>

አብርሃ ደስታ ''እናመሠግናለን'' ¡ (ሙሉአለም ገብረመድህን)

አብርሃ ደስታ ”እናመሠግናለን” ¡

ሙሉአለም ገብረመድህን

* በዛሬው ዕለት ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ዳንሻ፣ ወፍ-አርግፍ፣ ማክሰኞ ገበያ፣…ህጻናት፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ …የቀረ የህብረተሰብ ክፍል የለም፦
“በትግሬ ገዥዎች ለዘመናት ለተፈጸመብን ግፍና በደል ‘ይቅርታ’ እና ‘ካሳ’ እንጠይቃለን!
#ወልቃይት #ጠገዴ #ጠለምት ፩ ዐማራ”
የሚል መሪ ጥያቄ በማንገብ መልዕክታቸውን በምስል ሲያስተላልፉ ውለዋል!!!
 
በመደበኛዋ ትግራይ (Proper Tigray) በተቋቋመው ጊዜዊ አስተዳደር ውስጥ የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ሆኖ የተሾመው የአረናው አብርሃ ደስታ ዛሬ ቀላል ግምት የማይሰጠው “ውለታ” ውሎልናል።
በጠዋቱ የትህነግን የተስፋፊነትና የዘር ማጥፋት ምልክት የሆነውን Political Tigray Map (በአማራ የግዛት ቅነሳና የዘር ምንጠራ ተስፋፍታ ድኀረ-1983 የተመሰረተችውን የፖለቲካዊ ትግራይ ካርታ)ን ለጥፎ፤ በተለያዩ  ጉዳዮች ተዘናግቶ የሰነበተውን ሕዝባችንን አንቅቶልናል።
መቼም የኛ ሕዝብ ገራሚ ነው! ትህነግን ለመደምሰስ በተደረገው ዘመቻ አራሹም፣ ተኳሹም፣ ቀዳሽና ዱዓ አድራሹ እንደየ አምዱ ንቁ ተሳትፎ ካደረገ በኋላ ወደ መደበኛ ሕይወቱ ተመልሷል። ወልቃይት በለው ራያ የአማራ መንግሥት ተተክሏል (መንግሥት ተመስርቷል) ብሎ ስለሚያምን ለተጨማሪ ተልዕኮ ጥሪ እስካልተደረገለት ድረስ በሌላ አቅጣጫ  (መተከል) በኩል ወዳለው ጉዳይ ትኩረት አድርጓል።
የማይካድራው ዘግናኝ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ጥፋተኞቹ (ያልተደመሰሱት) እየታደኑ “በሕግ ይጠየቃሉ” የሚል እምነት በመንግሥት ላይ አሳድሮ የሚሆነውን በመጠባበቅ ላይ ነበር። ይህ አማራው ለሥነ-መንግሥት እሳቤ ካለው ቅርበት የሚመነጭ “በመንግሥት እምነት የማሳደር” ጉዳይ ከለውጡ ወዲህ በብዙ መልኩ ሕዝቡን ለጉዳት ዳርጎታል።
በመንግሥት ላይ እምነት ያሳደረው ሕዝባችን ትርጉም ያለው መስዋዕትነት የከፈለበትን የወልቃይትና የራያ ጉዳይ የትላንት አራጆችን ውርስ ለማስቀጠል የሚያልሙት እነ አብርሃ ደስታ በሕዝብ ትግል የተቀበረውን የተስፋፊነት አጀንዳ  መግለጥ ሲጀምሩ ሕዝባችን ዳግም ወደንቅናቄ ለመግባት ተገዷል።
አብርሃ ደስታ በተጨባጭ ታሪክ የሆነውን የ Political Tigray Map ከለጠፈበት ደቂቃ ጀምሮ በመላው ዓለም  ካሉ የአማራ ልጆች የተሰማው ስላቅ የቀላቀለ ቁጣ   አስደስቶኛል። በተለይም የዘር ማጥፋቱ የወዲያው ተጠቂ የሆኑት የወልቃይት ጠገዴ አማሮች ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተሳካ ሊባል የሚችል ንቅናቄ አድርገዋል።
በዛሬው ዕለት ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ዳንሻ፣ ወፍ-አርግፍ፣ ማክሰኞ ገበያ፣…ህጻናት፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ …የቀረ የህብረተሰብ ክፍል የለም፦
“በትግሬ ገዥዎች ለዘመናት ለተፈጸመብን ግፍና በደል ‘ይቅርታ’ እና ‘ካሳ’ እንጠይቃለን!
ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት
፩ ዐማራ”
የሚል መሪ ጥያቄ በማንገብ መልዕክታቸውን በምስል ሲያስተላልፉ ውለዋል። ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ ወልቃይት ምድር “መጥተን እንግደላችሁ ስትሉን እጃችን ዘርግተን አንቀበላችሁም” የሚል ሕዝባዊ ድምጽ ተስተጋብቷል።
አብርሃ ደስታ ይህን ታሪክ የሆነ ካርታ ባይልጠፍ ኑሮ ይህን ንቅናቄ ማየት ባልቻልን ነበር። ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ሕዝባችን መንግሥትን ያምናል። ከትሕነግ መደምሰስ በኋላ ያለው ስራ የአማራ መንግሥት የቤት ሥራ ነው ብሎ እምነቱን ጥሎ (እንደእውነቱ ከሆነ ‘ተዘናግቶ’) ነበር። ከምንም ነገር የመማር ፍላጎት የሌላቸው እነ አብርሃ ደስታ የትህነግን ውርስ የማስቀጠል ፍላጎታቻውን ሲገልጡ የተዘናጋውን ሕዝባችንን ቆቅ እንዲሆን አድርገውልናል። አብርሃ በዚህ ድርጊቱ ቀላል ግምት የማይሰጠው “ውለታ”  ውሎልናሎ።
የትህነግን ተስፋፊነትና የዘር ማጥፋት ምልክት የሆነውን Political Tigray Map በመለጠፍ በተለያዩ  ጉዳዮች ተዘናግቶ የሰነበተውን ሕዝባችንን የማንቃት ስራ በመስራቱ አብርሃ ደስታን “እናመሰግናለን”¡
የቀድሞው የቃላሚኖው ተማሪ “የሳልሳዊ ወያኔ” ትውልድን ከፊት ሆኖ እንዲመሩ ከታጩና በከፍተኛ ወጭ የሁለተኛ ደረጃ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ትምህርታቸውን ከተከታተሉት አንዱ የሆነው አብርሃ ደስታ፤ በእርሱ ቤት ሳልሳዊ ወያኔን ለመምራት ‘Populist Agenda’ ይዞ መምጣቱ ነበር፣ የነሱን ባላውቅም  በዚህ አጀንዳው እኛን አትራፊ አድርጎናል።
የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ለአፍታም ቢሆን አይናችንን ልንነቅልበት የማይገባ ጉዳይ ስለመሆኑ የአብርሃ ቅዥት ‘የማንቂያ ደወል’ ሆኖናል። ሰዎቹ እንደማይተኙ መንግሥትን አምኖ ለተዘናጋው ሕዝባችን ጥሩ ትምህርት ነው።
***
የአማራ መንግሥት አመራሮች ከሕዝብ ጋር የታረቃችሁበት አንዱ የንስሃ ድልድያችሁ ወልቃይትና ራያ ይባላሉ።
በሁኔታዎች ልክ ትኩረት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ። [በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩና ካቢኔቸው በኩል የውሳኔ ችግር ባይኖርም] ከመወሰን ባሻገር  ውሳኔዎች ስለመፈጸማቸው መከታተል ይገባል። የገቨርናንስ ስራው በሁኔታዎች ልክ ሊጓዝ ይገባዋል። መፈጸም የሚችል አስተዳደር መትከል የሞት_ሽረት ጉዳይ ነው!
ያመናችሁን ሕዝብ እምነት ለመጠበቅ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ከመልካም ጉርብትና በዘለለ በአስተዳደራዊ ጉዳይ እጁን ከሰደደ እንደአመጣጡ እጁን በመቁረጥ የሕዝብ መንግሥት መሆናችሁን አስመስክሩ።
***
በተረፈ የትግራይ “ክልል” ጊዜያዊ አስተዳደር የዘመን አቆጣጠር መምታታት አጋጥሞት ከሆነ ላስታውሰው እወዳለሁ። ይህ ዘመን 2013 እንጅ 1983 አይደለም!
የጊዜዊ አስተዳደሩ ተልዕኮ በፈረሰው የክልሉ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር ጊዜያዊ አስተዳደር በመመስረት እስከ ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ድረስ ‘ትግሬ ነኝ’ የሚለውን ሕዝባቸውን በጊዜዊነት ማስተዳደር እንደሆነ ይታወቃል።
ይህ መደበኛዋን  ትግራይ (Proper Tigray Territory) እንጅ ፖለቲካዊ ትግራይ (Political Tigray Territory)ን አይመለከትም። ራያም ሆነ ወልቃይት አማራነቱን አውጇል። ይህ 2013 ነውና የማያምንበትን ማንነት ልትጭኑበት  አትችሉም!  የሕግም ሆነ የጉልበት አቅሙ ከናንተ ዘንድ የለም። ፖለቲካ የሚሰራው በምኞት ሳይሆን በሚቻለው መጠን ልክ ነው። አሁናዊው እውነታ ‘ፖለቲካዊ ትግራይን’ ሊያስተናግድ የሚችል አይደለም። ራያም ሆነ ወልቃይት በምን መንገድ ወደ ፖለቲካዊ ትግራይ ግዛት እንደተጠቃለሉ ይታወቃል (That was real annexation)  እናም አሁን ሰዓቱ የምልሰት renewing = restoration ነው።
በርግጥ እናንተን ከመምከር ድንጋይ መቀቀል ይቀላል። ከምንም ነገር የማትማሩ የፖለቲካ መርህም ሆነ ማህበራዊ ይሉኝታ የማይገዛችሁ ልብ-ውልቅ ናችሁ።
አብርሃ ደስታ ግን በቀሽሙ ፕሮፖጋንዳህ መንግሥትን በማመን ሁኔታዎችን በአርምሞ ሲከታተል የቆየውን ሕዝባችን  ወደንቅናቄ ስለመለስክልን ‘የቐንየልና’ ¡
Filed in: Amharic