የመረጃ ቴቪን የዩቲዩብ ቻናል ዘጉት…!!!
ዘመድኩን በቀለ
… በጣም ነው የፈሩኝ። ከምር አዛኜን ከምር ነው የፈሩኝ። የኢትዮጵያን ትንሣኤ አብሳሪ ነኝና ባይፈሩኝ ነበር የሚገርመው። እወቁት። ይሄን እውነት በየፌስ ቡካችሁ ሼር አድርጉት።
… የዩቲዩብ ካምፓኒ ሆዬ ያው እንደተለመደው እኔ አሸናፊው ዘመዴ ነፃ ሃሳቤን ስለገለጽኩበት ብቻ የመረጃ ቴቪን የዩቲዩብ ቻናል ነጮቹ ሙሉ ለሙሉ ዘግተውታል። መረጃ ቴቬ በሁኔታው በመገረም በመደነቅም የፊታችን ሰኞ የዩቱዩብ ካምፓኒውን በአሜሪካ ሕግ መሠረት ለመጠየቅ በአሜሪካ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት በመወሰን ከጠበቃ ጋር ተማክሮ ጨርሷል። ሰኞ የክስ ሄደቱ ይጀመራል። የቴሌቭዥን ጣቢያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ እንደነገረኝ ከሆነ ጉዳዩ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የፈጀውን ጊዜ ፈጅቶ ይሄን ጉዳይ ሕግ ይፈታዋል። እስከዚያው ግን በርካታ አማራጮች ስላሉን በዚያ እንጠቀማለን በማለት የማይሰበረው ኤልያስ ሃሳቡን ሰጥቶኛል። ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ሟቿ ህወሓትና ሼክ አላሙዲን በጋራ ከሰውት በፍርድ ቤት ተከራክሮ የረታቸው ብርቱ የኢትዮጵያን ሪቪው መጽሔት ባለቤትና አዘጋጅ የነበረ ወንድማችን ነው።
•••
መንገድ ዝጉ፣ ኢትዮጵያን አፍርሱ፣ ጎማ አቃጥሉ፣ ንብረት አውድሙ፣ ሰው ግደሉ የሚሉ መልእክቶችን የሚያስተላልፉ ሚዲያዎችንና ግለሰቦችን ባላየ ባልሰማ ዝም ጭጭ ብሎ ሲያይ የሚውለው ዩቲዩብ፣ ስለ ዝሙት፣ ግብረገብ የሌላቸው መልእክቶችን፣ የሐሰት ዜናዎችን ሲፈበርኩ የሚኖሩ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን ጭጭ ሲል የሚከርመው ዩቲዩብ በአንጻሩ ለመላ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥብቅና የሚቆሙ ግለሰቦችም ሆነ ተቋማት ብቅ ሲሉ በመኮርኮም አካውንቶቻቸውን መጠርቀሙ የሚያሳየው በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ የታሰበ የጥፋት ድግስ መኖሩን ነው። እናም ይህን አስቀያሚ ድርጊት ሁላችንም ልንቃወመውም ይገባል። በቀጣይም የዩቲዩብ የሥራ ኃላፊዎች በሙሉ የኢሜይል አድራሻ በቴሌቭዥንና በቴሌግራም እንዲሁም በፌስቡክ ጭምር በመልቀቅ ተቃውሞአችንን እናሰማለን። ጠብቁኝ። ኤትአባታቸውንስና ደግሞ የምን እጅ መስጠት ነው። ሌሎች እንዲሁ ከዩቲዩብ በመባረራቸው ምክንያት ዩቲዩብን የሚተካ ዩቲዩብን የመሰለ ካምፓኒም የመሰረቱ ነጮች ተገኝተዋል። እነሱንም አጥንተን እንቀላቀላቸዋለን።
•••
ለማንኛውም የቴሌቭዥን አገልግሎቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል። አይቋረጥም። አይቆምም። ዋናው ተደራሽ እንዲሆን የሚፈለገውም የቴሌቪዥኑ ነውና እሱ ተጠናክሮ ነው የሚቀጥለው። እሁድ፣ ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ዝግጅታችን በመረጃ ቴቪ እና
በ https://mereja.tv ዌብሳይት ላይ ሳይቋረጥ ይቀጥላል። እሱን ምንም ማድረግ አይችሉም። በዚህ አዛዦቹ እኛው ነን።
•••
ከኢትዮጵያ ውጪ ያላችሁም አባል ሳትሆኑም ለጥቂት ጊዜያት በዚያው በመረጃ ቴቪ ዌብሳይት ላይ መርሀ ግብሮቼን መከታተል ትችላላችሁ።
አበደን አዛኜን እጅ መስጠት ብሎ ነገርማ የለም። አበደን አልኳችሁ።
ድል ለኢትዮጵያዬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን።