>

ምን አይነት ጉዶች ናቸው ግን? (ጌታቸው ሽፈራው)

ምን አይነት ጉዶች ናቸው ግን?

ጌታቸው ሽፈራው


*…. በሚዲያቸው “እንበር ተጋዳላይ” ጎዳና ላይ “እንበር ተንከባላይ” ሆነው ከረሙ…!!!
* በቴሌቪዥን ግፋ በለው ጦርነቱ ብለው ይቀሰቅሳሉ፣ በቲውተር  ደግሞ ያለ የሌለ የነጭ ስም እየጠሩ ኧረ  እባካችሁ የኢትዮጵያ መንግስት  ጦርነቱን እንዲያቆም  ግፊት አድርጉልን ይላሉ።
 
~”ጦርነት ባሕላዊ ጨዋታችን ነው።” ብለው ሲደነፉ ከረሙ፣  ጦርነቱ ሲጀመር የሴቶችን የባሕል ልብስ ለብሰው ያመለጡት አመለጡ። እንዲህም ሆኖ በየቀኑ ማረክን፣ አንበረከክን እያሉ “የተጋዳላይ” ተመሳሳይ ድምፅ እየቀረፁ ዜና ይሰራሉ። ቲውተር ላይ ደግሞ የተከፈተብን ጦርነት ይቁም እያሉ ያለቃቅሳሉ።  በቴሌቪዥን ግፋ በለው ጦርነቱ ብለው ይቀሰቅሳሉ፣ በቲውተር  ደግሞ ያለ የሌለ የነጭ ስም እየጠሩ ኧረ  እባካችሁ የኢትዮጵያ መንግስት  ጦርነቱን እንዲያቆም  ግፊት አድርጉልን ይላሉ። በሚዲያቸው “እንበር ተጋዳላይ” ጎዳና ላይ “እንበር ተንከባላይ” ሆነው ከረሙ።
~ራሳቸው መብረቃዊ ጥቃት አደረግን ብለው የጀመሩትን ጥቃት፣ እያሸነፍን ነው እያሉት የከረሙትን ጦርነት፣ መልሰው ደግሞ ኢትዮጵያ የሀይማኖት አባት የላትም፣ በትግራይ ላይ ጦርነት ሲታወጅ ዝም አሉ ብለው ሲዘልፏቸው ይውላሉ። ትናንት መቀሌ ሲሄዱ “ለምን ይሄዱብናል፣ እንዳትቀበሉ።” ብለው ቅስቀሳ አደረጉ። በእርግጥ  እነዚህ ሽማግሌዎች ድሮም ጦርነት እንዳይነሳ ወደ ትግራይ ሄደው ነበር።  አዋርደው መለሷቸው።  ጦርነቱ ተጀመረ። የሆነው ከሆነ በኋላ ሽማግሌ የለም አሉ። ትናንት ሲሄዱ አንፈልግም ብለው እየዘለፏቸው ነው። ከጦርነቱ በፊት ሽማግሌ ዘለፋ፣ ጦርነቱ ሲጀምር ዝም አሉ ተብሎ ዘለፋ፣ አሁን ሄዱብን ብለው ዘለፋ።
~ሕዝባችን ተራበ ብለው በጦር ሜዳ ያጡትን ድል በማሕበራዊ ሚዲያ ተገጠሙት። ያው ጦር ሜዳ ላይ ውሸት አያድንም። “ገጥመናል ገጥመናል” ብሎ ፊት ለፊት ነው የሚመጣው። ልብስህን በቀሚስ ቀየርከው፣ የወቶአደር ልብስህን በቲጃማ ለውጠህ ለበስክ፣ አውልቀኸው እንደ እብድ ሮጥክ አይለቅህም። ለዛ ነው የቄስ፣ የመነኩሴ፣ የሴት ልብስ ለብሰው  ያልዳኑት። ጦርነት ላይ ለመዋሸት ጊዜም የለህም። ዋሽተህም አታመልጣትም። ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ግን ተያያዙት። አሁን ወገኖቻችን ተራቡብን ብለው እነ ታማኝ  እርዳታ ሲያሰባስቡ “አንፈልግም።” ኧረ የጉድ ሀገር። አንተ ነህ እንዴ የተራብከው? ተራቡ፣ እየሞቱ ነው ብለሃል? እና እውነት ከሆነ በፀሎት ልታድናቸው ነው? በመንከባለል ልትታደጋቸው ነው? ቲውተር መድሃኒትና አልሚ ምግብ ይሆናል? ሀሽ ታግ ጉርሻ ይሆናል?  ብዙው ነገር ለፕሮፖጋንዳ ባይሆን እንዲህ ሲጮሁበት ለነበረው መልስ ሲሰጥ መልሰው አይቃወሙትም ነበር። አብዛኛው ነገር በጦር ሜዳው ቀሚስ ለበሰው ያላመለጡበትን ድል በፕሮፖጋንዳው  ለማግኘት ነው።
ደግሞ ሰሞኑን የትህነግ ጫጩት በሆኑት ሶስት ፓርቲዎች ስም መግለጫ ሲበትኑ ነበር። የእነዚህን ጫጩት ፓርቲዎች ቀርቶ በትህነግ ስም መግለጫ አውጥተው የሚበትኑትኮ የዳያስፖራ ፕሮፖጋንዲስቶች ናቸው። እና ምን አሉ። “3 ነጥብ 8 ሚሊዮን  የትግራይ እንሰሳት በጦርነቱ ምክንያት ታርደዋል።” ኧረ የፈጣሪ ያለህ!! በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግራይ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ሰንጋ እየላከ አስገደለን ይላሉ። ይህ ሁሉ ሰንጋ ተላከ እያሉ በሌላ በኩል ደግሞ ትግራይ ውስጥ ስለመኖሩ የማይታወቅ የቀንድ ከብት ታረደብን እያሉ መግለጫ ይሰጣሉ። ቀንድ ያወጣ ውሸት ማለት ይሄ ነውኮ።  በጦር ሜዳ ቀንድ ቀንዱን ሲባል የሌለ የቀንድ ከብት ቆጠራ ውስጥ ገባ። ዶሮ ረስታችኋል በልልኝማ ማን ነህ አንተ!
50 ሺህ ያህል ወታደር ዘምቶብናል ነው የሚሉት። ይህ ሁሉ ለመቁጠር የሚታክት ሰንጋ ከታረደባቸው ባለፉት 90 ቀናት እያንዳንዱ ወታደር ታዲያ   በአማካይ 7 ሺህ ሰንጋ አርዶ በልቷል በእነሱ ስሌት።  ሌሎቹ መቶ ሽህ ዘመተብን ስለሚሉ ለእያንዳንዱ 3500 ደረሰው ማለት ነው። ወታደሩን ሰው ገደለብን ነው ሰንጋ አረደብን ብለው ነው እየከሰሱት ያሉት ግን? በአንድ በኩል ወታደሩ በየገጠሩ ሰው ፈጀ ይላሉ፣ ይህን ያህል ሰንጋ እያረደ ከሆነማ ከዳስ ሊወጣ አይችልምኮ። ነው ያችው ዩናይትድ አረብ ኢሜሬትስም በድሮን እየጫነች ወሰደችው?
 
ይህም ጥጋብ አልፎ ወደ ጥርስ ማፋጨት ተደርሷል
Filed in: Amharic