>

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ፤ ዐቢይ አሕመድ፣ መለስ ዜናዊ፣ ፍራንቼስኮ ክሪስፒና ቤንቶ ሙሶሎኒ!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ፤ ዐቢይ አሕመድ፣ መለስ ዜናዊ፣ ፍራንቼስኮ ክሪስፒና ቤንቶ ሙሶሎኒ! 

አቻምየለህ ታምሩ

ዐቢይ አሕመድን፣ መለስ ዜናዊን፣ ፍራንቼስኮ ክሪስፒንና ቤንቶ ሙሶሎኒ ከሚጋሯቸው ባሕርያት አንዱ  አድዋ ላይ ከፍ ብሎ ለተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የድል ሰንደቅ ዓላማ ያላቸው ስር የሰደደ ጥላቻ ነው።
ፍራንቼስኮ ክሪስፒ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመያዝ ባሕር ተሻግሮ አገራችንን የወረረውና በዳግማዊ ምኒልክ በተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ጦር አድዋ ላይ አፈር ድሜ የጋጠው የጣሊያን ጦር ጠቅላይ አዛዥ የነበረው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስቴር ነው።
ቤንቶ ሙሶሎኒ ደግሞ የክሪስፒን ራዕይ ተከትሎ የአድዋውን ድል ለመበቀል ከአርባ ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያን የወረረውና አምስት ዓመታት ሙሉ አገራችንን ፍዳዋን ያሳያት የፋሽስት ጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ነው። ሁለቱም የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ኢትዮጵያን የወረሩት በቅኝ የተያዙ የአላም ሕዝቦች የነጻነት ጮራና የተስፋ አርአያ የሆነውን አድዋ ላይ የተውለበለበውን የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ አዲስ ስበባና በመላው ኢትዮጵያ እንዳይውለበለብ ለማድረግ ነበር።
የኢትዮጵያን ባንዲራ ጨርቅ ነው ያለው የባንዳው ልጅ  መለስ ዜናዊ ስለኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ የነበረውን ጥላቻ ሁላችንም በሕይዎት ኖረን የምናውቀው ስለሆነ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የነበረውን ጥላቻ ማስታወስ አያሻም።
አድዋ ላይ ለተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ሰንደቅ ዓላማ ያለው ስር የሰደደ ጥላቻ ለብዙ ሰዎች ያልተገለጠው አፋዊ ቀለሙን የኢትዮጵያዊነት ገጽታ አላብሶ ልቡና ስራው ግን ከደቡብ አፍሪካው የአፓርታይድ አገዛዝ በእጅጉ የከፋ የአፓርታይድ አገዛዝ የዘረጋው ዐቢይ አሕመድ ነው። ሆኖም ግን ዛሬ ጭንብሉን አውልቋል። የሚመራው የአፓርታይድ አገዛዝ የካቲት 23  ቀን 1888 ዓ.ም. የጦርነቱ ፍጻሜና የአድዋ ድል በዳግማዊ ምኒልክ  ሲበሰር የተውለበለበውን የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ ነገ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የአድዋ ድል 125ኛ ዝክር ሲከበር ማውለብለው የተከለከለ መሆኑን  በዛረው ዕለት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል አስታወቋል።
እንግዲህ ጥያቄው አድዋ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች የድል ሰንደቅ አዲስ አበባ ላይ እንዳይውለበለብ በከለከለው በዐቢይ አሕመድና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይውለበለብ ባገደው በመለስ ዜናዊ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው የሚለው ነው?
ለኛ ለኢትዮጵያውያን የአድዋ ድል ሲዘከር አድዋ ላይ ከፍ ብሎ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ ውስጥ የአድዋ ድል ሲዘከር እንዳይውለበለብ በከለከለው የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ የአፓርታይግ አገዛዝ እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይውለበለብ ባዘዘው በቅኝ ገዢው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስቴር በፍራንቼስኮ ክሪስፒ መንግሥት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
አድዋ ላይ የተውለበለበውን የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ ውስጥ እንዳይውለበለብ በከለከለው በዐቢይ አሕመድ እና አድዋ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ ውስጥ እንዳይውለበለበ በከለከለው በፋሽስቱ መሪ በቤንቶ ሙሶሎኒ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
ለኛ ለኢትዮጵያውያን አድዋ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ እንዳይውለበለብ ያገደው የዐቢይ አሕመድ ድርጊት አድዋ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ እንዳይውለበለብ ካገደው መለስ ዜናዊ ያደረገውን፤ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት የመጣው ፍራንቼስኮ ክሪስፒ ካደረገውንና  አድዋ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ በመላው ኢትዮጵያ እንዳይውለበለብ በሕግ ከከለከለው ከፋሽስቱ ቤንቶ ሙሲሎኑ በምን ይለያል? እስቲ ንገሩኝ?
ከላይ የታተመው ታሪካዊ  ስዕል ከአድዋ ድል በኋላ ድል አድራጊው ሠራዊት  አድዋ ላይ  ያውለበለበውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ ሲጓዝ የጦሩ መሪ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ሠራዊታቸውን ሲመለከቱ ያሳያል። ከንጉሠ ነገሥቱ በኋላ ቆመው የሚታዩት የራስ ልብ የለበሱ የጦር መሪም  የሚያውለበልቡት አድዋ ላይ የተሰቀለውን የኢትዮጵያ ድል አድራጊዎች ሰንደቅ ዓላማ ነው። ስዕሉን የሳሉት አድዋ የተማረኩ የጣሊያን ወታደሮች ናቸው። ዐቢይ አሕመድ ነገ የአድዋ ድል በሚዘከርበት ክብረ በዓል  ላይ እንዳይውለበለበ ያገደው ይህንን አድዋ ላይ ከፍ ብሎ የተውለበለበውን የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ ነው።
Filed in: Amharic