>
5:26 pm - Sunday September 17, 7865

፻፳፭ ኛው የኢትዮጵያውያን ድል በአድዋ ጦርነት ፤ (ከዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

ከዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

           የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን  ፲፰፻፹፰ ዓ/ም=1896 በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ነው። የጦርነቱ ትልቁና የመጀመሪያው የሆነበትም ምሥጢር፤ ኢትዮጵያና ሮማው በትረ-መንግሥታት መካከል(በጣሊያን)የጦርነት ሰበብ የተፈጠረ ነው፤የውጤቱም ሐቅ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት የጣልያን የኝ ግዛት ማስፋፋቱ ተንኮል ተኮላሸቷል።ዘንድሮም በአድዋ ጦርነት የተገኘውን የኢትዮጵያን መቶ ሃያ አምስኛ ዓመቱን የድል በዓል በዓለም የካቲት ፳፫ ቀን ፻፳፭ ኛውን  ዓመቱን እናከብረዋለን።   

አድዋ በትግሬ ክፍለ ሐገር የምትገኝ አንድ አውራጃ ናት፤በጆግራፊካል ኣቀማመጧ አውራጃዋ በኢትዮጵያ ጠረፍ ላይ የምትገኝ የብዙ አገር ሰዎች የሚገበያዩባት ከተማ ቀመስ ቦታ ብትሆንም ጠላት ዐይኑን ያሳረፈባት መሆኑ ይታወቃል።በተለይም የንግድ ማእከልነቷ ምንጊዜም ከመሃል አገር በሚመጡ ኢትዮጵያውያን የምትደቅ ስለሆነ ዝምድናም ከባእዳን ጋር ተፈጥሯል ጠላት ለዚህም ነው ቀዳዳ ኣግኝቶ በኤርትራ ጠረፍ በኩል አድርጎ አድዋ በቀላሉ ሊሰፍር የቻለው፤የሚያሳዝነው ግን ልጆቿ ናቸው  በአሻጥር በተገዙ አገር ከዳተኞች እንደልብ እንዲገቡና እንዲወጡ መንገድ በማሳየት መረጃ መስጠትም በላይ፣በክፉ ቀን ኢትዮጵያ እንድትወጋና ጠላትን በጦር እንዲመሽግ ያደረጉት።ሌሎች የስውር ጠላቶችም ቅኝ ለማስደረግ ሞክረው ማእከላዊው የኢትዮጵያ መንግስት ስለተቆጣጠረው እንዳሰቡት ተንኮላቸው ስላልተሳካላቸው፥ሠራዊታቸውን ላለማጣት ወደኢትዮጵያ ወረራ ማድረጉን ሲተዉ፣የሮማዊው ሥረወ-የባላባት መንግሥት ግን ለዘመናት ብዙ አገሮችን በኃይል ማስገበሩ በዓለም ስለሚታወቅ፣ የካቶሊክ ክርስቲያን ጭምብሉን በመንግሥትነቱ ላይ አስመስሎና አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።በሕግ የተንኮል ኣፈጻጸምን መጠቀሚያ በማድረግ ኢትዮጵያንም በሰበቦች እየተበተቡ ትዕቢትን አምጠው ኢትዮጵያን በእጅ አዙር በቅኝነት ገዥነት አስገብራለሁ ብሎ በጉልበቱ ለመግዛት ውስጣችን ገብቶ ቀና አለ።ይህንንም ተስፋ ይዞ ከሰላዮቹና የወዳጅ ጠላቶቻችን ጋር መረጃዎችን በማሰባሰብ በጦርነት ሊያስፈፅም ወሰነ።
የታሪክ ጉዳይ ሆኖ ግን፥የጣሊያን ባላባታዊ መንግሥት እንዳሰበው የጥቁር ሕዝብ ከዝንጀሮ የመጣ እንደሆነ ለዘመናት ሲተረት የነበረውን ሀሳብ በመያዝና በመናቅ፤ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ያለውን የሰው ልጅ ሁሉ በእግዚኣብሔር ሃምሳል እንደተፈጠረ የሚታወቀውን፤በንቀት በሌሎች አገሮች ላይ ሲያደርገው የነበረውን የግፍ አመፅ ኢትዮጵያ ላይ ለመጀመር ቆርጦ ተነሳ።     
የሮማው ስረወ መንግስት በጎረቤት አገሮቹ በባርነት ወጥመድ ሲጠልፍበት የነበረው የራሱን ሐይማኖት በማስርጽ እንጂ፣ምንም ምክንያት ግን አልነበረውም።ስለዚህም የውጫሌውን የሠላም እና ወዳጅነት ስምምነት መነሻ ሰበብ አደርጎ “ያለፈቃዴ መንግስታችሁ እንደፈለገው ይፈጽማል ያስፈጽማል ስለዚህ ሕገወጥ ነው አሉ፤”የጠቡም ሰበብ በውጫሌው ስምምነት አንቀጽ ፲፯ ላይ የሰፈረው በጣሊያንኛ እና በአማርኛ የተጻፈው ትርጉሙ የተለያየ በመሆኑ፤እንደ አገሮቹ ፍላጎት እንጂ አንድ ዓይነት  ስምምነት አለመሆኑ ተረጋገጠ።ሰበቡ የተፈጠረው ሆን ተብሎ እና ለተንኮል ታስቦ ቢሆንም”ይህንን ችግር በሰላማዊ መንገድ ልናስተካክለው ይገባል እናንተም እኛም መረጃዎቹ አሉን፣”ብለው እምዬ ምንሊክ ለጣሊያን መንግሥት ቢያቀርቡም ሮማውያን ግን “ስምምነት ብሎ ነገር የለም በኃይል እናስፈጽማለን፦”ብለው ወሰኑ፤ለዚሁም ጉዳዩን በጦርነት ሊፈቱት ሁለቱም ቀን ቆረጡበየካቲት ፳፫ አድዋ ላይ ጦርነት ሊገጥሙ።እንግዲህ በጥሞና ታሪካችንን እናስተውል የሰላም እምቢታው የመጣው   ሮማው ንጉሠ ነገሥት የስርወ መንግሥት ነው፤ምን ተማምነው?በሚገባ ስለላው መፈጸሙን፣ምሽጎች መያዛቸውን፣ተጨማሪ የተዋጊ ጦር በጎረቤት አገሮች ኤርትራን ጨምሮ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።ትልቁ ያልተረዱት ነገር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በልቡ ውስጥ እግዚአብሔር የሰጠው የተፈጥሮ እሳት መኖሩን ነው።(Bob Marley – WAR BOB MARLEY “Songs of Freedom” CD 4 of 4 (1992) (FULL ALBUM))ይህ ሥጦታ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ፀጋ ነው፤ለዚህም ነው በትንንሽ ጦርነቶች ሳንሸነፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ  ተፈትኖም እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሮማው መንግሥት ኢትዮጵያን ለማንበርከክ መውጋቱን ያላቆመው። የሚያሳዝነው ደግሞ ከሱዳን፣ከግብፅ፣ከትግሬ፣ከኤርትራ እና ከሌሎች የሮማውያን ቅኝ የተገዙ አገሮችን ወቅቱ ድፍን አፍሪቃን የመቀራመትና በእስፓንሾች የተጀመረው ጥቁር ሰውን ለሰፋፊ እርሻዎች በነጻ በጉልበት የማጋዙ ሁኔታ ተጧጡፎ ስለነበር፣በወታደርነት አሰባስቦ በመረጃነት እና በተለያዩ ሙያዎች ቄስነትን ሳይቀር በስለላ ሥራ ላይ አዝምቷቸው ነበር።
በተጨማሪም በዘመናዊ መሳሪያዎች እና የጦር ባለሙያዎች ታጅቦ፣የጣሊያን ገበሬዎችን ሳይቀር በግዴታ አሰልፎ  ሲጠቀምባቸው፣በኢትዮጵያ  በወቅቱ ንጉሠ ነገሥት  የነበሩት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነበሩና፤ጾም ጸሎት ኣድርገው፣ታቦታቸውን አሸክመው ሰራዊት እና የጦር ኣዛዦቻቸውን ኣስከትለው፤በኢትዮጵያ ሕዝብ ታጅበው በጊዮርጊስ መሪነት በኣንድዬ ጠባቂነት ዘመቱ።ትዕግሥት ጥበብ ዘዴ እና ቆራጥ የእናት ልብ የያዙት እምዬ ምንሊክ ምንም ኣማራጭ አልነበራቸውም ሁሉም ነገር ወደጦር ግምባር ብሎ ጠላትን ፊትለፊት ከመጋፈጥ ሌላ።
አዋጅ አስነግረው ነጋሪት አስጎስመው፤ጀግና የጦር መሪዎቹን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ያለውን የእያንዳንዱን ልብ ችቦ በፉከራ፣በቀረርቶ፣ በሙሉ ልበነት፣በወኔ አቀጣጥለው፣ በአገር ፍቅር ስሜት አጥምደው፣እዚያው አድዋ ድረስ ለሁለት ወራት በመጓዝ ወዳጅም ሆነ ጠላት ባልጠበቀው መንገድ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት አስሸክመው የሮማውያንን የዘረኛ ባላባት ሠራዊትን እንደተባለው ኣገኙት።
ወዲያው አድዋ ላይ ጦርነት ገጥመው በእግዚአብሔር ክንድ አዋርደው የካቲት ፳፫ ማርች ፪ ፲፰፻፹፰ በአድዋው ጦርነት የኢትዮጵያን ድል ለዘላለም ለማስጠበቅ  የሮማውያንን ቅኝ፡ገዢዎችን ድል አደረጓቸው።የሮማው ሥርወ፡ባላባት መንግሥት ለዘመናት በጉልበቱ እየተመካ ብዙ መንግሥታትን ሲያሸንፍና ቅኝ ሲያደርግ የነበረው በዓለም መንግሥታት ፊት የተዋረደበት ምክንያት፥የጥቁር አገር ሕዝብ አልሰለጠነም እየተባለ በዓለም ላይ ግፍ ይሰራ እንደነበረ እና ይህም ጭቆና የተንሰራፋው ፍፁም ከማይታመን ፍልስፍና ጋር ተያይዞ በካቶሊክ ዕምነት በሚመራ መንግሥታት ውስጥ በመሆኑ እጅግ አሳዛኝ ነበር።
  “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።”
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ ፩ ቁ ፳፯

በውጭ መንግሥታት የእግዚኣብሔ ንብረትነቷ እና ስጦታዋ ብዙ የማይታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ፣ለውጭ ዜጎች በሯ ጥንትም የተዘጋ ሲሆን፣ጠንካራ ጦር ባላት የክርስቲያን አገር በሆነች በሮማውያን ካቶሊክ የመወረር ሚሥጥራዊ ምክንያት፣ከትዕቢት የመነጨ ክርስቶስን እንኳ የዳኘነው እኛ ነን ብለው የሚመፃደቁ መንግሥታት በመሆናቸው እና ጥቁር ሰው ዝንጀሮ እንጂ ሰው አይደለም ብለው ከተሰለፉት መካከል፣ግንባር ቀደም ስለሆኑ ነው።

አሳፋሪው ደግሞ በክርስትና ሥም በዓለም ላይ ሠይጣናዊ ግፍ በትውልድ ላይ መፈፀሙ ሳያንስ የብዙ አገሮች በቅኝ መያዝ ዋናው መረጃ አቀባይ ክርስቲያኖች መሆናቸው ሲታወቅ እጅግ ኣድርጎ ያሳፍራል።ዛሬ ዛሬ ግን ሮማውያን በኢትዮጵያውያን(በጥቁር ሕዝቦች) ተሸነፈ ሲባል ሠለጠኑ የተባሉት መንግሥታት ሁሉ አፋቸውን ሲይዙ፣የሮማው ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግን ውርደቱን ተከናንቦ በሰላም ሊኖር አልፈለገም፤ስለዚህም ራሱን ለመረረ የመሰሪ በቀል በግዴታ ውስጥ ውስጡን በመዘጋጀት እምቢ የተባለውንም ውል ፈርማ ተቀብላለች።ሆኖም ግን ምንጊዜም ተንኮል የምትጎነጉን የሮማ መንግስት ኢትዮጵያ በነፃነቷ የነበርችና አሁንም ያለች ሉአላዊ መንግሥት ያላት የክርስቲያን አገር መሆኗን አረጋግጣለሁ ብላ ብትፈርምም በሌላ በኩል ለበቅል እንደምትመለስም እምዬ ምኒልክ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ኢትዮጵያን በሁሉም መስክ ማዘመንን ተያያዙት።የስልክ ማስተከል፣ የፖስታ መላላክ፣የትምህርት ቤቶች መኖር፣የህክምና ሙያ ማሰልጠን እና ሌሎችም የስልጣኔ ዘርፎች ሁሉ አገርህ በሰላም እንድትኖር ከፈለግክ፣ምንጊዜም ለጦርነት ዝግጁ መሆን ይገባል የሚለውን ብሂል ይዘው ነው።አሳዛኙና የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነውና በዓለም ላይ እስከዛሬም ድረስ እየተዋረደ ያለው የሮማው ሥረወ፡መንግሥት፣ኢትዮጵያ ላይ እንደዚህ ጠላት የሆነበት ምሥጢር የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስን በማጥፋት የካቶሊክ ዕምነትን በኢትዮጵያ ላይ በግድ ለማስረጽ በሚደረግ የመጨረሻው ሰማያዊ ፍልሚያ ለመሆኑ በጥንቃቄ ማገናዘብ የሚቻል ነው።ምንም ዓይነት ዕምነት ይሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዕምነትን የሚያዳክም ሁሉ፣ተራ ፖለቲከኛም ሆነ አክራሪ እስላም ኢትዮጵያያን  ለመበታተን ካቶሊኮች እንደሚያግዟቸው ስላመኑበት በማንኛውም መንገድ የመንግሥት ሥልጣንነትና ልዩነቶችን በማስፋትና የገንዘብ ያላሰለሰ ድጋፍ በአንዳንድ ሮማውያኑ መንግሥት(ኢጣሊያ)በአንዳንድ ሚሥጥር ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
ዳሩ ግን ኢትዮጵያ እጆቿን የምትዘረጋው ወደኃሉ እግዚአብሔር እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱሳችንም ላይ ታዟልና፣“መዝሙረ ዳዊት ፷፰፥፫፩ መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”
 እኛ ግን በኢትዮጵያ አገራችን ለኢትዮጵያ የተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ዕምነታችን ዛሬም በኢትዮጵያ ነፃነት ውስጥ እንደ አድዋው ጦርነት የኢትዮጵያን ድል ከውጥም ከውጭም  ለዘላለም ለትውልድ ለማስጠበቅ እንደ የአድዋው ጦርነት በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣውን የኢትዮጵያ ጠላት አምርረን እንታገላለንበቅርቡ በትግሬ ክልል በሕግ እንደተፈጸመው። 

 

 

ኢትዮጵያ በልጆቿ በሠላም በእኩልነት እና በነጻነት ተከብራ ለዘላለም ትኑር፤አሜን። 
Filed in: Amharic