>

ያብይ አህመድ እኩይ አዟሪት    (መስፍን አረጋ)

ያብይ አህመድ እኩይ አዟሪት

 

መስፍን አረጋ


ቡድሃውያን (buddhists) እንደሚሉት ያለፈው ድርጊት ያሁኑን፣ ያሁኑ ደግሞ የወደፊቱን ይነግራል (If you want to know your present look at your past.  If you want to know your future look at your present)፡፡  የዐብይ አህመድን ተዛማጅ ድርጊቶች በመስመር በማገናኘት፣ አዝማሚያ መስመሩን (trend line) አርዝሞ ወይም ዘንድቦ (extrapolate) የወደፊት ድርጊቱን አስቀድሞ መገመት የማይችል ሕጻን ወይም ሕጹጽ ብቻ ነው፡፡  የዐብይ አህመድ አካሄድ ግልጽ ስለሆነ፣ መዳረሻውን ለማወቅ ሕገ ልቦና ወይም ወል ስሜት (common sense) ብቻ በቂ ነው፡፡

የኦሮሙማው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ ባንደበቱ ጦቢያዊ በግብሩ ግን ኦነጋዊ መሆኑን ያደረጋቸውና የሚያደርጋቸው ድርጊቶች በግልጽ ይመሰክራሉ፡፡  ‹‹ዐብይ አህመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ፣ አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ›› የተባለበትም ምክኒያት ይሄው ነው፡፡  ዐብይ አህመድ ኦነጋዊ ነው ማለት ደግሞ ፀራማራ ነው ማለት ነው፣ የኦነግ አሌፍና ፓሌፍ (alpha and omega) ፀራማራነት ነውና፡፡ 

አብዛኞቻችን አገር ወዳድ ጦቢያውያን በኢተስፋ ላይ በመተሰፍ (hope against hope) የዐብይ እናት አልኦሮሞ (non-oromo) መሆን የዐብይን የኦሮሞ ጎጠኝነት ስሜት ያለዝበዋል የሚል እምነት ነበረን፡፡  ታሪክ የሚመሰክረው ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፡፡  ያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ የዚያ ብሔር ብሔርተኛ ከሆነ፣  ጥርጣሬውን ለማስወገድ ሲል ብቻ ማናቸውንም አረመኔያዊ ድርጊት ለመፈጸም ቅንጣት አያቅማማም፡፡ 

ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡  ምሥራቅ አውሮጳውያን (ቸኮች፣ ፖሊሾች፣ ዩክሬኖች፣ ክሮአቶች…) ካንግሎ ሳክሶኖች በከፋ ሁኔታ ዘረኛ መስለው ለመታየት የሚጥሩት፣  ከነጭ አይቆጥሩንም ለሚሏቸው ለምዕራብ አውሮጳውያን ነጮች መሆናቸውን ለማወጅ ነው፡፡  ያሜሪቃ ጥቁር ፖሊስ ከነጭ ፖሊስ የበለጠ በጥቁር ላይ የሚጨክነው፣ ታማኝነቱን ለነጭ አለቆቹ ለማሳየት ነው፡፡   

ባባቱ አማራ ነው የሚባለው ጌታቸው አሰፋ ያማራ ሳጥናኤል የሆነው፣ ትግሬነቱን ለማስመስከር ነው፡፡  ዐብይ አህመድ ደግሞ በናቱ አማራ ከመሆኑም በላይ ካማራ ጋር የተዋለደ በመሆኑ፣ ፀራማራነትን ከመረጠ፣ ፀራማራነቱ ከጌታቸው አሰፋ ፀራማራነት እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው፡፡  

ዐብይ አህመድ፣ ፀጋየ አራርሳና የመሳሰሉት ግማሽ አማራ የኦሮሞ ጎጠኞች በኦሮሞነታቸው ስለሚጠረጠሩ፣ ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቁና እያንዳንዷ ድርጊታቸው በጢኖፓይፋ (microscope) እንደምትመረመር አሳምረው ያውቃሉ፡፡  ትንሽ ቢሳሳቱ ግዙፍ ውለታቸው መና ቀርቶ ከሃዲወች እንደሚባሉ ነጋሪ አያስፈልጋቸውም፡፡  እስከጣፈጡ ድረስ ተላምጠው የሚተፉ አገዳወች እንደሆኑ በደንብ ያውቃሉ፡፡  ስለዚህም እነዚህ ግማሽ ኦሮሞወች ለኦሮሞ ጥቅም ሽንጣቸውን ገትረው የቆሙ መሆናቸው ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገባ ሲሉ ብቻ ከኦሮሞወች የጸነፉ ጽንፈኞች መሆን አለባቸው፡፡  ከለማበት የተጋባት፡፡  

ዐብይ አህመድ ለኦነግ ዓላማ መሳካት ሲል ማናቸውንም ጭራቃዊ ድርጊት ለማድረግ ቅንጣት እንደማያቅማማ በባሕርዳር ድርጊቱ በግልጽ ቢያሳይም፣ ግማሽ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ኦነጋውያን መቸም ቢሆን በሙሉ ልብ አያምኑትም፡፡  ስለዚህም ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ከፈለገ ትናንት ካደረገው የከፋ ዛሬ ማድረግ አለበት፡፡    ስለዚህም ዐብይ አህመድ የኦሮሙማ ቀንደኛ ጠላት ተደርገው የተወሰዱትን አማሮችን በተመለከተ የበለጠ እና የበለጠ ጭራቅ እየሆነ እንደሚሄድ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡  

ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አህመድ በማንነቱ ምክኒያት መቸም ከማይወጣበት እኩይ አዟሪት (vicious circle) ውስጥ የገባ፣ የጦቢያዊነት ለምድ የለበሰ የኦነግ ተኩላ ነው፡፡  ከዚህ የኦነግ ተኩላ በዲስኩር ሳይሆን በተግባር ጦቢያዊነትን መጠበቅ፣ ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ነው፡፡    

 

    መስፍን አረጋ 

  mesfin.arega@gmail.com

 

Filed in: Amharic