>

የዲባቶ አምባቸው ፋውንዴሽን፤ አሁን ለምን? (መስፍን አረጋ)

የዲባቶ አምባቸው ፋውንዴሽን፤ አሁን ለምን?

መስፍን አረጋ


 የሰሞኑ ትኩስ ጉዳይ የዲባቶ (ዶክተር) አምባቸው ፋውንዴሽን ነው፡፡  ሌሎቹን ሁሉን ጥያቄወች ወደጎን በመተው፣ የፋውንሽኑ ምሥረታ ቢያንስ ቢያንስ ወቅቱን የጠበቀ አይደለም ማለት ይቻላል፡፡  ዐብይ አህመድ የፋውንዴሽኑ ጉዳይ ባሁኑ ጊዜ በሰፈው እንዲናፈስለት የፈለገው፣ በሱ በራሱ ዋና አቀናባሪነት ባሕርዳር ላይ የደረሰው የሰኔ 15ቱ ያማራ ቁስል እንዲያመረቅዝ ለማድረግ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ከወያኔ መወገድ በኋላ ያማራ ክልል አመራሮች በተወሰነ ደረጃ ተጠናክረው ኦሮሙማን መገዳደር በመጀመራቸው፣ የባሕርዳሩን ጭፍጨፋ እያስታወሱ እንዲሸማቀቁና በጎጥ እንዲከፋፈሉ መደረግ አለባቸው፡፡  

ጊዜው ጦቢያን ሊቆረጣጥማማት ባሰፈሰፈው በኦሮሙማ ጅብ ላይ ሙሉ ትኩረት አድርጎ፣ የሞት ሽረት ትግል የሚደረግበት እንጅ፣ ያለፈውን ቁስል እያስታወሱ የሚወቃቀሱበት አይደለም፡፡  ስለዚህም የዲባቶ አምባቸውን ፋውንዴሽን ጉዳይ ያለወቅቱ የሚያናፍሱ ግለሰቦች፣ አውቀውም ሆነ ባለማወቅ የጦቢያውያንን ትኩረት እየበታተኑ፣ በዚህም ደግሞ የኦሮሙማን አጀንዳ ለማሳካት የበኩላቸውን እያገዙ መሆናቸውን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡  የዲባቶ አምባቸው ፋውንዴሽን ጉዳይ ሲደርስ ይደርሳል፡፡  መጀመርያ የቂጤን ብላለች ብልጢት፡፡    

EMAIL; mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic