>

የካራማራው ድል በተከበረ ቁጥር ኦነጋውያን የሚንጫጩት ለምን ይመስላችኋል...!?! (አቻምየለህ ታምሩ)

የካራማራው ድል በተከበረ ቁጥር ኦነጋውያን የሚንጫጩት ለምን ይመስላችኋል…!?!

አቻምየለህ ታምሩ

ከዛሬ 43 ዓመታት በፊት ሞቃድሾ ዚያድ ባሬ ቤተመንግሥት ቤተኛ የነበረው ኦነግ የኩባ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈው የሶማሊያን ወራሪ ጦር እንዳይወጉ፤ ይልቁንም ኢትዮጵያን በመክዳት ከሶማሊያ ጦር ጋር በመሰለፍ የኢትዮጵያን ጦር እንዲወጉ ከታች የታተመውን ደብዳቤ በሐረር ግንባር ለተሰለፉ የኩባ ወታደሮች ጽፎ ነበር።
ኦነግ ለኩባ ወታደሮች የላከው ይህ ደብዳቤ የታተመው “Horn of Africa” የሚባል ጆርናል ሲሆን ጆርናሉ ኦነግ ሐረር ለነበሩ የኩባ ወታደሮች የጻፈውን ደብዳቤ ያተመው ደብዳቤው ወደ ኩባ ወታደሮች በተላከ በዓመቱ በ1971 ዓ.ም. ነው።
ለኦሮሞ መብት እታገላለሁ የሚለው ኦነግ የኩባ ወታደሮች እንዳይዋጉ ደብዳቤ የጻፈው ሐረርጌን፣ ባሌንና አርሲን የታላቋ ሶማሊያ አካል ለማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጦር የከፈተውን የዚያድ ባሬን ወራሪ ሠራዊት ነው። የካራማራ ድል በተከበረ ቁጥር ኦነጋውያን የሚንጫጩት ከዚያድ ባሬ ጦር ጋር ተሰልፈው ኢትዮጵያ ስለወጉና በካራማራው ድል የዚያ ባሬ ጦር ብቻ ሳይሆን እነሱም አብረው ስለተሸነፉ ነው። የደብዳቤውን ሙሉ ገጾች ወደፊት በማዘጋጀው ጽሑፍ አትማቸዋለሁ።
Filed in: Amharic