>
5:31 pm - Wednesday November 13, 5078

ኢትዮጵ/ኢትኤል - ኢትዮጵያ መጠሪያዋን ከየት አገኘች??? (ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ)

ኢትዮጵ/ኢትኤል – ኢትዮጵያ መጠሪያዋን ከየት አገኘች???

ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው ሊቀ ካህኑብ መልከፄዴቅ ሶስት ወንድ ልጆች ነበሩት ከነኛ ልጆች አንዱ ደግሞ ኢትኤል ነበር ኢትኤል በመንፈስ ተመርቶ ካለበት ከሳሌም እስራኤል ወደ ጣና ላይ እንዲሰፍር ታዘዘ። ኢትኤል ጣና ሲደርስ ስሙን ቀይሮ ኢትዮጵ እንዲባል ሆነ። ኢትዮጵ ማለት ፦ ኢት – ስጦታ ማለት ሲሆን ዮጵ ደግሞ ቢጫ ወርቅ ማለት ነው። ኢትዮጵ የቢጫ ወርቅ ስጦታ! ኢትኤል ማለት ደግሞ የእግዚአብሄር ስጦታ ማለት ነው። የሃገራችን መጠሪያ የመጣው ከንጉስ ኢትዮጵ በኃላ ነበር በኢትዮጵ ኢትዮጵያ ተባለች።
ሃገራችን ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት እንቆጳግዮን ተብላ ትጠራ ነበር። በነገደ ዮቅጣን አግአዝያን የሚባሉት አቡሳውያን እንቆጳግዬን የሚለውን ወደ እንቆጳፅዮን ቀይረውታል። እንቆጳግዮን – የአባይ ወርቅ ፤ እንቆጳፅዮን – የፅዮን ወርቅ ማለት ነው።
ንጉስ ኢትዮጵ በግዮን ወንዝ ዳርቻ ላይ የድንጋይ ወንበር አስቀምጦ የልጅ ልጆቹ በሚነግሱበት ግዜ ቅብኣ መንግስቱን እንዲነግሱበት ሲል በክብር አስቀምጦታል። ንጉስ ኢትዮጵ ከአባቱ መልከፄዴቅ የተረከባቸውን መፅሃፍት እየተረጎመ አስቀምጧቸዋል ለልጆቹም ስርአተ ክህነት እና የቅብአ መንግስትን ግብር አስተምሯቸው እስከወዲያኛው ድረስ እንዲተላለፍ አድርጒል። ኢትዮጵ የግዮን ወንዝ የሚደርስባቸውን መሬቶች በሙሉ የኢትዮጵያ ግዛት እንዲሆኑ ያደረገ ሃያል ንጉስ ነበር።
ብዙ ሰዎች ንጉስ ኢትዮጵን ከ ኢትዮጲስ ጋር አንድ አድርገው ሲመለከቱ ይስተዋላል ስህተት ነው። ንጉስ ኢትዮጲስ ኢትዮጵ ከነገሰ ከብዙ ዘመናት በኃላ የነገሰ ንጉስ ነበር በ1856 አ.አ የነገሰ ንጉስ ነው።
የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት ኢትዮጵ በተወለደ በ150 አመቱ አርፏል። ልጆቹም አባቱ መልከፄዴቅ ካስፈለፈለው ዋሻ ውስጥ ወስደው እንደቀበሩት የታሪክ ድርሳናት ይዘግባሉ።
Filed in: Amharic