>

ምናለበት በዚህ እንኳን ባታስመርሩን ? (ሀብታሙ አያሌው)

ምናለበት በዚህ እንኳን ባታስመርሩን ?  

ሀብታሙ አያሌው

* ….እረ ተው በዚህ መንገድ አገር አይገነባም። እረ ተረኝነቱን በልክ አድርጉት።  ኢትዮጵያን  ለአባዱላ ገነት ለአለቃ አያሌው ሲኦል አታድርጓት፤  ይህ የግፍ ግፍ ነው!
 
በታላቁ ሊቅ  በአለቃ አያሌው ስም በራሳቸው የግል ይዞታ ላይ  በመንፈስ እና በስጋ ልጆቻቸው ትብብር   ሊሰራ የታሰበው የግዕዝ ት/ቤት እንዳይገነባ ትላንት ታከለ ኡማ ዛሬ አዳነች አቤቤ ቆልፈው ይዘዋል ።  አሁን ለእኚህ ታላቅ ሊቅ በገዛ ቦታቸው በገዛ እርስታቸው መታሰቢያቸው እንዳይሰራ  ከልክሎ  ለአባዱላ ፋውንዴሽን 19 ሚሊዮን ብር ከተንጣለ መሬት ጋር የሰጠው የአብይ አህመድ መንግስት በእውነት ይህ የግፍ ግፍ አይደለም ?
============
እስከዛሬ ለዓመታት የታገደውን  የአለቃ አያሌውን መታሰቢያ ጉዳይ  እና ከታች ያያያዝኩትን የጠቅላይ ሚንስትሩ ባለቤት ወ/ሮ ዝናሽ ለአባዱላ የሰጡትን 19 ሚሊዮን የሚገልፅ ዜና በንፅፅር እዩት።  እረ ተው በዚህ መንገድ አገር አይገነባም። እረ ተረኝነቱን በልክ አድርጉት።  ኢትዮጵያን  ለአባዱላ ገነት ለአለቃ አያሌው ሲኦል አታድርጓት፤  ይህ የግፍ ግፍ ነው።
============
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ
ታህሳስ 3 ቀን 2012 ዓ.ም
ለክቡር ከንቲባ
አለቃ አያሌው ታምሩ ” በህይወት ዘመናቸው ስለ ኢትዮጰያ አንድነት ሰላምና ፍትህ መስፈን ከፍተኛ ሥራ ሰርተዋል”፡፡ በአዲስ አበባ ተክለሃይማኖት አካባቢ ይገኝ የነበረው መኖሪያ ቤታቸው በመልሶ ማልማት ምክንያት የፈረሰ ስለሆነ ቦታው በርካታ ሊቃውንቶችን ያስተማሩበትና ያፈሩበት ስለሆነ ታሪካዊ ቅርስነቱን ጠብቆ ለማቆየት እንዲቻል ለእኝህ የሀገርና የቤተክርስቲያን ባለውለታ ለሆኑ አገልጋይ ሊቅ በሆኑት አባት ስም ቦታው የዝክረ ሊቃውንት መታሰቢያ ሆኖ እንዲያገለግል በአለቃ አያሌው ታምሩ ስም የግዕዝ ሁለገብ ት/ቤት መገንባት እንዲችሉ በእርስዎ በኩል መመሪያ እንዲሰጥበት በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡
===========
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም
ለክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ
በመሠረቱ አለቃ አያሌው ታምሩ በኖሩበት በግል ቤታቸው ከመደበኛው የሥራ ሰዐት ውጪ ፡ በዓላትንና የዕረፍት ጊዜያቸውን በመጠቀም የጠይቆ መረዳት ፕሮግራም አዘጋጅተው ወንበር ዘርግተው በማስተማር ብዙ ሊቃውንትን ያስገኙበት ቤትና ቦታ ስለሆነ በዚሁ ቦታ ላይ የዝክረ ሊቃውንት መታሰቢያ ሆኖ የሚያገለግል ሕንፃ ቢገነባበት ለሀገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ፈለጋቸውን ለሚከተሉ ሊቃውንት “ባለውለታ” መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ጠቀሜታ ስለሚኖረው በስማቸው የሚጠራ ለታሪክ መዘክርነት የሚበቃ የግዕዝ ሁለገብ ትምህርት መስጫ ተቋም መገንባት እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸው በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን፡፡
========
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳ ባህልና ኪነ ጥበብ ቱሪዝም ቢሮ 
 
ለመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ
የአለቃ አያሌው ታምሩ መኖሪያ ቤት የሊቃውንት መማሪያ የሆነ የጉባኤ ቤት ” የማይዳሰስ ቅርስ ”  የሆነን ጥንታዊ የሀገራችንን ዕውቀት የያዘ መኾኑ ቦታው ለ 50 ዓመታት የሊቃውንት ጉባኤ ሊቀ መንበር በነበሩት በአለቃ አያሌው ታምሩ ዕውቀት ይሰጥበት የነበረ በመሆኑ ቤቱ በቀጣይ በቅርስነት ሊመዘገብ የሚችል ስለሆነ ፡ ታሪካዊነቱን ጠብቆ ለማቆየት እንዲቻል መታሰቢያ ሆኖ እንዲያገለግል በእናንተ በኩል ትኩረት በመስጠት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው፡፡
============
                  ስለ አለቃ አያሌው ዝም አንበል !
         የምትችሉ ሁሉ ለአለቃ አያሌው ውለታ ቢያንስ
         ድምፅ በመሆን  እንተባበር።
         መልዕክቱን እናስተላልፍ።
Filed in: Amharic