>

የ EBS ነገር…  ?!? (ዘመድኩን በቀለ)

የ EBS ነገር…  ?!?

ዘመድኩን በቀለ

… መቼም የዕለት አጀንዳ አናጣም። በትግራይ 4ነጥብ 5 ሚልዮን ህዝብ ተርቦ፣ በሰሜን ጎንደር በኩል ሱዳን ለጦርነት ድንበር ጥሳ ገብታ፣ ጎጃም በረሃብና በስደተኞች ተጥለቅልቃ፣ ኦነግ ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ጦርነት ገጥሞ፣ ረሃብ፣ እሳት እየፈጀን፣ በሽታ ወረርሽኝ እየቀጣን በዚህ ላይ ነው እንግዲህ አሁን ደግሞ ይሄ ነውረኛ ፀረ ኦርቶዶክስ የሆነ የፕሮ ጣቢያ ሌላ አስቀያሽ አጀንዳ እንካችሁ ተነታረኩበት ብሎ ጀባ ያለን። ይሄን በቶሎ ዘግተን ወደ ዋናው ጣቢያ በቶሎ እንመለስ።
… መጀመሪያ “ከጆሲ ኢንዘሃውስ” የቴሌቭዥን መዝናኛ መርሃ ግብር አዘጋጅ ከጆሲ ጋር ተጣሉ። ጆሲ ደግሞ በጌታ እናት በእመቤታችን ድንግል ማርያም ድርድር ብሎ ነገር አያውቅም። በቢሮው ከጀርባው ምስለ ፍቁር ወልዳን አስቀምጦ የሚሠራ ባለማዕተብ ምርጥ የተዋሕዶ ልጅ ነው ጆሲ ( ዮሴፍ ገብሬ)። በአሻባሪዎች ምክንያት በሊቢያ የታረዱትን ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጆችን በተመለከተ በሠራው አመርቂ ሥራ ምክንያት ፕሮቴስታንቶቹ ኤርትራውያን የጣቢያው ባለቤቶች ሄፕ አሉበት። ልጁን ሰቅዘውም ያዙት። ጠመዱትም። ልጁን በማስታወቂያ ስፖንሰር በሚያገኘው ገቢም ጉዳይ ታጋተቱት። በመጨረሻም ተፋታቸው። ተለያዩ።
… ሲጀመር ኢቢኤስ ተቀማጭነቱን በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላን በሃገረ አሜሪካ ያደረገ ባለቤቶቹ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ በኤርትራዊ ዜግነት ምክንያት ለሃገር አደጋ ያመጣሉ ተብለው የተባረሩ ኤርትራዊያን ናቸው ይላሉ። ኋላ ላይ ኤርትራዊው የጣቢያው ባለቤት በዐማራ የትግራይ ተወካዩ ኤርትራዊው አይተ በረከት ስምኦን ኤርትራዊውን የሃገራቸውን ልጅ ከሕግ አግባብ ውጪ አስመጥተው በወቅቱ በኃይልኛ ጠብ ላይ የበነበረን የጎረቤት ሃገር ዜጋ በኢትዮጵያ ወሳኝ የሚዲያ ሥራ ላይ እንዲሠማራ አደረጉ። በወቅቱ ኢሳትን በሚልዮን ዶላር ከአየር እያስወረዱ ኢቢኤስን ግን በአየሩ ላይ እንዲናኝ አረጉት። (አቶ በረከት ስምኦን) ይላሉ ተቺዎች።
… የኢቢኤስ ባለቤቶች በግል የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ናቸውም ይላሉ ከኢቢኤስ በሃይማኖት ጉዳይ ተጣልተው የሚወጡ ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጆች። ካሜራ ፊት መቆም ከፈለክ ማዕተብህን በጥስ የድርጅቱ መመሪያም ነው። “የጣቢያው ባለቤት አቶ አማኑኤል” በፀረ ኦርቶዶክስ አቋማቸውም ይታወቃሉ ይሏቸዋል። ጣቢያው ገና ሲጀመር በጠዋቱ ተሃድሶዎቹንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማፍረስ የበግ ለምድ ለብሰው የመጡትን እነ በጋሻው ደሳለኝን “ታኦሎጎስ”፣ እነ አሰግድ ተስፋዬን “ቃለ ዐዋዲ” በሚል ፕሮግራም ሌሎችንም ከአቶ ፀጋዬ ደበላ ፀጋዬ ሮቶ የሮዳስ ቀለም ፋብሪካ ባለቤት ጋር በመተባበር በኦርቶዶክስ ላይ ግልጽ ዘመቻም የከፈተ ነው EBS ማለት። እነዘርፌን፣ እነ ትዝታውን ፈትቶ የለቀቀብን አውሬ ጣቢያ ነው። መቼም ለኦርቶዶክስ ያለው ንቀት አይጣል ነው። ድብቅ ሴራውም ዛሬ የተጀመረ አይደለም።
… EBS የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶንና እንደ ሃገር ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ለማቀንጨር፣ ራዕይ የሌላቸው ነውረኛ እንዲሆኑ፣ ብልጭልጭ ስድአደግ እንዲሆኑ፣ ባህሉን የማይጠብቅ አለሌ፣ ሃሞቱ የፈሰሰ፣ ነውር የነውር ጥግ የሚባሉ የኢትዮጵያውያንን የባህል አሴቶች በድማሚት አፍርሶ ትውልዱን ልቅ ለማድረግ የአውሬው መንገድ ጠራጊ ሆኖ የመጣ የተላከ ጣቢያም ነው። ብዙ ጊዜ ተመክሮ ተዘልፎ ለመሰበር የተዘጋጀ ነውረኛ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ተዋሕዶ የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው። ቃና ከሚባል የቱርክ የባህል ወረራ አስፋፊ፣ ነውር ቸርቻሪ፣ ግድያ፣ የህጻናት መሰወር አስተማሪ ጣቢያ ጋር የሚሠራ አፍራሽ ጣቢያ ነው ጣቢያው። (አቤት ሙስሊሞችን ሲፈራ፣ ሲያከብር ለጉድ ነው። ሲጀመር እስላም አይቀጥርም። ካልቀጠረ ደግሞ ሂጃብ አውልቂ ብሎ አይጋተትም። የሚከተለውን ያውቃላ።) ሂኢ…
… ጣቢያው ውስጥ ከሚሠሩ ባለሙያዎች መካከል አንተነህ ብርሃኑ የሚባል ባለማዕተብ የካሜራ ባለሙያ አውቃለሁ። ሁልጊዜ ማዕተቡን እንዳሠረ ነው በፌስቡክ የማየው። አስፋው መሸሻም የእናቴ አባት አያቴና የአባቱ አባት አቶ አስፋው አብረው ሐረርጌን ያቀኑ ዘመዴ ነው። ከጥብቅ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ የተወለደው አስፋው መሸሻ አሁን ሃይማኖቱ ምን ይሁን ምን አላውቅም። የማዕተብ ማሰርና መፍታትም ጉዳይ ይጨንቀዋል ብዬ ግን አላስብም። አላውቅም ግን።
… ጣቢያው ነውሩን ዛሬ አይደለም የጀመረው። ሴቶች እህቶቻችንን እንደ በግ ደርድሮ በቴሌቭዥን ወንዶችን እያስመረጠ፣ ምራጯን ሴት የሆቴል አልጋ እየፈከለ፣ ወይን እያጠጣ አስክሮ ዘመናዊ የወሲብ፣ ንግድ፣ ልቅ ዝሙት በኢትዮጵያውያን ጭንቅላት ውስጥ በግልጽ በአደባባይ አይተ በረከትን ተማምኖ የዘራ፣ ነውረኛ ቅሌታም ጣቢያ ነው። ለምዕራባውያኑ ባህል ለእኛ ግን ስድ የሆነ ባህል እንደወረደ አምጥቶ በላያችን ላይ ልዘፍዝፍ ያለም አሁንም ወጣቱን ዳንሰኛ ዝሙታም በማድረግ ላይ ያለ አውሬ ጣቢያ ነው። ነገርኳችሁ በፌርኮስሞ ያበዱ ፊኒሺንጉ ያላማረ የሃብታም ቤት የሚመስሉ ቫምፓይር ሴቶችን እንደበግ ደርድሮ ዳሌና ትከሻ እያስገመተ ለዝሙት የሚሸጥ ነውረኛ ጣቢያ ነው። የበግተራ ፕሮግራሙን በስንት ጩኸት አቁሞ እንደነበርም አስታውሳለሁ። ጣቢያው የአውሬው መንገድ ጠራጊ ደንበኛ ፀረ ኢትዮጵያ የጎረቤት ሃገር ጣቢያ ነው ይላሉ ውስጥ አዋቂዎቹ።
… የቫላንታይን ዕለት የሚባል የዝሙት ቀን በኢትዮጵያ ጮሆ እንዲስፋፋ ያደረገ፣ ከጣሪያ በላይ እያጮኸ ኢትዮጵያውያን ህጻናትን በቫለንታይን ሰበብ ከክብር ያሳነሰ፣ በዝሙት ጉጉት በጥማት እንዲቃጠሉ ያደረገ ትውልድ ገዳይ ጣቢያ ነው። ጣቢያው ወጣቶችን ማዕከል አድርጎ የሚቀረጽ፣ የሃይማኖት ምልክትም ማየት የማይፈልግ፣ ሂጃብሽን አውልቂ፣ ማዕተብሽን በጥሽ፣ ፕሮቴስታንት ምሰይ፣ ምሰል ብቻ የሚል ነውረኛ የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው።
… ከዚህ ቀደም ጋዜጠኛ ሰላማዊት ደጀኔ የምትባል ጋዜጠኛ ማዕተብሽን አውልቂ የሚሏትን ነገር መቋቋም አቅቷት በዚያ ምክንያት ሥራዋን መልቀቋን ነግራን እንደነበር ይታወሳል። ልጅቷ ማዕተቧን ስትበጥስ ከርማ ፀፀቱ ሲገድላት ለምን ጥንቅር ብሎ አይቀርም። ባይበላስ ቢቀር ብላ የፕሮቴስታንት ድርጅት አባል የሆነውን ጣቢያ ለቅቃ ለምኜ ብበላስ በማለት መውጣቷን የምናስታውሰው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ጣቢያው “እምነት የግል ነው ሃገር የጋራ ነው” የሚለውን መርህ የጣሰ ድርጊት ነው የሚፈጽመው። ይሄ ባለቤቱ የጎረቤት ሃገር የውጭ ዜጋ የሆነ ጣቢያ ገና ብዙ ነውረኛ ተአምር ያሳየናል።
… ትናንት ደግሞ አንጋፋዋን ተዋናይት እና የቴሌቭዥን ፕሮግራም መሪ ባለማዕተቧን ሃና ዮሐንስን ኤርትራዊው የፕሮቴስታንት አማኝ ጣቢያ ማዕተብሽን በጥሺ በማለት አካኪ ዘራፍ ሲል ቆይቶ ልጅቷ ጥንቅር በል፤ ማዕተቤንማ አልበጥስም በማለቷ ምክንያት እንደተለያዩ ይፋ አድርጋለች። እስከዛሬ ለሚነሡበት ተቃውሞዎች ምንም ዓይነት ምላሽ የማይሰጠው ኢቢኤስ( ማንን ፈርቶ ይሰጣል? በፊት በበረከት ስምኦን አሁን በፕሮነቱ በዐቢይ አሕመድ ይተማመናል። ማንን ፈርቶ? እኛ እንደሆነ እኛው ነን። በዚህ በኩል ሙስሊሞቹ ኦኦ።) ትናንት ግን የግዱን ጣቢያውም ለተነሣበት ጥያቄ የማይመስል መልስ ሰጥቶ ዙሪያ ዙሪያውን ሲሽከረከር ከዋለ በኋላ አኞ የሆነ አዛ መግለጫ ቢጤም አውጥቶ ሊሸወደን ሲሞክር ውላል።
… በመጀመሪያ አርቲስት ዮሴፍ ገብሬ ( ጆሲ ኢንዘ ሃውስን ) በሃይማኖቱ ምክንያት አሳባው ተጣሉት። ዝም አልናቸው። ቀጥለው ሰላማዊት ደጀኔን ማዕተብሽን በጥሺ አሏት። እምቢዮ ስትላቸው ኤርትራውያኑ ኢቢኤሶች በይ ንኪው ብለው አባረሯት። አሁንም ዝም አልናቸው። በመሃል በአንዲት ማዕተቧን ባስበጠሷት እና ለሆዷ ስትል በጣቢያው በምትሠራ ምስኪን ጋዜጠኛ አማካኝነት ( ከእውቀት ማነስ) ምስጢረ ሥጋዌን በማይገባ መንገድ በመግለጿ ምክንያት በእመቤታችን ላይ የተላለፈን ፅርፈት አስተካክሉ ሲባል እምቢዮ ብሎ በስንት ሽማግሌ ውትወታ በመምህር ዘበነ አማካኝነት ጣቢያው ሳይሆን ሠራተኞቹ በይፋ ይቅርታ ብለው ለማለፍ ሞከሩ። አሁን ደግሞ በሃና ዮሐንስ ለከት የለሽ ድፍረታቸውን አስታወኩብን፣ ቅርሻታቸውንም አቀረሹብን።
… ለነገሩ እነሱ ምን ያድርጉ? የጣቢያው ደንበኞች እንደሆነ እኛው ባለ ማዕተቦቹ ነን። ተዘፍዝፈን ስናያቸው የምንኖር እኛው ነን። ዝሙቱን፣ ነውሩን ንቀቱን የሚግቱን እኛኑ ነው። እንደ ሙስሊሞቹ ዲኔ ተነካ የማንል፣ ሃይማኖታችንን ለማስከበር ወኔም ኅብረትም የሌለን። ልፍስፍስ ሃሞተ ቢስ፣ የመጣ ሁሉ በዓይናችንም፣ በጆሮአችንም ላይ የሚጸዳዳብን፣ ክብር አጥተን ክብራችንን በፈቃደኝነት የሸጥን፣ እኛው እኮ ነን ቴሌቭዥን ብርቁዎች። ሳንጠየቅ አቤት፣ ሳንላክ ወዴት የምንል። እናም EBS ምን ያድርግ? መንጋ ጎጋ ሲያገኝ፣ ምን ያድርግ? ገና ጉድ ያሳየናል።
… ኢቤኤስ በመግለጫው በፊትም አስወልቃለሁ፣ አሁንም አስወልቃለሁ፣ ወደፊትም ማስወለቄን አጠንክሬ እገፋበታለሁ። ምንአባክ ታመጫላቹ ነው በተዘዋዋሪ ያለው። ደብዳቤው ከታች ተያይዟል።
… ምን እናድርግ? መፍትሄውስ?
እዚህ ላይ ነው መነጋገር ያለብን። “ሲኖዶሱ” እንዳንል እሱን እንዝለለው። ሲኖዶሱን አንረብሸው። ተከብረው የሚያስከብሩን አባቶች እስኪፈጠሩ ድረስ ሲኖዶሱን አንቀስቅሰው። ለመንጋው ክብር የሚጨነቅ እረኛ እስኪነሣ ድረስ ጮጋ እንበል። ስንትና ስንት ጉዳይ ዝም ያለን አካል ለማዕተብ ጉዳይ ጆሮ ይሰጠናል ብለን አናስብ። ማኅበራትም ንግድ ላይ ናቸው። ይሄን ጉዳይ እንደቀላል ነው የሚቆጥሩት። ማዕተብክን ካልበጠስክ እንጀራ መብላት አትችልም በሚለውና ማዕተብክን ካልበጠስክ አንገትህን ነው የምቆርጠው በሚለው መሃል ልዩነቱ እኮ” EBS ዘግይቶ ይገድልሃል። ያኛው በሰከንድ ቆርጦ ይገላግልሃል።” ኢቢኤስ የተዋሕዶ ልጆች አራጅ ነው። ኢቢኤስ የሚሠሩ ማዕተባቸውን በጥሰው የሚሠሩት ሆዳም ጋዜጠኞችም ያው ከሃዲ መናፍቅ ናቸው።
… በቀደም ሰሞኑን መምህር ዘበነ ለማ ሽማግሌ ሆኖ ያስታረቃት ልጅ ስትናገር እንዲህ ስትል ሰማኋት። “እርስዎ አለች። እርስዎ እኮ ረስተውኝ እንጂ አሜሪካ ሆነው በየቀኑ ምሽት ምሽት እየደወሉ ብቻዬን ያስተምሩኝ፣ ያጽናኑኝም የነበሩ ነዎት አለችው።” በሃገረ ስብከት ደብዳቤ፣ በሚሊዮን የስልክ ጥሪ የማይገኙትን መምህራችንን መምህር ዘበነ ለማን ጋዜጠኛዋ እንዲያ አለቻቸው። “በVIP” በስልክ ያስተምሯት ነበር ማለት ነው። የሆነው ሆኖ የመምህር ዘበነ ለማዋ ተማሪት ጋዜጠኛ በአንገቷ ላይ ማዕተብ የላትም። ክዳ ነው የምትገባው። ማዕተቧን በጥሳ ነው የምትገባው። ደግሞ እኮ የሰንበት ተማሪ ነኝም ባይ ናት። እናም የሆነ ቀን ሲደብራት ማዕተቤን አውልቂ አሉኝ እያለች ትለፋደድብንም ይሆናል። እንደ ሃና አላወልቅም ብሎ ውልቅ ማለት ነው እንጂ የምን ከደበሯት በኋላ ስትባረር እየዬ ማለት ነው። ያኔ እዬዬ ብትል እኔ በበኩሌ አልሰማትም። ( ነፍሰ ጡሯ ማዕተብሽን አጥብቂ፣ አጥልቂ፣ እሠሪም።”
… ኢቢኤስን ከቻናላችሁ ላይ መደለት፣ ዩቲዩብ አንሰብስክራይብ ማድረግ፣ ወዘተ እሱ አንዱ አማራጭ ቢሆንም መፍትሄው ግን ሌላ ነው። እንደሚታወቀው የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ቀጥ ብለው የሚቆሙት በስፖንሰርና በማስታወቂያ ገቢ፣ በዩቱዩብም ሽቀላ ነው። እናም አሁን ያለው አማራጭ ሌሎቹን ዘዴዎች መጠቀሙ እንዳለ ሆኖ በኢቢኤስ ላይ ማስታወቂያ የሚያስነግሩ ድርጅቶችን በመጀመሪያ መዝግበን እንያዝ። ከዚያ ወደ ቀጣዩ ትግል እንገባለን። ይሄን ብሽቅ ጣቢያማ ልኩን ማሳየት ተገቢ ነው ባይ ነኝ።
… የኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት ነን ባዮች ግን አንዳንዶቹ እያሳቁኝ እያሳቀቁኝም መጥተዋል። መንግሥታችን ጰንጥጧል ብለው እንዲህ ባይወበሩ መልካም ነው። ያ ማነው የሚሉት “ሰኞ ጠዋት ዝናብ ዘንቦ ፈረስ ፊት የሆነ” ዮናታን ተብዬው ሶዬ ልቅና ክፍት አፉን ዐቢይ አሕመድን ተማምኖ እንዲያ ሲዝረከረክብን ዝም ያልነው ሳያንስ አሁን አሁን በዚህ መልክ የመጣውን ውጊያ ግን ለመመከት መዘጋጀቱ መልካም ነው ባይ ነኝ።
… መጀመሪያ በኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁ ድርጅቶችን መመዝገብ እንጀምር። ከዚያ ቀጣዩን አብረን ማየት ነው። አሁን ግን ትኩረታችንን ወደ ሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል እናዙር። በጦሰኛዋ ህወሓት ምክንያት የመጣው መቅሰፍት ለህዝቡ ተርፏል። ረሃብ አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሷል።  በኦሮሚያም ዐማራና ኦርቶዶክስን እንደ አዲስ መግደሉ ተጀምሯል። ከትግራይን ቀጥሎ አሁን ተረኛው ዐማራ ነው። ለዐማራ እነ አቢቹ ከሱዳን ጋር ምን እንደ ዶለቱለት አይታወቅም። መከላከያውን ደጀን አድርጎ የዐማራን ልዩ ሃይል በክላሽ የሱዳንና የዐረቡን ጦር እንዲገጥም ወደ ግንባር እየላኩት ነው። በጎን ደግሞ 500 ሺ የኦሮሞ ጦር ሰልጥኖ የት እንደተደበቀ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። አዎ ትኩረታችንን ወደ ሰሜን እናዙር።
… ሱዳን እየነደደች ነው። የራሷ ጉዳይ።
… ግብጽ እየተናጠች ነው። የራሷ ጉዳይ።
… ለራሳችን እንጨነቅ።
ኢ ቃ ጢ ላ ል ። ሂ ኢ  …
Filed in: Amharic