>
5:21 pm - Monday July 20, 3812

የኦሮሞ አክራሪ ፖለቲከኞች አብን የሚፈሩበት ሚስጢር....!?! (ሸንቁጥ አየለ)

የኦሮሞ አክራሪ ፖለቲከኞች አብን የሚፈሩበት ሚስጢር….!?!

ሸንቁጥ አየለ

ታዬ ደንደዓ የሚባል ኦነግ/ኦህዴድ ሰሞኑን አብን ለምን ተቃወምኩት የሚል ትንታኔ ሲሰጥ አይቸዉ አሳቀኝ::በቃ እነሱ ብቻ ብልጥ የሆኑ ይመስላቸዋል::
ታዬ ደንደዓ የዝንጀሮ ተጠይቁን ደርድሮ አብንን የተቃወምኩት በዚህ ምክንያት ነዉ ይለናል::የኦሮሞ አክራሪ ፖለቲከኞች አብንን የሚቃወሙበት ዋናዉ ምክንያት ግን የብሄረተኝነትን ጉልበት ስለሚያዉቁት ነዉ::
ብሄረተኝነት ጉልበቱ ጉድ ነዉ::ለምሳሌ እኛ ካህን ናቸዉ ያልናቸዉ የተዋህዶ ቀሚስ የለበሱ የኦሮሞ አክራሪ ካህናት ከአክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጋር ወግነዉ ኦርቶዶክሶች በተፈጨፉበት ሰሞን መስቀላቸዉን ወርዉረዉ ቀሚሳቸዉን በጀለቢያ ቀይረዉ “ክርስቲያኖች በኦሮምያ መታረዳቸዉ ልክ ነዉ::እንዲያዉም የታረደ የተገደለ ክርስቲያን የለም የተጨፈጨፉት ክርስቲያን ነን የሚሉ ምኒሊክን ተከትለዉ የሄዱ ሰዎች ናቸዉ” ብለዉ ጥቂት ሳይቀፋቸዉ ከክርቶስ ይልቅ የብሄራቸዉ አክራሪ ፖለቲከኞች ጉዳይ በልጦባቸዉ ምስክረነት ሲሰጡ ነበር::
የትግሬ አክራሪ ብሄረተኛ ፖለቲከኞችም ባህሪ ይሄዉ ነዉ::ግማሽ ሚሊዮን አማሮች ከጉራ ፋርዳ በተፈናቀሉ ሰሞን ጉራ ፋርዳ በመሄድ ከአንድ ሽህ ገጽ በላይ ሰንድ አዘጋጅተን ነበር::ይሄንኑ አንድ ሽህ ገጽ የተከተለ ሌላ ከሁለት መቶ በላይ ገጽ ያለዉ በጉራ ፋርዳ ባሉ 24 ቤተክርስቲያኖች ላይ የደረሰዉን መቃጠል:መፍረስ እና መዘረፍ የሚያብራራም ሰነድ አዘጋጅተን ነበር::በእራሴም እጅ ለአንዳን አባቶች ኮፒዉን አስገብቼላቸዉ ነበር::ኮፒዉን ከሰጠሁዋቸዉ አንዱ ታዲያ አንድ አክራሪ የህዉሃት ካድሬ የሆኑ መለኩሴ መሳይ ሰዉ ነበሩ::እሳቸዉም እንደ አክራሪዉ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ካህን እየሳቁ “እነዚህ እኮ ተፈናቀሉ አይባልም::ቤተክርስቲያናቱም ያለ አግባብ የተሰሩ ናቸዉ::ዛፍ ጨፍጭፈዉ ነዉ የተባረሩት እየተባለ ነዉ” ሲሉ የመለስን ንግግር ደግመዉልኝ ነበር::እኔም በጣም  “በህይወት ዘመንዎት ከዚህ የበለጠ መከራ በትግራይ ህዝብ ላይ ሲወርድ ያያሉ::አሁን አይንዎትን የጨፈኑት እና በቤተክርስቲያን ጥፋት ላይ የተሳለቁት ዛሬ ቤተክርስቲያኑ የአማራ ቤተክርስቲያን ነዉ ብለዉ ነዉ::ነገ ግን በትግሬ ክርስቲያኖች ላይ ከዚህ የበለጠ መከራ እንደሚወርድ እንዳይጠራጠሩ” ብዬ ከቢሮአቸዉ መዉጣቴ ትዝ ይለኛል::
ዋናዉ ነጥብ ምንድን ነዉ? ዋናዉ ነጥብ የብሄረተኝነትን ጉልበት ብሄረተኞቹ የኦሮሞ እና የትግሬ አክራሪዎች በደንብ ያዉቁታል::ኢትዮጵያን ተባብረዉ ያፈረሷት እና ኢትዮጵያዊነትን ወደ ብሄር ደረጃ ዝቅ ያደረጉት ይሄንኑ የብሄረተኝነት ጉልበት ተጠቅመዉ ነበር::
ኢትዮጵያዊ ነዉ ብለህ ያልከዉ ሰዉዬ የነገዱ እና የዘሩ አክራሪ ፖለቲከኞች ወንጀል ጉዳይ ሲሆን አይኑን ጨፍኖ ወንጀላቸዉን ይደግፋል::እንኳን ሊቃወማቸዉ እንዴያዉም ምክንያት እየፈለገ ያገናቸዋል::ደም ከዉሃ ይቀጥናል እንዲሉ ነዉ ነገሩ::ካህን ነዉ: ፓስተር ነዉ: ምሁር ነዉ: የሀገር ታሪክ አዋቂ ነዉ : ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነዉ የተባለዉ ሁሉ የራሱ ነገድ አክራሪዎችን ወንጀል አይቃወምም::ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን በአክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እጂ ሲፈናቀሉ:ሲሳደዱ:ሲገደሉ:ሲጨፈጨፉ አንድም የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ ወጥቶ ይሄን ያወገዘ የለም::ይባስ ብሎም ካህን ያልናቸዉ ሳይቀሩ መጨፍጨፋቸዉ ልክ ነዉ::የተጨፈጨፉት ምኒሊክን ተከትለዉ የሄዱት ናቸዉ እስከ ማለት የተራመዱ ናቸዉ::
የብሄር ፖለቲካ ለሚስጢር አስተማማኝ ነዉ::ወዳጄ ብለህዉ ካንተ ጋር ተኝቶ ከነገዱ አክራሪ ፖለቲከኛ ጋር ሲሻተት ታገኘዋለህ::ነገዱ ነዋ::ደም ከዉሃ ይቀጥናል ይባል የለም እንዴ?የብሄር ፖለቲካ ጉልበቱ ብዙ ነዉ::ጭፍን ደጋፊዎች:በጥላቻ ያበዱ ተከታዮች:ገንዘባቸዉን ለኛ ነገድ ለሚሉት ፖለቲካ ለመመደብ የማይሳሱ ጨካኝ ደጋፊዎችን ያፈራልሃል::የነገርካቸዉን ሁሉ የሚያምኑ አምላኪ ተከታዮችንም ያፈራልሃል::
በመሆኑም የኦሮሞ አክራሪ ፖለቲከኞች እነሱ አማራን የሚያሳርደዉን መርዛማ  ትርክታቸዉን  ተሸክመዉ ትዉልድ እያበላሹ:ሀገር እያመሱ:ያዩትን ሜዳ ሁሉ የኛ ነዉ እያሉ አማራ በነገዱ ሲደራጅ የሚከተለዉን ነገር ያዉቁታልና ይቃወማሉ::ሀገሪቷን የትግሬ አክራሪ ፖለቲከኞች 27 አመታት በዘር ፖለቲካ ከረጢት ዉስጥ ሆነዉ ሲመሯት እንደነበረዉ አሁንም የኦሮሞ አክራሪ ፖለቲከኞች በዘር ፖለቲካ ከረጢት ዉስጥ ሆነዉ ኢትዮጵያን እያመሷት የዘር ፖለቲካ አደረጃጀትን ይቃወማሉ::የአማራን ዘር ለማጥፋት ከቤኒሻንጉል እስከ ወለጋ:ከወለጋ እስከ ሀረር:ከሀረር እስከ መላዉ ኦሮሚያ እየሰሩ ሳለ አማራ እራሱን እንዳያድን በነገዱ አይደራጅ ይሉሃል::እነሱ ብልጥ መሆናቸዉ ነዉ::
የዘር ፖለቲካ ጅብ ነዉ::ሆኖም ጅብ ከሚበላህ በልተህዉ ተቀደስ እንደሚባለዉ የአማራ ህዝብ እራሱን ለረዥሙ ትግል ማዘጋጀት አለበት::የዘር ፖለቲካ ከኢትዮጵያ በህግ እስኪታገድ ድረስ አማሮች በስፋት በነገዳቸዉ መደራጀት እንዲሁም ከሌሎች በኢትዮጵያዊነት ከደተደራጁ የአማራ ህዝብ ወዳጅ ከሆኑ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር አብሮ መቆም ይገባቸዋል::ምክንያቱም የአማራ ህዝብ አሁን ጥምር የህልዉና አደጋ ከፊቱ ተጋርጦበታል እና::አንደኛዉ በራሱ በነገዱ ላይ የተጋረጠ የህልዉና አደጋ ሲሆን ሁለተኛዉ እንደ ሃገር ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር የሚጋራዉ የሀገሪቱ ህልዉና ጉዳይ ነዉ::እንደ ኦህዴድ/ኦነግ ያለ ሀይል ሳይከስም የአማራ ህዝብ ሰላም ያገኛል : ከመጨፍጨፍ ይድናል ብሎ የሚያስብ ሞኛሞኝ የአማራ ምሁር ብዙ ነዉ::ህዉሃት 27 አመታት ያረደችዉ ያሳረደችዉ ያስጨፈጨፈችዉ የአማራ ህዝብ በሰፋና በከፋ ጥልቀት በኦህዴድ/ኦነግ መዳፍ ዉስጥ ገብቷል::
ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛዉ መፍተሄ የብሄር ፖለቲካ ስሩ ተነቅሎ ተቀጥቅጦ መቃጠል ሲችል ነዉ::ይሄ ግን አሁን ምኞች እንጂ እዉነት አይደለም::አንዳድ አስመሳዮች ታዲያ የብሄር ፖለቲካ መጥፋት ካለበት ለምን በብሄር መደራጀት ያስፈልጋል? የሚል ጥያቄ ሊጠይቁ ይችላሉ:: በኢትዮጵያዊነት እንደራጅ ብለህ ብትጠራቸዉ ግን የነገድ ገመድ ጎትተዉ ይዘዉ በመምጣት ጠልፈዉ ያንከባልሉሃል:: የአማራን ህዝብ በነፍጠኝነት እና በቅኝ ገዥነት የሚኮንን ቆሻሻ የፖለቲካ ትርክት ከእነ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ምናምንቴ መጽሃፍ እያጣቀሱ ይዘዉ መጥተዉ አብረን ፖለቲካ እንስራ ይሉሃል::ቀድመዉ በትንታኔ ገለዉህ ህዝብህንም ወንጀለኛ አድርገዉ ዞረዉ ሳያፍሩ እንደ ኢትዮጵያዊ ድርጅት አብረን እንሰለፍ ይሉሃል::
ስለዚህ የአማራ ህዝብ እንደ ሁኔታዉ ሁለት አይነት እንቅስቃሴዎችን እያጣመረ መጓዝ ይኖርበታል::በህብረ ብሄር ተደራጁ የሚባሉት እንደ ግ7 አይነት ድርጅቶች የአማራን ህዝብ እና ኢትዮጵያን በአንድ ጊዜ ለኦነግ/ኦህዴድ ለቆራጣ ትርፍ አሳልፈዉ ሲሸጡ አስተዉለናል::ግ7/ኢዜማ ዉስጥ የተሰባሰቡ ጸረ አማራ ኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ እናራምዳለን ባዮች ከኦነግ/ኦህዴድ ጋር እየተግማሙ በአንድ መልኩ ደግሞ አማራ ሲጨፈጨፍ የዘር ፍጅት አማራ ላይ አልተደረገም ከማለትም ዘለዉ የዘር ፍጅት ተፈጸመ አትበሉ እስከ ማለት ዘልቀዋል::ስለሆነም በርካታ ከሃዲያን እና ጸረ አማራዎች በህብረ ብሄር ድርጅት ስም ተሰግስገዉ የአማራን ህዝብ ለማስፈጀት ሊንቀሳቀሱ ስለሚችሉ አሁን ብድግ ብሎ የአማራ የብሄር ፖለቲካ ድርጅት አያስፈልግም ማለት ሞኝነት ነዉ::ኢትዮጵያ በነገድ የፖለቲካ ድርጅት እስከተመራች ድረስ የአማራ የፖለቲካ ድርጅት ወሳኝ ነዉ::ሆኖም የመዳረሻ ጉዞዎ እና ግስጋሴዉ ኢትዮጵያን ማዳን ኢትዮጵያን እጅ ማድረግ አላማቸዉ ካደረጉ ሀይሎች ጋር ተባብሮ መስራት ብሎም ኢትዮጵያን ማዳን መሆን አለበት::
ለአቢይ ድጋፍ ሰልፍ በኦሮሚያ ሲደረግ አቢይ ሆን ብሎ “አብን ጠላት” ነዉ የሚል መፈክር አሲዞ ካስወጣ ብኋላ ያንን የሰልፈኞች ፎቶ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፔጅ ላይ ለጥፎት ነበር::
እናም እነ ታዬ ደንደዓ ጭንቀታቸዉ የአማራ ፖለቲካ ድርጅት ፈጽሞ እንዳይኖር ነዉ እንጂ የአብን ጉዳይ አይደለም ያስጨነቃቸዉ::የነ ታዬ ደንደዓ ጭንቀት አማራን በኦነግ/ኦህዴድ ሲያስጨፈጭፉት ለአማራ አንድም ድምጽ የሚሆን ሀይል አለመኖሩን ማረጋገጥ መፈለጋቸዉ ነዉ::አንዳንድ የሶሺዮሎጅ ባለሞያዎች የጋብቻ ፖለቲካ የሚባል ቀልድ የለም የሚሉት ነገር እኛ ሀገር ደጋግሞ ታይቷል::የአማራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር የጋራ ታሪክ አለን ሀይማኖታችን አንድ ነዉ ባህላችን አንድ ነዉ ጥቂት የተለያዬዉ ቋንቋችን ነዉ እንጅ የሚል እምነት ቢኖረዉም ከትግራይ ህዝብ የወጡት ህዉሃታዉያን የሰሩት ግፍ የአማራ ህዝብ በዘመናት ታሪኩ ዉስጥ ተጽፎም አይገኝም::የህዉሃት የራሳቸዉ ግፍ አልበቃ ብሎ ወንጀለኛ ህሳቤአቸዉን ሌሎችን እስከ ማሸከም ድረስ ሄደዋል::ተሳክቶላቸዋልም::ዛሬም ህዉሃት የወለደቻቸዉ ኦህዴድ/ኦነግ ዉስጥ የተሰገሰጉ አንዳንድ ሰዎችን በእናታቸዉ እንዲህ ናቸዉ :ከዚህ አካባቢ ናቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ጭካኔ እና ጥላቻ የላቸዉም የሚል እዚህ እና እዚያ የሚተረክ ትርክ ቢኖርም እዉነታዉ ግን ሁሉም ኦነጋዊ/ኦህዴዳዊ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት በማድረግ የተስማማ ብቻ ሳይሆን የአማራ የዘር ፍጅት እንዳይነገር የወሰነም ነዉ::
ለዚህም ነዉ አማራዉ አንድም ድምጽ እንዳይኖረዉ አብንን ደካማ ለማድረግ ከቻሉም ለማክሰም ኢዜማ ዉስጥ ከተሰገሰጉት ሸቃጭ ፖለቲከኖች : የኦነግ/ኦህዴድ ተላላኪዎች እስከ ዋንኞቹ የኦህዴድ/ኦነግ ካድሬዎች እንደ ታዬ ደንደዓ አብንን መቃወማቸዉን ስም ማጥፋታቸዉን የቀጠሉት::የንቀታቸዉ ንቀትም አማራ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ሊመረጥ አይገባዉም እስከማለት የተራመዱት::እንግዳ እሰዉ ቤት ገብቶ ባለቤት ነኝ እንደ ማለት ነዉ::
የብሄር ፖለቲካ ጅብ ነዉ::ጅብ ከሚበላህ በልተህዉ ተቀደስ እንዲል ነገሩ የብሄር ፖለቲካ በህግ ከኢትዮጵያ እስኪታገድ ድረስ አማራ በነገዱ እየተደራጀ ኢትዮጵያን ከሚያድኑ ሌሎች የአማራ ወዳጅ ከሆኑ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር ደግሞ ተባብሮ ኢትዮጵያን ለማዳንንም እጅ ለማድረግም መስራት የብልሃት ጉዞ ነዉ::
Filed in: Amharic