አቶ ጎዳና ያዕቆብ
* እነሱ 10 አይን ይዘው አንዱን አጥፍተው በዘጠኙ እያዩ የእኛን ያለንን አንዱን አጥፍተው
” የእኛም ጠፍቷል” ይሉናል?!?
* እህ… እስክንድር ነው ለጃዋር ማባያነት የታሰረው ? ወይስ ጃዋር ለእስክንድር ማባያነት የታሰረው???
ዶ/ር አብይ አህመድ ከነጃዋር እስር በኃላ << ለጉርሻ ስንጣላ: ማእዱን ደፋነው>> ሲል ተደምጧል:: የሲዳማን ክልልነት ጃዋር ተዋደቀለት: አብይ አህመድ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው ሲል ገለፀው: አባ ዱላ አሳለጠው: ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አበቤ ካዝናቸውን ከፍተው በድምር 150 ሚሊዮን ለገሱ:: ሲዳማን በተመለከተ በማእዱ ላይ ልዩነት የለም::
አዲስ አበባን ፊንፊኔ በማድረግ ያላሰለሰ ትግልም በማእዱ ላይ የነጥብ ልዩነት የለም:: በመጪው ምርጫም ኦፌኮና ኦነግ ተሳተፉም አልተሳተፉም የጉርሻ ጉዳይ እንጂ ማእዱ ላይ ልዩነት የለም:: ለዚህም ነው ከጃዋር ጋር ተጣሉ: ከለማ ጋር ተጣሉ የሚለው ድራማ ላይ ከአጀንዳ ያለፈ ፋይዳ የለውም ብዬ የደመደምኩት::
ማእዱን በሚመለከት ያም የኦሮሙማ ፕሮጀክት በቤተ መንግስት ያለው አብይ አህመድና በእስር ቤት ያለው ጃዋር ወይም መረራ: ዳውድ ኢብሳ: ሽመልስ አብዲሳ እያልን ስንደረድር ብንውል እነሱ ፍጽም የአላማ ጥራትና አንድነት ያላቸው:: ነገር ግን አንዳንዴ ማን ትልቅ ይጉረስ ላይ ፀብ ነው::
አንዳንዴ እስክንድር ነው ለጃዋር ማባያነት የታሰረው ወይስ ጃዋር ለእስክንድር ማባያነት የታሰረው ብዬ እጠይቃለሁ:: የኦሮሙማ ፕሮጀክትን ማስቀጠል የሚችሉ እጅግ ብዙ ጃዋሮች አሉ:: ነገር ግን አዲስ አበባን ለማዳን ስንት እስክንድሮች አሉ?
እነሱ 10 አይን ይዘው አንዱን አጥተው በተቀሩት 9 አይኖች አላማቸው ሲያስፈፅሙ: የኛን አንድ ያለችንን አይን አጥፍተው ከኛም እኮ ጠፍቷል የሚል ብልጣ ብልጥ ምክኒያት ሲያቀርቡልን የኛዎቹ ጅሎች ደግሞ ጃዋር እስከታሰረ ድረስ እስክንድርም ስራው ያውጣው ብለው ቁጭ ብለዋል::
ወዳጄ በአብይ አህመድና በእስክንድር ነጋ መካከል ያለው አለመግባባት የማእዱ ሲሆን ከጃዋር ጋር ያለው የጉርሻ ብቻ ነው::