>
5:13 pm - Wednesday April 19, 6637

የራስ መኮነንን ሐውልት አፍርሶ የአድዋን ድል የሚዘክረው የሐረሪ ክልል...!!!   (አቻምየለህ ታምሩ)

የራስ መኮነንን ሐውልት አፍርሶ የአድዋን ድል የሚዘክረው የሐረሪ ክልል…!!!  

አቻምየለህ ታምሩ

* … ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አድዋ ቆስለው ስለተመለሱት አባታቸው ስለ ራስ መኮንን የሰጡት ምስክርነት! 
 
ያገራችን ሰው “ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር” የሚል ብሒል አለ። ብሒሉን ማስታወሴ ከሐረር ወደ አድዋ የዘመተውን የኢትዮጵያ ጦር የመሩትንና የጣሊያንን ወራሪ ጦር በአምባላጌ፣ በመቀሌና መጨረሻም በአድዋ  አቧራ ያስገሱትንና ወደ አድዋ የዘመተው ጦር ጠቅላይ ኢታማጆር የነበሩትን የራስ መኮነን መታሰቢያ ሐውልት ያፈረሰው የሐረሪ ክልል የአድዋን ድል እያከበርሁ ነው ሲም በማየቴ አለማፈሩ  ገርሞኝ ነው።
 ከንጉሠ ቀጥለው የአድዋው ድል ምልክት የሆኑትን የራስ መኮንን ሐውልት በጠራራ ፀሐይ ያፈረሰው የሐረሪ ክልል የነማንን ድል ነው እያከበረ ያለው? ሐውልታቸውን ያፈረሰውን የራስ መኮነን ድል? በሐረሪ ክልሉ እፍረተቢስ ፕሬዝደትንት ቧልት እሱ ባያፍር እኛ ሐረር ከተማ ቆሞ የነበረውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠራራ ፀሐይ ሲያፈርስ ወይም ሲያስፈርስ ያየነው የሚጣላ ኅሊና ያለን ሰዎች እናፍራለን! እኛ ብቻ ሳይሆን የሐረሪ ክልሉ ፕሬዝደትን እያከበርነው ነው እያለ የሚቀልድበት የአድዋ ድልም አፍሮበታል።
ራስ መኮነንን ጠልተው መታሰቢያቸውን ካፈረሱ በኋላ ራስ መኮነን ያስቆጠሩትን ድል ለምን ይኮሩበታል? ስለምስን ያከብሩታል? የአድዋን ድል ወድዶ የአድዋውን ጀግና ግን ጠልቶ ይሆናልን? አፍረተቢስ ነውረኞች!
እኛ ግን እንዲህ እንላለን. . .
የቃኘውን ሐውልት ማፍረስ መደምሰሱ፣
የጠቅልን ሐውልት ማፍረስ መደምሰሱ፣
ይቀርበት እንጂ አፍራሹ ለራሱ፣
ምን ሊያጎልባቸው ምን ሊቀር ለነሱ፤
ስራቸው ይኖራል ቢፈርስ ሐውልታቸው፣
መች አውርተን ጠገብን ስለውሌታችው።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አድዋ ቆስለው ስለተመለሱት አባታቸው ስለ ራስ መኮንን የሰጡት ምስክርነት! 
ከታች የታተመው ታሪካዊ ድምጽ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥሳሌ አባታቸው ስለሆኑት ስለ አድዋው ጀግና ስለ ራስ መኮነን የሚያውቁትንና በዐይናቸው ያዩትን በአንደበታቸውየሰጡት ምስክርነት ነው። ግርማዊ ጃንሆይ ስለ አባታቸው ይህንን ታሪካዊ ምስክርነት የሰጡት ከ64 ዓመታት በፊት የአድዋን ድል ዝክረ በዓል ባከበሩበት እለት ነበር።
የሐረሪ ክልል ግን አድዋ ቆስለው የተመለሱትን  የብሔራዊውን ጦር  ጠቅላይ ኢታማጆች የመታሰቢያ ሐውልት አፍርሶ ያለ ድሉ ምልክት ያለ ራስ መኮንን የአድዋን ድል እዘክራለሁ እያለ የአድዋን ድል እያጎደለ ይቀላል!
ከታች የታተመው የጃንሆይ ንግግር ከድምጽና ምስል ክምችት ክፍላችን የተወሰደ ነው።

*      *      *

*….  የሐረሪ ክልል የራስ መኮነንን ሐውልት አፍርሶ  የአድዋን ድል የሚዘክርበት ምን ሞራል አለው??? https://youtu.be/N0gNKhSgC4M
Filed in: Amharic