“ከትግራይ መሬት አንድ ካሬ ሜትር ብትወሰድ መሬቴን ለማስመለስ እታገላለሁ…!!!”
አብርሀ ደስታ
የትግራይ ክልል ግዝያዊ መስተዳድርን እደግፋለሁ። ምክንያቱም መንግስት አልባ ከመሆን የግዝያዊ መንግስትን መኖር ይሻላል። ምክንያቱም መንግስት ካለ መብራት፣ ስልክ፣ ባንክ ወዘተ ይኖራሉ። ህዝብ በደል ሲደርስበት የሚጮህበት/ለት አካል ያስፈልገዋል። የግዝያዊ መስተዳድሩ አካል የሆንኩት በፖለቲካዊ ምርጫዬ አይደለም፤ የፌደራል መንግስትን አቋም ደግፌ ወይም ህወሓትን ተቃውሜ አይደለም። የግዝያዊ መስተዳድሩ አካል የሆንኩት በሰብአዊነት ነው፤ ቢያንስ የአንድን ትግራዋይ ህይወት ማዳን እችላለሁ ብዬ ነው። ከትግራይ መሬት አንድ ካሬ ሜትር ብትወሰድ ግን ስልጣኔን በገዛ ፍቃዴ እለቃለሁ። መልቀቅ ብቻ አይደለም፤ የፌደራል መንግስትን ባደባባይ እቃወማለሁ። መቃወም ብቻ አይደለም፤ መሬቴን ለማስመለስ እታገላለሁ። ደግነቱ የትግራይ ክልል ግዝያዊ አስተዳደር ካቢኔ አቋምም ይሄ ነው። ትግራይ ለዘላለም ትኑር!