>

"ኑ በመተባበር ሀገር እናድን...!

 
“ኑ በመተባበር ሀገር እናድን…!
                 ህብር ኢትዮጵያ 
* “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ…!”
             ተመስገን ደሳለኝ በቅርቡ የፃፈው
* “እስኪ ተዋደዱ ይያያዝ እጃችሁ ካለበለዝያማ በምን ያስታውቃል እኛን መውደዳችሁ?”
                    ቴዲ አፍሮ 
* “እጅ ለእጅ ተያይዘን ሀገር እናድን…!”
                       የወቅቱ ጥሪ 
በደግሰው አለሙ

            መጭው ምርጫ በብዙ ችግር የተሞላ ነው። በምርጫው ማን ያሸንፋል ሳይሆን የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል፣ ህዝቡን ማን ወደ አንድነቱ ይመልሰዋል እና የአዲሳ አበባ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለው ነው አሳሳቢው።
      ይህ ሁኔታ ያሳሰበው ህብር ኢትዮጵያ ከአጉል ፉክክር በወጣ መልኩ ሀገርን እና ህዝብን የሚያድነው በመሰረታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ ልዩነት የሌላቸው ፓርቲዎች እንዲተባበሩ እና በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፏል።
       ፓርቲዎችም ከግል ፉክክር ከቂም በቀል ወጥተው መለየት የማይቻሉትን ደጋፊዎቻቸውን እና ህዝቡን አስተባብረው በጋራ በመታገል ለህዝብ እና ለሀገር ያላቸውን ፍቅር እንዲያሳዩ አንድነቱን እንዲያስቀጥሉ እንዲሁም በጋራ ይሄን የዘር ፌደራሊዝም እና ህገ መንግስት ለማሻሻል ቢሰሩ መልካም ነው።
የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / Hibir Ethiopia Democratic Party  ሰዎች ኢንጂነር ይልቃልና አቶ ልደቱ ከመጀመሪያው ጀምረው አብሮ ለመስራትና ለትብብር በራቸውን ክፍት አድርገው የነበር ቢሆንም በአንዳንድ ተልካሻ ምክንያቶች የተፈለገው ጥምረት ሳይሰምር ቀርቶ ነበር። በእርግጥ የእነ አብን፣ መኢአድና ባለድራስ ጥምረት ታክቲካሊ ምን እንደሚመስል ባላውቅም ጥምረታቸው ሰምሮ እርስ በርስ ሳይፎካከሩ በአንድ ምልክትና በአንድ ተወካይ የሚወዳደሩ ከሆነ ጥሩ ጅምር ይመስለኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ህብር ኢትዮጵያ አንድም ድምጽ መባከን እንደሌለበት እና እርስ በርስ ላለመፎካከር በማመን ለሁለተኛ ጊዜ የአብረን እንስራ ጥሪ አቅርቧል። ይሄ በእውነቱ ይበል የሚያሰኛና የሀገር ህልውናን ለማስቀጠል የተሻለው አማራጭ ነው። ይሄ ጉዞ እንደሚሰምር ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
 ህብር ለመግልጥ እንደሞከረው በተለይም ቀጠናው ሰላም በሆነበት የአማራ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የሶማሌ ክልል፣ ድሬደዋ አስተዳደር፣ አዲስ አበባ አስተዳደር፣ አፋር ክልል እና ጋምቤላ ላይ በአንድ ምልክትና በአንድ ሰው መወዳደር ከተቻለ ብልጽግና ወ ኢዜማ ቻው ይባላሉ።
በአንድ ምልክት እና አንድ ሰው መወዳደር ምን ማለት ነው ካላችሁኝ የምናምንበትና የተሻለ ተቀባይነት አለው የምንለው የሌላ ፓርቲ አባል ልደቱ የሚወዳደርበት የምርጫ ወረዳ ላይ ራሱን በማግለል ልደቱን ኢንዶርስ አድርጎ ታዛቢወቹም መራጮቹም ለልደቱ እንዲሰሩ ማድረግ። በለጠ ሞላ ወሎ ላይ የሚወዳደር ከሆነ የሌሎች ፓርቲ አባላት ራሳቸውን በማግለል በለጠን ኢንዶርስ አድርገው ለበለጠ የሎቢ ስራ መስራት አለባቸው።
ይሄንን ማድረግ ከተቻለ በዚህ አገር ላይ ታምራዊ ምርጫ እናካሂዳለን የፈለግነው ለውጥም ይመጣል።
ህብር ኢትዮጵያዎች. አድናቆት ውሰዱ።

ተባበሩ

ተጋገዙ

ሀገርን አድኑ

Filed in: Amharic