>
5:13 pm - Sunday April 20, 4279

"የሰዎችን ደህንነት እና ሰብዓዊ መብቶች የማስከበር ግዴታውን ይወጣ" ለሚለው ውትወታ መንግስት ጆሮ ይስጥ! (ኢሰመጉ)

አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ

 
“የሰዎችን ደህንነት እና ሰብዓዊ መብቶች የማስከበር ግዴታውን ይወጣ” ለሚለው ውትወታ መንግስት ጆሮ ይስጥ!

 


 

 የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም
 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ በኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሱ ያሉ አይነተ ብዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸው እጅግ እንደሚያሳስበው  ገልፆ፤ የሚመለከታቸው መንግስት አካላት ፈጣን እርምጃ በመውሰድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከዚህ ቀደም ባወጣቸው  አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም ድረስ የሰብዓዊ
መብቶች ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳሉ ኢሰመጉ በየሳምንቱ ከሚያከናውነው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትሎች ለመረዳት ችሏል፡፡ በዚህም በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ በመንግሥት ታጣቂ ኃይሎችና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል በሚደረግ የተኩስ ልዉዉጥ ሰዎች እንደሚገደሉ፣ የኦሮሚያ  ልዩ ኃይል በእነዚህ አካባቢዎችና ከቡኖ በደሌ ዞን ወረዳዎች፤ ጫዋቃ ወረዳ መንደር 1፣ 3፣ 5 እና 7 በሚባሉ ቦታዎች ድብደባ፣ ሕገ ወጥ እስርና ግድያ እንዲሁም “ልጆቻችሁ ኦነግ ሸኔን ተቀላቅለዋል ካሉበት አምጡ” በሚል ደካማ እናቶችና አባቶች ላይ እስርና እንግልት እንደሚፈፅም ለኢሰመጉ በሚቀርቡ አቤቱታዎች ተጠቅሰዋል፡፡ በሌላ በኩል በእነዚህ አካባቢዎች፤ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ግድያና እንግልት እየተፈፀመባቸው መሆኑን እንዲሁም የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎችና የመንግሥት ደህንነቶች ከምስራቅ ወለጋና ከቄለም ወለጋ ሰዎችን አስገድደው ወደ ሌላ አከባቢ የመዉሰድ ተግባር እንደሚፈፅሙ በቀረቡ አቤቱታዎች ተገልፀዋል፡፡  ከዚህም ሌላ በምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ፤ በጉዳቱ አርጆ ፖሊስ ጣብያ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፤  አባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫዓ ፖሊስ ጣብያና ፊንጫዓ ሸለቆ ፖሊስ ጣብያ ያሉ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት የመቅረብ  መብታቸው ተነፍጎ በጠባብ ክፍል ውስጥ ታስረው ከረጅም ጊዜ በኋላ የተፈቱ መሆኑን ከቀረቡ አቤቱታዎች ተረድተናል፡፡  በመሆኑም የተጠቀሱት ድርጊቶች በህገ-መንግሰቱ ዕውቅና ካገኙት የተያዙ ሰዎች መብቶች እንዲሁም በአገራችን እየተባባሰ  ካለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አንፃር ተገቢ አይደሉም፡፡ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ ሌሊስቱ ሀንገር ከተማም ግጭቶች ተከስተው የሰው ህይወት ማለፉን፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት መድረሱን የቀረቡ አቤቱታዎች ይጠቁማሉ፡፡…
Filed in: Amharic