>

ለንጉሱ አጎንብሱ !! (እንግዳ ታደሰ)

ለንጉሱ አጎንብሱ !!

እንግዳ ታደሰ

•  በዛቻና ማስፈራሪያ ያስወጡትን ህዝብ ነው 
• “በራሱ ፍቃድ ግልብጥ ብሎ ወጣ” እያሉ የሚያደነቁሩን…!!!
 
ለጠሚው ማንገሻ ህዝቡ በራሱ ፍቃድ ግልብጥ ብሎ ወጣ ጨዋታ’ ይኽውላችሁ።
ከሥር ያለው ትርጉም የአማርኛው ነው። በአፋን’ኦሮሞ የወጣው የማዘዣ ደብዳቤ ከስር አለ። እንዲህ #እንዲነግሱ የወጣህበትን ሰልፍ፣እንዴት ነው በምርጫ የምትጥላቸው?
ቀን 22/52013
ማስታወቂያ
ለባቱ የመሰናዶ ት/ቤት መምህራንና ሠራተኞች በሙሉ
ጉዳዩ:- የድጋፍ ሰልፍ እንድትወጡ ማሣወቅን ይመለከታል
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በባቱ ከተማ ጁንታን ለማውገዝ በ26/5/2013 ከጠዋቱ 1 ሰአት ጀምሮ  በሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ እናንተም ተገኝታችሁ እንድታወግዙ በማክበር እናሳውቃለን
ከሰላምታ ጋር
ማሳሰቢያ : ማንኛውም መምህርና ሰራተኛ ከሰልፉ ላይ ያለመገኘትም ሆነ ፍቃድ መጠየቅ የማይቻል መሆኑን እያስገነዘብን ቀድማችሁ እንድትዘጋጁበት እያሳወቅን በኋላ ለሚፈጠረው ችግር ትምህርት ቤቱ ተጠያቂ እንደማይሆን በድጋሚ እናሳውቃለን
Filed in: Amharic