮች አንዱ ትሆናለች ያሉበት ቅዠት(Dellusion) እነኝህና የመሳሰሉት ከእውነት የራቁ የአእምሮ ግንዛቤዎችና እምነቶች የword of faith እምነት ውጤቶች ናቸው።
 አቢይ አህመድ ከመጡ የሆነውን ስናስብና፣  ምንም እርምጃ አለመውሰዳቸውን ስናይ ጤንነታቸውን መጠራጠር ግድ ይሉዋል።
ከዚህ በታች ለተዘረዘሩትና እዚህ ውስጥ ላልተካተቱ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ወንጀሎች ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ የማዘንም ሆነ የእርማት እርምጃ አልወሰዱም።  በተዘረዘሩት ወንጀሎች በሃላፊነት የተያዙ ግለሰቦችም ይሁን ግሩፖች አልነበሩም (እርግጥ በተለመደ የመዋሸት ልምዳቸው አንዳንዴ ይህን ያህል ሰዎች ተይዘዋል ይሉናል። ያ ሁሉ ግን ውሸት ነበር)። ጠ/ሚኒስትሩ ይህ ሁሉ ህዝብ ሲያልቅ  ምንም የፀፀት ወይም የሃዘን ምልክት አልታየባቸውም።
• በኦሮሚያ ከ80 በሚበልጡ ከተሞች እና የገጠር መንደሮች ዘርን እና ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ዘግኛኝ ግድያዎች ተፈፅመዋል በዚህም ምክንት በ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ እጃቸው፣ እግራቸው ተቆራርጦ፣ አንገታቸው ተቆርጦ፣ አይናቸው ወጥቶ አልፈዋል
• በአጋርፋ የተገደሉት ሰዎች ማንነታቸው እንዳይታወቅ አስከሬናቸውን በእሳት ተለብልቦ ተቃጥሏል
• ከኦሮሚያ ክልል ብቻ ከሶስት ሚሊዮን በላይ አማራዎች ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ፣ ያለምንም መጠለያ ለችግር እና ለርሀብ ተጋልጠው መንገድ ላይ ተጥለዋል ወይም ተበትነዋል
• አለም አቀፉ የስደተኞች ኮሚሽን ( IOM )ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘርን መሰረት ባደረገ ጥቃት መክንያት ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንደተፈነቀሉ ተገልፆአል
• ቀድሞ የጎጃም እርስት በሆነችው መተከል በኦሮሙማ ተስፋፊዎች ፣ በህወሀት ርዝራዦች እና በጉምዝ ባለስልጣናት የተቀነባበረ ሴራ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ እና የአገው ተወላጆች ህፃናትንና ፣ ነፍሰጡሮችን፣ጨምሮ በአሰቃቂ ሁኔታ በቀስት ፣ በጥይት እና በገጀራ ተገለዋል ፣ መንግስታችንም የሀዘን ቀን ማወጅ ይቅርና ስለሞታችን ዜና ለመስራትም ይጠየፋል፣ በአብይ ዘመን የአማራ ነፍስ እንዲህ አርክሶታል
• በመተከል አሁንም በመቶ ሺዎች ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ በተለያዩ የመጠለያ ስፍራዎች ፣ ያለ በቂ ምግብ፣ ዉሀ እና ህክምና በስቃይ ላይ እያሉ የአገሪቱ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን በየሳምንቱ ትግራይ ምግብና መድሀኒት እያመላለሰ፣ ለመተከል ተፈናቃዮች ግን አንዴ እንኳ የላከው በትክክል ሳይደርስ በኦነግ ታጣቂዎች እና በቤኒሻንጉል አመራሮች እርዳታውን አግተው ወስደውታል
• በደቡብ ክልል ቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በርካታ የአማራ ተወላጆች በተወለዱበት ቀየ የመንግስት ታጣቂዎች እያሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ፣ ተታርደዋል፣ ቤት ንብረታቸውን ተቃጥሎአል ፣ አሁንም የእለት እርዳታ እንኳ የሚያደርስላቸው ወገን አጥተው ፣ በርሀብ እና በበሽታ ልጆች ይዘው ዕየተሰቃዩ መንግስት አማራ ጠል በመሆኑ በዝምታ አልፎታል
• በአዲስ አበባ የኦሮሙማው ታከለ ኦማ የአዲስ አበባ ህዝብ አንጀቱን አስሮ በቆጠበው ብር የተገነባውን 100ሺ ኮንዶሚኒየም ከባሌ ከወለጋ፣ ከአንቦ እየጠራ ለኦሮሞ ተወላጆች ሲያድል ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ባላየ ያልፋሉ፣ እንዴውም ታከለ ኡማ ይህን ስላደረገ የሚኒስተርነት ሹመት ሰጥተዉታል
                    ሄለን ደመቀ    (የአማራ UK ማህበር)
የጠ/ሚኒስትሩ የመሪነት ሃላፊነትን ማጉዋደልና በመተከል ግፍ ስለመጠየቅ
– ጭፍጨፋው ሲፈፀም የሀገሪቱ መሪ በመሆኑ
– መተከልን በበላይነት በቀጥታ ሀላፊነት ወስዶ እየመራ ባለበት ወቅት
   በመሆኑ
– ቢያንስ ሁለቱ ጀኖሳይዶች የተፈፀሙት ገዳይ አስገዳዮቹን ሰብስቦ
   በአነጋገረበት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ በመሆኑ
-የመንግስት ሚዲያወች ስለመተከል ጀኖሳይድ ያለውን ሁኔታ
   እንዳይዘግቡ ትዕዛዝ በማስተላለፍ
– አብረውት የሚሰሩ የአማራ ባለስልጣናት ስለመተከል እንዳይፅፉ
    እንዳይናገሩ ትዕዛዝ በማስተላለፍ
– በቅርብ እርቀት የሚገኜው የአማራ ልዩ ሀይል ገብቶ ንፁሃንን
   እንዳይታደግ በመከልከል
– እጅግ ዘግናኝ የሆነው ጀኖሳይድ ከህዝብ ጆሮ እና አይን እንዲሰወር በማሰብ የተለያዩ አጀንዳወችን በመቅረፅ ማረሳሳት:: ለምሳሌ የፓርክ ግንባታ እቅድ ዲዛይን ምናምን እያለ ጫካ ለጫካ በመዞር:: ይህንንም ተግባር ጀኖሳይዱ እየተፈፀመ ባለበት ሰዓት ለመንጋ ተከታዮቹ በሶሻል ሚዲያ በመልቀቅ
– በአጠቃላይ በዚህ ዘመን የማይጠበቅ ጭካኔን እና ግዴለሽነትን ከ100
   ሚሊዮን ህዝብ በላይ እንደ ተራ ነገር እንዲለምደው ምሳሌ በመሆን
– ከአንድ ዘመናዊ መሪ የሚጠበቅ ርህራሄ (social empathy) ስላላሳየ
                                                           (Amharagenocide)
ፈጣሪ ይታደገን !!
Simmons, L (2020). How Narcissistic Leaders Destroy from Within
(Psychology Today,2020). Psychopath.https://www.psychologytoday.com/us/basics/psychopathy
Taylor, B (2016). Machiavellianism, Cognition, and Emotion: Understanding how the Machiavellian Thinks, Feels, and Thrives. https://psychcentral.com/lib/machiavellianism-cognition-and-emotion-understanding-how-the-machiavellian-thinks-feels-and-thrives#1
Filed in: Amharic