የባርነት ተሸካሚዎች፡- ኢዜማ ወ ብአዴን….!!!
ሸንቁጥ አየለ
“…ኢዜማዎች የአማራ ህዝብ ሞትኩ ማለቱን እንደ ዘረኝነት እየቆጠራችሁ አማራ ላየ የዘር ፍጅት ካደረጉ ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ጋር ህብረት የፈጠራችሁ የባርነት ሀሳብ ተሸካሚዎች—-“
ኢዜማ የሚባሉት ብርሃኑ ነጋ ጠፍጥፎ የሰራቸዉ ጉግ ማንጉጎች አማራን እና ኦርቶዶክስን 70 አመታት ካረደዉ ኦነግ ጋር ግንባር ፈጥረዋል። የኦነግ/ኦህዴድን አጠቃላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል በፓርቲ ደርጃ ክደዋል።የኢትዮጵያ ህዝብም በአማራ የዘር ፍጅት ላይ ክህደት እንዲያደርግ ሰርተዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃም ሰልፍ አስተባብረዉ አማራም ሆነ ኦርቶዶክስ አልታረደም ብለዋል። ለነጭ ለጥቁሩ ጮህዋል። የኦነግ/ኦህዴድ የወንጀል አተላ ደፊ ሆነዋል። እነዚህ የባርነት አስተሳሰብ ተሸካሚ የኢዜማ ሰዎች ሁለተኛ ተልዕኳቸዉ ደግሞ አንድ ግለሰብ ወይም አንድ ድርጅትበኢትዮጵያዊነት ወይም በአማራነት ተደራጅቶ በአማራ ወይም በተዋህዶ ላይ የሚደረገዉን የዘር ፍጅት ሲቃወም ዘረኛ ነህ ብሄረተኛ ነህ ብለዉ ይከሱታል።
ዛሬ አንድ የተማርኩ ነኝ የሚል የኢዜማ ሰዉ መልዕክት ላከልኝ “ኢትዮጵያን እወዳለሁ እያልክ ለምን አማራ ተጨፈጨፈ እያልክ ልዩነትን ታሰፋለህ?” ብሎ ሜሴንጀር ላይ ላከልኝ። መጀመሪያ ተናደድኩ። እንደገና ቁጭ ብዬ አሰብኩ። በሶስት ወራት ብቻ 700 መቶ ሽህ ህዝብ ከወለጋና ከመተከል ብቻ ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ ስለፈሰሰዉ ህዝብ አትናገሩለት እንዴት ይባላል?
ለግማሽ ቀን ዉስጤ እሳተ ገሞራ ይፈላል። የመስሪያ ቤት ስብሰባ ላይ ቁጭ ብዬ ስለዚህ አይነት ሰዎች ነበር የማስበዉ። የራሴን ፕሮጀክት እያቀረብኩ የስሜተ ከፍታ ድምጼ ዉስጥ ለራሴ ይታወቀኛል።
ለዚህ አይነት ተኮላ እና ተንኮለኛ ጸረ ህዝብ ተጠይቃዊ መልስ አይገባዉም። ምን መመለስ አለብኝ?
ዝም ብዬ ለሌሎች ባለጌዎች የምሰጠዉን መልስ እንዳልመልስለት ይሄ ሰዉ ከ15 አመታት በላይ አወቀዋለሁ። ባንድ ወቅት ስለ ኢትዮጵያ ብዙ መክረናል። ግን ምንድን ነዉ የብርሃኑ ነጋ ስብከት እንዲህ ህዝቡን ጀሌ ያደረገዉ? ማንሰላሰል ቀጥያለሁ።
እሱ ግን መልሴ ቢዘገይበት ነዉ መሰለኝ ድጋሚ
” መልስህን እየጠበቅሁ ነዉ ” ብሎኝ ቁጭ። አሁን መልስ ሰጠሁት ። ” አንተ የባርነት አስተሳሰብ ቀንበር ዉስጥ ስለገባህ ምን እየተከናወነ እንደሆነ አይገባህም። ልክ እንደ ብአዴን ጀሌዎችቸያሰብክ ያለህዉ ጭንቅላትህን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠህ ነዉ። የብአዴን የባርነት ተሸካሚዎች 700 መቶ ህሽ. አማራ ከመተከል እና ወለጋ በሶስት ወር ዉስጥ ተፈናቅሎ ለሞት ተዳርጎ በአቢይ ትዛዝ አማራ ላይ ሞት ተበይኖበት እያስተዋሉ ብልጽግና መብራት ነዉ ለማለት የማይቀፋቸዉ ናቸዉ።
እናንተ ኢዜማዎችም የአማራ ህዝብ ሞትኩ ማለቱን እንደ ዘረኝነት እየቆጠራችሁ አማራ ላየ የዘር ፍጅት ካደረጉ ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ጋር ህብረት የፈጠራችሁ የባርነት ሀሳብ ተሸካሚ ናችሁ” ስል መለስኩ። ግን አልረካሁም።
ብዕር ምን ጉልበት አለዉ? ህዝብህን ከመታረድ የማያድን ብዕር ይቃጠል። እንደነዚህ አይነት ሽኮኮዎች ጋር አብሮ ኢትዮጵያዊ ተብሎ መጠራትን አበጥሮ የማያቃጥል ብዕር እራሱ ይቃጠል።
ኢትዮጵያዊ ሁሉ በእግዚአብሄር አንደበት በመጽሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ልጅ ተብሎ ሳለ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊን እንዲያርደዉ የሚሰሩ፡ የሚተባበሩ፡ ከአራጅ ጋር ቆመዉ የሚታረደዉ ህዝብ እንዳይጮህ ዘረኛ ብለዉ ሀገራዊ ኑፋቄ የሚሰሩትን ሰብስቦ ማቃጠል የማይችል ብዕር እራሱ ይቃጠል።
እኔ ቸኩዬ እንጂ የኢትዮጵያ አምላክ ይሄን ሁሉ የባርነት ሀሳብ ተሸካሚ ወንጀለኛ ያለ ብዕርም ያለ ጦርም ሰብስቦ እና ስሩን ነቅሎ ከቅድስት ኢትዮጵያ ምድር ላይ አቃጥሎ ያጠፋዋል።
—————————— ————————
————–
ኢዜማ ዉስጥ የተሰገሰጉ የባርነት አስተሳሰብ ተሸካሚዎች ታክቲክ:- የዘር ፍጅት የሚደረግበት ስለ መብቱ ሲጮህ ዘረኛ ብሎ መክሰስ ። ከዘር ፍጅት ፈጻሚዉ እና አራጁ ጋር ግን ቆሞ መዘመር !
————‘—————-
የባርነት ተሸካሚዉ ብአዴን በሶስት ወር ብቻ ከ700 መቶ በላይ እወክለዋለሁ የሚለዉ ህዝብ ከወለጋ እና መተከል ተጨፍጭፎ ተፈናቅሎ ለሞት ተዳርጎ ተበትኖ ሳለ ከአራጁ ኦህዴድ/ኦህዴድ ጋር ቆሞ እኛ ብልጽግናዎች መብራት ነን አምፖል ነን ለማለት አለማፈር