>

ሁለቱ የአብይ አህመድ ተረኞቹ "ጁንታዎች" !! (ሀብታሙ አያሌው)

ሁለቱ የአብይ አህመድ ተረኞቹ “ጁንታዎች” !!

ሀብታሙ አያሌው

አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘውን የአቶ አባይ ፀሐዬን ቤት አስለቅቆ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ወርቅ አድርጎ አድሶ ለመግባት ቀናት ሲቀረው፣ እዚያው ቤት ለፊት ወይዘሮ አዜብ መስፍን የምትኖርበትን ቤት እንድትለቅ ተደረገ። አቶ ሽመልስም አይኑ ቀላ፣ ሰፊውን ቤትም ለመያዝ ቋመጠ። የአቶ አባይ ፀሐየን የመንግስት ቤት ለመውረስ ያወጣሁት ረብጣ ገንዘብ ቀርቶብኝ፣ የተንጣለለውን የአዜብ ቤት ልውረስ የሚል ሀሳብም መጣለት። ወዲያውም የአዜብን ቤት በእጁ አስገባ።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለእድሳት አያሌ ገንዘብ ያወጣበትን የአባይ ፀሐዬን ቤት በመተው የአዜብን ቤት ሲወርስም፣ በቅርብ ርቀት ሲቋምጥ የነበረው የቀድሞው ብሄራዊ ደህንነት፣ የአሁኑ ፌደራል ፖሊስ ጀኔራል ደመላሽ በሽመልስ የታደሰውን የአቶ አባይን ቤት አፈፍ አደረገ።
Filed in: Amharic