>

ጥቁር አሜሪካዊያን (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

ጥቁር አሜሪካዊያን
የሚወዱ አፍሪቃን፤
ሲሰሙ ኢትዮጵያን
በጠላት እንደተጠቃን።
155813169_116500477102246_1291570686575717133_o.jpg
ማንም ሳያዛቸው
ታሪኳን የሚያውቁ፤
ለኢትዮጵያ ለመሞት
በፍጥነት ታጠቁ።
ዘለቁና መጡ
ውጊያ ተቀላቀሉ፤
ገጠሙት ጠላትን
የእኛ አገር እያሉ።
በዕውቀት ደባለቁት
ጦር ሜዳው  ታመሰ ፤
ለኢትዮጵያ ተሰዉ
ደማቸው ፈሰሰ።
ቀይ ጥለት ደማሙ
የሰንደቁ ዓርማ፤
ጀግኖቹ ሲወድቁ
አገር እየደማ።
መስዋእቱ በዝቶ
ምድራችን ላይ ፈስሶ፤
አልምልሞ ቢጫን
የሚያነሳው ልሶ።
የሶስቱም ቀላማት
አላቸው
 ምክንያት፤
ኢትዮጵያን በእጆቿ
መሥጥረን እንያት።
እጅ ያጣ አይተኩስም
ከጦር ሜዳ ገብቶ፤
ልብ ጀግና ይፈጥራል
ባምላክ ተመክቶ።
ምኒልክ ጥቁሩ ሰው
ማድመቅ ነበር ድርሻው፤
በድል አንቆጥቁጦ
ይሄው መጨረሻው። 

Filed in: Amharic