>
5:26 pm - Wednesday September 17, 4549

"ሱዳን ከወረረችው የኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ እንድትወጣ እንጠይቃለን"  (በአሜሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት)

“ሱዳን ከወረረችው የኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ እንድትወጣ እንጠይቃለን”

በአሜሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት 

ባሕር ዳር፡ የካቲት 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ፤ በአሜሪካ በሁሉም ግዛቶች ከሚገኙ ከ800 በላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የሃይማኖት አባቶች፣ የአደረጃጀት ተወካዮች፣ ምሁራንና ሌሎች አካላት በተገኙበት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በበይነ መረብ ስብሰባ በማካሄድ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫቸውም በውጭ የሚኖሩ የጽንፈኛው ትህነግ ቡድን ደጋፊዎች በማኅበራዊና በመደበኛ ሚዲያ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን፣ የውጭ መንግሥታትንና የዓለም አቀፍ ተቋማትን ለማሳሳት በትግራይ ሕዝብ ስም የሚያካሂዱትን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እናወግዛለን፤ ይህንን በብቃት ለመመከከት በተደራጀ መንገድ እንሰራለን ብለዋል።
በትግራይ ክልል እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈናቀሉ እና አስቸኳይ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች  እንዲቋቋሙ በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር በተያያዘ ከየትኛውም ወገን የሚነዛውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ አጥብቀው እንደሚያወግዙና ለግድቡ ግንባታ ፍፃሜ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
ሱዳን ከወረረችው የኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ እንድትወጣ በመግለጫቸው መጠየቃቸውን  ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Filed in: Amharic