>

"ህዝብ ሆይ መሪን ሳይሆን መርህን ተከተል ...!!!" ልበ ብርሀኑዋ የጣይቱ ልጅ የትነበርሽ ንጉሴ

“ህዝብ ሆይ መሪን ሳይሆን መርህን ተከተል …!!!”

ልበ ብርሀኑዋ የጣይቱ ልጅ የትነበርሽ ንጉሴ

አንደበቱዋ እርቱዋና ባለ ምጡቅ አእምሮዋ የት ነበርሽ የት ጠፋች????!
ህዝብ ሆይ መሪን ሳይሆን መርህን ተከተል ካለች በውሀላ ጠፍታለች  ለማንኛውም ባለችበት ሰላም ትሆን ዘንድ ምኞቴ ነው
ዶ/ር ዐቢይ የመፅሐፍ ቅዱስ የሚመስል ጥቅስ ቢነግራችሁ እንኳን ፖለቲከኛ መሆኑን አትርሱ። ከቤታቸው ብቻ የተፈናቀሉ አይደሉም፣ እነሱ የቆጠሩት ከቤታቸው የተፈናቀሉትን ነው። እኔ ደግሞ የሚያሳስበኝ ከሙያቸው የተፈናቀሉ ብዙ ተፈናቃዮች አሉ። በጣም ትልቁ ችግራችን መሪ እንከተላለን እንጅ መርህ አንከተልም። መሪ ደግሞ ይሄዳል። ይመጣል። ነግሬያችኋለሁ፣ እናንተም አይታችሁታል። መሪው ሀጥያት ሲሰራ ሀጥያት ሰራህ አንልም። ምክንያቱን መሪ ነዋ! ስለ መርህ አንጨነቅም።
በፊት ከዚህ ሀገር ታስረው ለነበሩት ጋዜጠኞች ነፃ ሆኖ የመጠበቅ መብታቸው እንዲከበር ስንከራከር የነበርን ሰዎች ዛሬ ደግሞ ለተጠረጠሩ ሰዎች ያ መብት ተጠብቆላቸዋል ወይ ብለን አንከራከርም ምክንያቱም አሳሪዎቹ የትናንቶቹ ስላልሆኑ  ይሄ ተገቢ አይመስለኝም፤ ሁሌም መሪውን እንጅ መርሁን አናነሳውም።”
     እኔን ጨምሮ አብዛኛዉ ኢትዮጲያዉያን  በአብይ አህመድ ስብከት ፍቅር በወደቅንበት ሰአት ይች ልበ ብርሃን እህታችን የትነበርሽ ንጉሴ የአብይ አህመድን ስብከት እና አፈጮሌነት ቀድማ የተረዳች እህታችን ነች።
Filed in: Amharic