>

አዲስአበቤ-Watch out!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

አዲስአበቤ-Watch out!!!

ኤርሚያስ ለገሰ

የነፃነት ጉዞህን ለማስጣል ብልጽግና የሐይማኖት መሪዎች፣ ታዋቂ ምሁራን፣ ባለሀብቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አርቲስቶች፣ አትሌቶች… እያዘጋጀ እንደሆነ ደጋግመን ነግረንሃል። አንዳንዶች ስለ አዲስ አበባ እና አዲስአበቤ ግድ የሌላቸው በኦሮሞ ብልጽግና ሊያስበሉህ አድርባይነትን ከጦርነት በላይ ከባድ አድርገውታል።
እነሆ! እቅዱ እየተፈፀመ ነው!!
በዓብይ አህመድ የሚመራው የኦሮሞ ብልፅግና የአዲስ አበባን ምርጫ ለማሸነፍ የተለያዩ ታክቲኮችን በመቀመር በስራ ላይ ማዋል ከጀመረ ሁለት አመት ሆኖታል። ከአነዚህ ታክቲኮች አንዱ የኦሮሞ ብልጽግና ከጀርባ የሚዘውራቸው የሃይማኖት ዘመም ፓርቲዎችን ማቋቋም ነው።
የቀድሞው ህውሃት/ኢህአዴግ በመርካቶ፣ በመሳለሚያ፣ በኮልፌ፣ በአየር ጤና፣ በሶማሌ ተራ፣ አጠና ተራ፣ በፒያሳ… ወዘተ የኃይማኖት መሪዎች ፓርቲውን ወክለው አሊያም በግላቸው እንዲወዳደሩ የማሳመንና የማማለል ስራ ይሰራ ነበር።
የዛሬው የኦሮሞ ብልጽግና ደግሞ ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው አዲስ አበባን በተመለከተ ራሱ ከሚያቀርባቸውና በግል ከሚያወዳድራቸው እጩዎች በተጨማሪ ከጀርባ የሚዘውራቸው የሃይማኖት ዘመም ፓርቲዎችን አቋቁሞ የአዲስ አበባን የነፃነት ጥያቄ ማኮላሸት ነው። አነ ዓብይ አህመድ ይሄን ሴረኛ ታክቲክ በመጠቀም እስከ 10 በመቶ የሚሆነውን መራጭ “ቅድሚያ ኃይማኖቴና የኃይማኖት ምልክቴ የሆነው መምህሬ” በማለት ከነፃነት ጥያቄው ያናጥቡታል። ይህ ታክቲክ ህውሃት/ ኢህአዴግ ከሚከተለውም እጅግ አደገኛና ከፋፋይ ነው! ሴራውንም ከአመት ከመንፈቅ በፊት ይፋ አድርገን ነበር!
Filed in: Amharic