ለአዲስ አበቤ ብቸኛው አማራጭ ባልደራስ ነው…!
ዶክተር በቃሉ አጥናፉ የባልደራስ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
* … እነ እስክንድርን በማሰር ትግሉን መጉዳት ይቻላል ማቆም ግን አይታሰብም፤ ምክንያቱም ሰዎችን ማሰር እንጂ ሀሳባቸውን ማሰር አይችልም!
* ይህችን አገርና ህዝብ እያመሱ ያሉት ጥቂት ሰዎች ናቸው በብሄር ፌደራሊዝሙ ተጠቅመው ያለ እውቀትና ብቃታቸው የስልጣን የሀብት ማማ ላይ የወጡና ተስፈኛ የሆኑ አካላት ናቸው ይህን ራሻንና ዩጎዝላቪያን ያፈራረሰ ፌደራሊዝምን የሙጥኝ የሚሉት
* ሰው መመዘን ያለበት ባለው እሳቤ የእውቀት ደረጃ እንጂ በብሄር መሆን የለበትም ብሎ ባልደራስ በጽኑ ያምናል….