>
5:18 pm - Friday June 15, 6655

ምርጫ ላይ ነን፤  የኢትዮጵያ ድል በአድዋ ጦርነት ወይስ የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ጦርነት። (ዐቢይ ኢትዮጵያው ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

ምርጫ ላይ ነን፤ 

የኢትዮጵያ ድል በአድዋ ጦርነት ወይስ የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ጦርነት።

 ዐቢይ ኢትዮጵያው ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

 


ምርጫ ላይ ነን የሕዝብ ሹማምንትን ለሥልጣን ለማብቃትና፣ባለሥልጣናቱም ወደውና ፈቅደው ለሕዝብ አገልግሎት በታማኝነት ሠርተን በአደባባይ ዕውቀታችንን እናስመሰክራለን፤ብቻ የሕዝብ ሥልጣን ስጡን ብለው ለሕዝቡ በየዕምነታቸው ቃለመሃላ ይፈጽማሉ፤ሁሉም ወደየ መንበራቸው ተቀምጠው ሕዝብ ሆነው ሊወስኑ። እንደተረከቡት ሥልጣን አደራቸውን በልተው፤እንዳመኑት ፈረስ በደንደሳችን በኩል ያረዱን ጥቂቶች አልነበሩም። ምርጫችን ተዛብቶ ሳይሆን ሰው ጨው ኣይደለም ተልሶ አይቀመስ ገብቶ በተግባሩ ካልተፈተነ፤እንዲያ እየሆነ ነው ሰው ተገኘ ብለን ሳንጨርስ እርኩስ እንደሰፈረበት የገንዘብ ኮርቻ መቀመቅ ይዞት ሲወርድ የምናገኘው።ስለዚህም በማንኛውም ጉዳያችን ላይ ምርጫችን በቅንነት ልቦና ከተመሠረተ እንደ ኢትዮጵያ የጦርነት ድሎች ቢያንስ እግዚኣብሐር ይረዳንና መንገዱን ያሳየናል፤እንደ አንቀፅ ፲፯ የውጫሌው ውል ስምምነት፣እንደ የካቲት፳፪ ፲፱፻፹፰ የዘነበው ዝናብ፣የሰርኪስ ቴሪዝያን መገኘት፤ቢትወደድ አልፍሬድ ኢልግ መኖር፣አመንበትም ወይም አላመንንበትም የእግዚአብሔር እጆች ነበሩ።
የዘመናችን ሰው ሠራሽ ምርጫ ደግሞ የኢትዮጵያን የወደፊት ሕልውና ለመወሰን በነፍስ ወከፍ ምርጫ ላይ እንገኛለን፤ዳግማዊ ምኒልክን የሚተካም ተገኝቷል፣ፊት አውራሪዎች እና ደጅ አዝማቾች  አሉን፤ባንዳዎቹም በሚሥጥር ተሰልፈዋል፣አሊያም አድፍጠዋል።የምርጫ ውሉም ተፈርሟል፣ አስፈጻሚዎችም በኮሚሽን ቦታቦታቸውን ይዘዋል፤ሕዝቡም በድምጹ ዳኝነቱን ሊሰጥ እየተጠባበቀ ነው፤ልክ እንደ እድዋ ጦርነት ለኢትዮጵያ ለመዋጋት፣ምኒልክ ማርያምን እንዳትቀር እንዳሉት፤ለምርጫውም እንዲሁ።


እነዚህ ኢትዮጵያዊ ሆነው የ አገር አደራ ተቀባዮች ከሆኑት መካከል የባንዳን የክህደት ተግባር በታሪካችን ውስጥ የሚዘሩት፣የኢትዮጵያን ዕውነተኛ ታሪክ አዛብተው ይጽፋሉ።በተለይም የአማርኛን ውስጠ ሚሥጥር እና አባባል ጠንቅቀን እና መስጥረን ካልተረዳን፣በየአደባባዩ ቋንቋውን   በስ  ህ ተት ተጠቀምነው ቁጥር አማርኛችን በየዕለቱ በቁሙ እንደሚሞት ሰው ያዋርደናል፤ አሊያም ተንኮለ ቢስ ያደርገናል፤በጎነትን ከማሰብ ሕሊና ከልቦናችን በየጊዜው ካልጨለፍንለት።ለዚህ ችግራችን መፍትሄ የሚሆነን፣ አስማት ሳይሆን አማርኛን ጠንቅቆ ለማወቅ ቢያንስ አባትዬውን እና እናቲቱን ግዕዝ፤ በልሳን መማር ተገቢ ይሆናል።በዛሬው መጣጥፌ ውስጥ ግን፤ያንን ዐቢይ የቋንቋ እውቀት ዘርፍ ለማንሳት አይደለም።ከአድዋ የጦርነት ፍጻሜ ማግስት ጀምሮ ባንዳ ሹመኞች የተሻለ ተምረው ነበረና፣በአማርኛ ቋንቋ ላይ ያልፈጸሙት ደባ አልነበረም። ዓላማዬ በዚህም በኩልም ይጽዳ ለማለት ነው፤ከነዚህም የመሰሪ አቅጣጫዎችአንዱ ድሉን ከኢትዮጵያውያን የታሪክ መዝገብ ላይ ቀስ በቀስ ማደብዘዝ ኋላም ፈጽሞ ማጥፋት አንዱ መንገዳቸው ነው፤ብዙ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል ከመንገድና ከመንደር ስያሜ ጀምሮ።

ስለዚህም እንምረጥ፤የኢትዮጵያ ድል በአድዋ ጦርነት  ወይስ የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ጦርነት።ከዚህ አባባል ብቻ ልዩነቱን አውቀን በግልፅ መታረም ይገባናል፤ ይኸውም የነባንዲራን ስያሜ፣የነካዛንቺስ ሰፈራት መጠሪያዎች፣ ስያሜዎች ብዙ መገልገያ ነባር ባሕላዊ እቃዎች እና የመሳሰሉት በቋንቋ ምሁራንም ሆነ የባሕል አዋቂዎች ርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።ምክንያቱም እነዚህ ቃላት የፋሺሽት  የታሪክ ቅርፊዎች በመሆናቸው፣የሚያስተላልፉት መልዕክት ጩኧትን መቀማት ብቻ ነው፣ምክን ያቱም አርበኞች ሲፋለሙ ባንዳዎቹ በወቅቱ ተምረው ከውጊያው በፊት በሰላሙ ጊዜ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳደረጉ ይታወቃል።በሌላ በኩል ግን ናቸው የሚባሉት ኢትዮጵያውያን ባንዳዎች ስለነበሩ የቋንቋ ችሎታቸው ውሱንነት መሆን የወረሷቸውን ደካማ ጎኖቻቸውን ማሳያዎቻቸው ናቸው፤ ስለዚህ በሁሉም የሙያ መስክ የአድዋ ጦርነት በየአቅጣጫው የፋሺሽቶችን አሻጥር ለማጥፋት ትግሉ ሊቀጣጠል ይገባዋል።

እናም ወደ ትክክለኛው አማርኛ ቋንቋ መባል ያለበት እንዳይነገር ስለመደረጉ ይባስ የፋሺሽት ሕውሃት ባለፉት የሃያ ዘጠኝ ዓምታት ችግሩን አስፍቶታል። በዕውነት የትኛው ነው የኢትዮጵያን የድል ታሪክ የሚገልፅ፥የአድዋ ድል ማለት ወይስ የኢትዮጵያ ድል፤በአንጻሩም በአድዋ ጦርነት፦ የፋሺሽት፡ሕውሃትን አሻጥር በቋንቋም አጠቃቀም ልናጋልጥ ይገባናል።ለምን ቢባል ይህን የተፋለሰ አገላለጽ ተንተርሰው ነው ብዙ ወገኖቻችን በድላችን ስያሜ አሰጣጥ የኢትዮጵያ ድል ባለመባሉ ምክንያት ኢትዮጵያውያን ወደተሳሳት ትርጓሜ የአድዋ ድል በማምራታቸው የታሪኩን አቅጣጫ በማሳት እንዲነገር እያደረጉ ባለቤትነቱ በተወሰኑ ጎሳዎች ውስጥ እንዲያንሰራፋ የተደረገው፤እንደውም የዚያኛው ድል ወይም የዚያኛው ክልል ለዚህኛው ምኑ ነው በማለት ማጣጣልና የ አንድነት መቀነታችንን ኢትዮጵያዊነትን የመበጣጠስ ሴራ መሆኑን ጥቂቶች ነበሩ የተገነዘቡት፣አሁን ግን በሚሊዮን ተቆጥረናል።እናም ቋንቋው ሲዛነፍ ፤መንገዳችንም ሆነ አመለካከታችን ወደተሳሳቱ አቅጣጫዎች ይመሩናል።በመሆናቸውም የትግሬ ዘር ብቻ የአድዋን ጦርነት እንደተዋጋ ለማስመሰል እና የተሳሳተ የባለድል ታሪክ ለመተረክ በጣም ፎቶኮፒ በሚመስል አገላለጽ የባለቤትነትን ድርሻ ለመወሰን ያለይሉኝታ በመሰሪ አገላለፅ ታሪካችንን ሲፈቀፍቁት ይታያሉ።አናም የአንድ ጎሳ ጦርነት እና የድል ባለቤትነትን ብቻ መሆኑን የሚያሳዩ የፈጠራ ታሪኮች በመከሰት ላይ ናቸው።
ስለሆነም የጦርነቱ ባለቤት የአድዋ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በመሆኑ ትክክለኛ አባባሎች መኖራቸው በመረጃ ላይ ተመርኩዘው የአድዋ ድል ሐውልት በአድዋ እንዲቆምና እነማን በጦርነቱ ላይ ተዋግተው በተገቢው ይዞታ ተጠንቶ ሊመዘገብ ይገባል።የግድ ይላል፤ያውም በሰሜን የተፈጠሩትን ጦርነቶች ሰበብ እና ምክንያቶቹን ማንሳቱን አላስፈላጊነቱ እስኪታመንበት፣ለጊዜው ሐቁን መራራ ታሪክ ቆልፈንበት እነማን መስዋት እንደሆኑ፤የት እንደወደቁ ሌሎችንም የጦርነቱ መረጃዎች እስከቀበሌ ድረስ ወርደው በኢትዮጵያ ግዛት በሙሉ፤በ አዲስ አበባ ብቻ ሳይወሰን በመላው ኢትዮጵያ ሊመዘገቡ ይገባቸዋል።እናም አድዋ አውራጃ የጦርነት ቀጠና ቦታ እንጂ የጦርነቱ ባለቤት አይደለም፤ የጦርነቱ ባለቤት ኢትዮጵያ ብቻ ናት ባለቤቱ፤አድዋ ውራጃ አይደለችም፤አልነበረችምም ስለዚህም ነው ድሉ የኢትዮጵያ ብቻ የሚሆነው፤የሁሉም ኢትዮጵያውያን።
ስለዚህ መባል ያለበት “የኢትዮጵያ ድል ከአድዋ ጦርነት፣” ነው እንጂ፤የአድዋ ድል ከኢትዮጵያ ጦርነት ሊሆን አይችልም።በምርጫችን አባባሎቹ ይመሳሰሉ እንጂ ባለቤቱ ላይ ግን ልዩነት አላቸው፤ዕውነቱ ፻፳፭ ኛው የኢትዮጵያውያን ድል፣ከአድዋ ጦርነት የመጣ ነው፤ይህ ነው መለመድ ያለበት፤የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ጦርነት አይደለም፣ለምን ቢባል የድሉ ባለቤት ኢትዮጵያውያን ጦርነቱን ከመምራት ጀምሮ እስከ ቀብር ፍጻሜው ድረስ የተዋጉ በመሆናቸው።ለማጠቃለል የሚወጡት ምስሉችም ሆኑ ሎጎዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፍታ እንደሚያሳዩ በጥንቃቄ ሊታዩ ይገባል፤የኢትዮጵያ ድል በአድዋ ጦርነት ባለቤቱ ማን እንደሆነ ሐቁን ፍንትው አድርጎ ታሪካችንን ያሳያልና።           በነገራችን ላይ አድዋ የሮም ሰላቶዎች በመጨረሻ የተቀበሩበት እንጂ ቢያንስ ከሦስት ያላነሱ ጦርነቶች ዳግማዊ ምኒልክን መንገድ ላይ ለማስቀረት የተደረጉ ጠላት የማፈግፈጊያ ጦርነቶችን አድርጓል፤እንደ ኮንከር እና ሴካ ካርታ ጨዋታ ሳይሆኑ፣እንደገበጣ እና ቼዝ ያሉ የጭንቅላት ችሎታ የሚጠይቁ የስልት አዕምሮ መመዘኛዎችን በዘመናችንም በዐቢይ ልቦና እያየን ነው።

Filed in: Amharic