>

 ጸረ አማራ ፕሮፖጋንዳችሁ አክሳሪያችሁም ቀባሪያችሁም ነዉና እሱን ተዉት...!!! ! ( ሸንቁጥ አየለ)

 ጸረ አማራ ፕሮፖጋንዳችሁ አክሳሪያችሁም ቀባሪያችሁም ነዉና እሱን ተዉት…!!! !

ሸንቁጥ አየለ

ይድረስ ለአብርሃ ደስታና አንዶም ገብረ ስላሴ
 ለስልጣን መታገል መብታችሁ ነዉ።   አሁን ስልጣን ላይ ያለዉ ደግሞ ኦህዴድ/ኦነግ ነዉና እሱን ማሸነፍ እንጂ በወንድማማች ህዝብ መሀል ጠብ መዝራቱ አይጠቅማችሁም
አብርሃ ደስታ አንዶም ገብረ ስላሴ የተባሉ ግልገል ወያኔ ያንኑ የተለመደዉን የህዉሃት ጸረ አማራ ትርክት ሰሞኑን እየተረኩ ነዉ። የአማራን ህዝብ በተለመደዉ ነጥሎ የማጥቃት ወያኔአዊ ስሌት ከሌሎች ነገዶች የመነጠል ካንሰራማ ፕሮፖጋንዳ እየሰሩ ይገኛሉ።
ከትከት አድርጎ ካሳቀኝ ፕሮፖጋንዳዉ ዉስጥ ደግሞ “አድዋን ካሁን ብኋላ አናከብረዉም !ያላት ነገር ነች። አይ አብርሃ ደስታ።
ወያኔ እኮ አድዋን ለ27 አመታት አክብራዉም አታዉቅ። ግራ ሲገባት አንዴ የአድዋን ተራራ ስትቆጥር ሌላ ጊዜም የአጼ ምኒልክ ስም እንዳይነሳ የ እቴጌ ጣይቱን ስም ብቻ ስታነሳ በቅዠት ዉስጥ ኢትዮጵያዊነትን በመጥላት በሽታ ዉስጥ ኖራ ሞተች።
   ሌላው ግልገል   ወያኔ.አንዶም ገብረ ስላሴ  ደግሞ “…የርስት ጉዳይ ከተነሳ ኣሁን ካለችው ትግራይ በሶስት እጥፍ የበለጡ ኣከባቢዎች ወደ ትግራይ መካለል ኣለባቸው። 
ኣማራ ክልል ከወረረው ምዕራባዊና ደቡባዊ የትግራይ ዞኖች ባስቸኳይ ይውጣ…”
ብሎ አረፈ ምኞት አይከለከል
ለካንስሐ ወያኔ አልሞተችም። እንደናንተ አይነት ግልገል ወያኔ የጸረ አማራ በሽታ ተሸካሚዎች አላችሁ ላት፤  ለማንኛዉም  የሚጠቅማችሁ ከመሰላችሁ በጸረ አማራ ፕሮፖጋንዳችሁ ጠንክሩበት።
 ወያኔ አማራን እጎዳ ብላ ወተት በጥላቻ በጥብጣ እየጋተች ያሳደገችው ዘንዶ( ኦነግ/ኦህዴድ)  ቢሰለቅጣትም በመቃብር አፋፍ ላይ በቆሙ ርዝራዦቿ ዛሬም ” አማራ ወራሪ …. አማራ ወረራ… ” እያለች አለሙን ሁል ማደናቆሩን ተያይዛዋለች።
እስኪ ዛሬ እንኳን “ጫካ እንገባለን!  እንገነጠላለን!” ከሚል ዘመኑን የማይመጥን እሳቤ ውጡና ኦነግ/ኦህዴድን በድምጽ ስለ መጣል እቅዱ። አለዚያም ለኦነግ/ኦህዴድ ሰጥ ለጥ ብላችሁ ተገዙ። አሁን ተራዉ የኦህዴድ/ ኦነግ ነዉ። ከዚያ ዉጭ ግን በአማራ ህዝብ እና በትግራይ ህዝብ መሃክል ልዩነት ለመዝራት ጸረ አማራ ፕሮፖጋንዳችሁን አትዝሩ። አይጠቅማችሁምና።
በርግጠኝነት የምነግርራችሁ በኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝቦች መሃከል ጸብ የለም። የስልጣን ጥመኞች እንደእናንተ አንዱን ብሄር ነጥለዉ እየተሳደቡ ችግሩን አወሳሰቡት እንጅ።
ለስልጣን መታገል መብታችሁ ነዉ። አሁን ስልጣን ላይ ያለዉ ደግሞ አቢይ ነዉና እሱን ገልብጣችሁ ስልጣን ለመያዝ ደግሞ ኦነግ/ኦህዴድን ጃዋር እንዳለው ” በምርጫም በጡጫም” ማሸነፍ ግዴታ ነዉ። እናም አቅጣጫዉን የሳተ ተኩስ እየተኮሳችሁ ህዝብ ከህዝብ ለማጫረስ አትዉተርተሩ። ለወያኔም መጥፊያዋ ነዉ የሆነዉና።
Filed in: Amharic