>

ሁላችንም ልንጮህ ይገባል!! (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

ሁላችንም ልንጮህ ይገባል!!

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ


ከፍጥረታት ዓለም የመጀመሪያው የሀሰት አባት ሳይጣን እንደሆነ መፅሀፍት ያስረዳናል፡፡ ስለሆነም ንፁሀንን ሰዎች በሀሰት መወንጀል የሳይጣን የግብር ልጆች ያደርገናል እንጅ እውነት ጊዜዋን ጠብቃ ትወጣለች፡፡ እኛ ግን እንደ ሰው ኢ-ፍትሀዊ ድርጊቶችን ልናወግዝ እና ልንቃወም ይገባል፡፡ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ እውነት ስትቀጭጭ እያየን ዝም ማለት እንደ ህዝብ መውጫ ወደሌለው መቀመቅ ይዞን ይገባል እንጅ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡ እኛ እንደ ሰው ሙሉ የምንሆነው ከእውነት ጋር ተገምደን ስንቆም ብቻ ነው፡፡

እስክንድር ነጋ ለከፈለው እና እየከፈለ ላለው ዋጋ ክብር ልንሰጠው ይገባል፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ በሚደርሰው ግፍ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁላችንም ልንጮህ ይገባል፡፡ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣አስቴር ስዬም እና አስካለ ደምሌ የህሌና እስረኞች ሲሆኑ ድምፅ ልንሆናቸው ይገባል፡፡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የእምነት አባቶች፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እስክንድር እና ጓዶቹ  የተከሰሱበትን መሰረተ ቢስ ምክንያት ልናወግዘው ይገባል፡፡ ህሌናችን ካልዶመዶመ በቀር እውነትን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ሰው ለተፈጠረበት አላማ ሲኖር እውነትን ያውቃልና፡፡ ዋጋ የሚያስከፍል ነገር እንኳን ቢሆን ዋጋ መክፈል ይኖርብናል እንጅ እውነትን ልንሸቅጣት አይገባም፡፡ ስለዚህ ሁላችንም የእውነት አበጋዞች ሁነን ድምፅ ለሚሹ ወገኖቻችን ድምፅ እንሁን፡፡

Filed in: Amharic