>

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በገበታ ለሀገር የምስጋና መርሀ ግብር ላይ የተናገሩት  ዋና ዋና ነጥቦች:-

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በገበታ ለሀገር የምስጋና መርሀ ግብር ላይ የተናገሩት  ዋና ዋና ነጥቦች:-
• ህመማችን፣ መድሃኒታችን፣ ተስፋችን፣ ድካማችን፣ ገበታችን፣ ስራችን ህልማችንና ግባችን ኢትዮጵያ ናት፡፡
• ኢትዮጵያ ወደ ከፍታ፣ ወደ ብልፅግና ማማ እንድትደርስ፣ እንድታምርና እንድትልቅ የማይፈልግ የማይመኝ ፣ የማይናገርና የማይተነትን የለም፤
• ነገር ግን ኢትዮጵያን በመሻት ብቻ ከምንፈልገው ደረጃ ልናደርሳት አንችልም፤
• ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ማማ የምትወጣው አዕምሯችን፣ ልባችንና እጃችን ሲተሳሰርና ከወንድም እህቶቻችን ጋር ተደምረን ሀገራችንን ማነፅና መገንባት ስንፈልግ ብቻ ነው፤
• በዓለም ላይ አድናቆት ያተረፉ ስራዎች ሁሉ የሰውን ጭንቅላት ፣ ገንዘብና ጊዜን ይሻሉ፤
• በቀደመው ታሪካችን በተለያዩ ከባቢ የነበሩ ነገስታት ግማሾቹ ቅርፃ ቅርፅን በመስራት፣ ከፊሎቹ የሐይማኖት ተቋማትን በመገንባት ወደ ደቡብና ምዕራብ ደግሞ የበለጠ ጫካና ደንን በማቆየት ይወዳደሩ ነበር፤
• እነዚያ ደኖች ቤተ መንግስቶችና ቅርፆች በኢትጵያውያን ላብና ደም ያማሩ የተዋቡና በኢትዮጵያውያን አጥንትና ስጋ የቆሙ ድሮ የተሰሩ ለዛሬ ወረትና የኩራት ምንጭ የሆኑ ናቸው፤
• ዛሬ ያለው ትውልድም መሰል ታሪክ መጣል ይገባዋል፤
• ታሪክ መስራት በገንዘብ፣ በጊዜና በትችቶች ላይ መጀገን ጠይቃል፤
• ላለፉት 100 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪዎች ቤተ መንግስት ለምን አልከፈታችሁልንም፣ ለምን መካለነ እንስሳት ቤተ መንግስት ውስጥ አልገነባችሁም፣ ለምን መዝናኛ ቦታ አላደረጋችሁም የሚል ጥያቄ ማንም አክትቪስትና ፖለቲከኛ ጠይቆ አያውቅም፤
• ስንሰራ ለምን ሳር በዛ ለምን አንበሳው ነጭና ጥቁር ሆነ የሚል ትችት ይነሳል አለመስራት ብቻ ነው ትችት የማያስነሳው፤
• ከሰራችሁ ትችት አለ፤ ውዳሴው ሙገሳውና ምስጋናው በትውልድ የሚፈጠር ይሆናል፤
• የእኔ ምኞት የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ገበታ ለአፍሪካ ብለን አንድ አራት አምስት የአፍሪካ አገራትን መርጠን መሰል ፕሮጀክቶችን በመስራት ልክ ቻይናዎች ሰሩልን ብለን እንደምናመሰግነው ኢትዮጵያ ሰራችልን የሚባልበት ዘመን እንዲመጣ ነው፤
• የተሸለ ነገር በጎርጎራ፣ በኮይሻና በወንጪ ላይ ሰርተን ለአዳዲስ ትችትና ነቀፋ እራሳችንን መዘጋጀት ይኖርብናል፤
• አዲስ አበባን ብቻ በማየት ኢትዮጵያን ማወቅ አይቻልም፤ ወጣ እያልን የኢትዮጵያን ልክ በማወቅ የምናስበውን ትልም ለህዝባችን በሙሉ ዕውቀት መግለፅ ይገባናል፤
• ስለድህነት እያወራን ፊታችን ከሚጨልም ስለ ብልፅግና እያወራን ፊታችን ቢፈካ ይሻለናል፤
• ስለ ጥላቻ እያሰብን ፊታችን ከሚኮስስ ስለ ፍቅር እያሰብንና እየተናገርን ፊታችን ቢያበራ ይሻላል::
EPA
Filed in: Amharic