>
5:26 pm - Wednesday September 15, 3943

"ከህወሀትም በከፋ ሁኔታ ፍትህን በገመድ አንቆ የሰቀላት ብልጽግና ነዉ!!!" (ሸንቁጥ አየለ)

“ከህወሀትም በከፋ ሁኔታ ፍትህን በገመድ አንቆ የሰቀላት ብልጽግና ነዉ!!!”

ሸንቁጥ አየለ

-በእነ እስክንድር ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤት ግልጽ ክርክር ከማድረግ በድብቅ ደብዳቤ በመለዋወጥ ነዉ የምዳኛዉ ሲል ፍትህና ፍርድን የህጻናት አኩኩሉ ጨዋታ አድርጎታል
-ምስክሮች በግልጽና በገሃድ አይሰሙም
-ዳኞች የሁለቱን ወገን ጠበቆች አያከራክሩም
-ፍርድቤቱ ግልጽ የሆነ ችሎት አይሰዬምለት
——-
ዳኝነቱ እንዲደረግ የተፈለገዉ ግልጽ ባልሆነ: በተድበሰበሰ እና በደብዳቤ ልዉዉጥ ነዉ::ምናልባትም በደብዳቤ ልዉዉጡ ወቅት የ እነ እስክንደር ጠበቆች የሚጽፉትን ደብዳቤ በሌላ የሸፍጥ ደብዳቤ በመቀዬር እነ እስክንድርን ወንጀለኛ ለማድረግም  ታቅዶ ይሆናል::ወይም ደግሞ ሁሉንም ነገር በማድበስበስ እነ እስክንድርን ወንጀለኛ ብሎ ለማወጅ እንዲመቻቸዉም አስበዉ ሊሆን ይችላል::
ከሁሉም ነገር ግልጽ ሆኖ የወጣዉ ግን እነ እስክንድርን መክሰሻ የሚሆን አንዳችም መረጃ የሌለዉ የአቢይ መንግስት አደባባይ ቆመዉ የሚከራከሩ ጠበቆችን ማጣቱን ጭምር ነዉ::
——
ይሄን ፍትህን እና ፍርድን አንቆ በገመድ የማንጠልጠል ሂደት ተከሳሾች ተቃዉመዉታል::የ እነ እስክንድር ጠበቃም ተቃዉሞዉን በዚህ መሰል ሸፍጠኛ ሂደት ዉስጥ አልሳተፍም ሲል አሳዉቋል::
ከመለስ ዜናዊ መንግስት በከፋ መልክ ህግን በገመድ አንቆ የሰቀላት የአቢይ መንግስት እዉን በዲሞክራሲ; አምኖ ምርጫ አድርጎ ስልጣኑን ያስረክባል?
እንዲህ አይነት ዝቃጭ ጸረ ህግ ስርዓት  የስልጣኔ ዉጤት በሆኑ የሰዉ ልጅ እሴቶች ያምናል ብሎ ማሰብ በራሱ በራስ ላይ መቀለድ ነዉ::
Filed in: Amharic